ሱራ 15:9 እና የቁርኣን አጠባበቅ

መግቢያ 
ሱራ 15:9 እንዲህ ይላል፦

እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡
 
በዚህ የቁርኣን አንቀጽ መሠረት አላህ «ማስታወሻውን»(ዚክር) እንደሚጠብቅ ቃል ይገባል። «ዚክር» የሚለው ስያሜ አንዳንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያመለክት ቢሆንም(ቁርኣን 16:43፣ 21:7)፣ በዚህ አውድ ውስጥ ግን ቁርኣንን የሚያመለክት ሆኖ እናገኘዋለን። ይህም ማለት በአንቀጹ ላይ ቃል የሚገባው አላህ ቁርኣንን እንደሚጠብቅ ነው።
 
ይህን አንቀጽ መሠረት በማድረግ፣ የእስልምና ሊቃውንት አላህ ቁርኣንን በማይለወጥ፣ ተዓማኒ በሆነ ሁኔታ እና ፍጹምም በሆነ መንገድ ለመጠበቅ ቃል ገብቷል ሲሉ ይሞግታሉ። እንዲህ ይነበባሉ፦

”The Qur’an is the only scripture which has been preserved in its exact original form, in its entire content, as it was revealed to the Prophet fourteen centuries ago, not a word added or removed. This is a historical fact beyond dispute. God Himself has assured us of its preservation.”

ትርጓሜው

“ቁርኣን በቀደመው መልኩ፣ በተሟላ ሁኔታ፣ ከአሥራ አራት ክፍለ ዘመናት በፊት ለነቢዩ በተገለጠው ሁኔታ፣ አንድ ቃል ሳጨመርበትና ከላዩ ላይ ሳይቀነስ ተጠብቆ የሚገኝ ብቸኛው መጽሐፍ ነው። ይህ ምንም የማያከራክር ታሪካዊ ሃቅ ነው። ጥበቃውን አምላክ ራሱ አረጋግጦልናል (ቁርኣን 15፡9)። ስለዚህ ከነቢዩ ዘመን ጀምሮ በዘመናት ሁሉ በመላው ዓለም አንድ ዓይነት የቁርኣን ቅጂ ብቻ ነው ያለው።”(Al-Ahsa Islamic Center, Before you start reading the Qur’an…, Hofus, no date, p. 4)

Its text has remained exactly as it was revealed by God, providing a challenge to every would-be perpetrator of distortion. This is irrefutable testimony to the fact that this Qur’an is God’s own book and He is the One who guarantees its preservation.

ትርጓሜው

«ጽሑፉ አምላክ እንዳወረደው በትክክለኛ ይዘቱ እንዳለ የጸና ሲሆን፣ ሊበርዙ ለሚሞክሩ ሁሉ ተፎካካሪ የሌለው ፈተና ሆኖ ይኖራል። ይህም ቁርኣን የአምላክ ራሱ መጽሐፍ ለመሆኑ እና ጥበቃውን በእርሱ ዘንድ የተረጋገጠ ለመሆኑ የማያስተባብል ምስክርነት ነው።» (Sayyid Qutb, In the Shade of the Qur’an, U.K: Islamic Foundation, vol. 10, Surahs 12-15, verse 15:9, 2009, p. 253)
 
ሱራ 15:9 እና የቁርኣን አንቀጾች መርሳት
 
እውን በሱራ15:9 እንደምንመለከተው አላህ ቁርኣንን ከመረሳት ይጠብቀዋል ማለት ነውን? በፍጹም አይደለም፤ ምክንያቱም በቁርኣን ውስጥ አንቀጾች እንደተረሱ የሚናገሩ ሁለት አንቀጾች ይገኛሉ፦
 
«(ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡ አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡
(ሱራ 87፡6-7)
 
«ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን።»
(ሱራ 2:106)
 
ሐዲሳት በሙሐመድ ሕይወት ዘመንም ሆነ ከእርሱ ሞት በኋላ ቁርኣን እንደተረሳ ወይም እንደተሻረ ምስክርነቶችን ይሰጣሉ። ከእነዚህም ውስጥ፦

Narrated Aisha: The Prophet heard a man reciting the Qur’an in the mosque and said, “May Allah bestow His Mercy on him, as he has reminded me of such-and-such verses of such a Surah.”
 
አይሻ እንዳስተላለፈችው፦ የአላህ መልእክተኛ የሆነ ሰው በመስጊድ ውስጥ ቁርኣን እየቀራ ሰሙና እንዲህ አሉ፦ «የአላህ እዝነትና ምህረት በርሱ ላይ ይሁንና፤ ይህ ሰው የረሳሁትን እንዲህ እና እንዲያ የተባሉትን የቁርኣን አያዎች እና ምዕራፎችን አታወሰኝ።» (Sahih al-Bukhari 5037; vol 6, bk 61, no 556)

Narrated Abdullah: The Prophet said, “Why does anyone of the people say, ‘I have forgotten such-and-such Verses (of the Qur’an)?’ He, in fact, is caused (by Allah) to forget.” 
 
አብደላህ እንደተረኩት፦ ነቢዩ እንዲህ አሉ፦ «ከሰዎች መካከል አንዱ ‘እንደዚህ እና እንደዚያ ያሉትን የቁርኣን አንቀጾች ረስቼአለሁ’ ለምን ይላል? በእውነቱ እርሱ እንዲረሳ የተደረገው (በአላህ) ነው።» (Sahih al-Bukhari 5039; vol 6, bk 61, no 559)

We used to recite a surah which resembled in length and severity to (surah 9) Bara’at. I have, however, forgotten it with the exception of this which I remember out of it: “If there were two valleys full of riches, for the son of Adam, he would long for a third valley, and nothing would fill the stomach of the son of Adam but dust.”

በርዝመትና በጥንካሬ ከሱራ በረዓት ጋር የሚነፃፀር ሱራ እናነበንብ ነበር፡፡ ነገር ግን ከተከታዩ ውጪ የተቀረውን ረስቼዋለሁ፡- ‹‹የአደም ልጅ በኃብት የተሞሉ ሁለት ሸለቆዎች ቢኖሩት ሦስተኛውን ይመኛል፡፡ ከአፈር ውጪ የአደምን ልጅ ሆድ የሚሞላ ምንም ነገር የለም፡፡›› (Sahih Muslim 1050; bk 5, no 2286)

‘Abdullah bin ‘Umar reportedly said: “Let none of you say, ‘I have got the whole of the Qur’an.’ How does he know what all of it is? Much of the Qur’an is gone. Let him say instead, ‘I have got what has survived.'”
 
አብደላህ ቢን ኡመር እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፦ “ከእናንተ መካከል ማንም ሰው ሙሉውን ቁርኣን አግኝቼዋለሁ ብሎ መናገር የለበትም፡፡ የቁርኣን አብዛኛው ክፍል የጠፋ ሆኖ ሳለ ሁሉን አውቃለሁ ብሎ መናገር እንዴት ይቻላል? ከዚህ ይልቅ የተረፈውን አግኝቼዋለሁ ብሎ ይናገር፡፡” (Jalal ad-Deen as-Suyuti, al-Itiqan fee ‘Uloom al-Qur’an, Cairo: al-Halabi, 1935, vol. 2, p. 25)
 
ስለዚህ የቁርኣን አንቀጾች ተረስተዋል፤ ኡመርም ቢሆን ማንም ሰው ሙሉውን ቁርኣን አውቃለሁ ማለት እንደሌለበት ተናግረዋል። በሱራ 87:6-7 እና 2:106 ላይ ሁለቱም አላህ የሻው ብቻ እንደተረሳ ቢናገሩም፣ ዋናው ነጥብ ግን የአላህ መጠበቅ አንቀጾች ከመረሳት ወይም ከመጥፋት እንዳላገዳቸው ያሳያል።
 
ሱራ 15:9 እና የቁርኣን መለወጥ
 
በ15:9 ማለት አላህ ቁርኣንን ከመለወጥ ይጠብቀዋል ማለት ነውን? አይደለም፤ ምክንያቱም በቁርኣን ውስጥ አንቀጾች እንደተለወጡ የሚናገሩ ሁለት አንቀጾች አሉ።
 
በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ነገር አዋቂ ነው፡፡ «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም» ይላሉ፡፡ (ቁርኣን 16:101)
 
«ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን።» (ቁርኣን 2:106)
 
ይህ ብቻ አይደለም አንድ ቁርኣን እንደተለወጠ የሚያሳይ ምሳሌ ልጨምር፦
Narrated Al-Bara: There was revealed:  “Not equal are those believers who sit (at home) and those who strive and fight in the cause of Allah.” (Qur’an 4.95) … and at that time ‘Amr bin Um Maktum, the blind man was sitting behind the Prophet. He said, “O Allah’s Apostle! What is your order for me (as regards the above verse) as I am a blind man?” So, instead of the above verse, the following verse was revealed:  “Not equal are those believers who sit (at home) except those who are disabled and those who strive and fight in the cause of Allah.” (Qur’an 4.95)

“አል-በራ እንዳስተላለፉት፡- ‹ተቀማጮቹና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የሚታገሉት አይተካከሉም› የሚል ሱራ ወርዶ ነበር (4፡95)። ነቢዩ እንዲህ አሉ፡- ‹እስኪ ዘይድን ጥሩልኝ መጻፍያ ሰሌዳ፣ የቀለም ገንቦና (እንደ ብዕር የሚያገለግል) አጥንት ያምጣልኝ…› ከዚያ፡- ‹ተቀማጮቹና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የሚታገሉት አይተካከሉም… ብለህ ጻፍ› አሉት። በዚህ ጊዜ ዓይነ ስውሩ አምር ቢን ኡም መክቱም አጠገባቸው ተቀምጦ ነበር። እርሱም እንዲህ አለ፡- ‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለኔስ የሚሰጡት ትዕዛዝ ምንድነው? እኔ ዓይነ ስውር ሰው ነኝ።› ስለዚህ በዚህኛው አንቀፅ ፋንታ ተከታዩ አንቀፅ ወረደ፡- ‹ከምእመናን የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር ተቀማጮቹና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የሚታገሉት አይተካከሉም።›”(ቁርኣን 4፡95) (Sahih al-Bukhari 4990; vol 6, bk 61, no 512, underline added)

እዚህ ጋር እንደምናየው የ4፡95 ቀዳሚ ቅጂ ታርሞ “የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር” የሚል ተጨምሮበታል። ሱራ 2:106 እና 16:101 ስለሚለወጡት ነገሮች አላህ ባለቤቱ እንደሆነ ቢገልጹም፣ ነገር ግን ዋናው ነጥብ አሁንም አለ፦ የአላህ መጠበቅ አንቀጾች ከመለወጥ አላገዳቸውም።
 
መደምደሚያ
ሱራ 15:9 አላህ ቁርኣንን እንደሚጠብቅ ይናገራል፤ የእስልምና ሊቃውንትም ይህንን «አላህ ቁርኣንን በማይለወጥ እና በተስተካከለ መንገድ ፍጹም በሆነ ሁኔታ ይጠብቀዋል» በማለት ይተረጉሙታል። ሆኖም ቁርኣን ራሱ ስለራሱ የሰጠውን ማብራሪያ ስንመረምር፣ ይህ ጥበቃ አንቀጾች ከመረሳት ወይም ከመለወጥ እንዳልጠበቃቸው እንረዳለን። በሙሐመድ ሕይወት ዘመንም ሆነ ከእርሱ በኋላ አንቀጾች ከተረሱ ወይም ከተለወጡ፣ ቁርኣን የእስልምና ሊቃውንት እንደሚሉት በሆነ መንገድ አልተጠበቀም። ይህ ማለት በሱራ15:9 ሊቃውንቱ ቁርኣን ራሱ ያላለንን ሀሳብ እንዲናገር በማስገደድ ላይ ናቸው።

[ማሳሰቢያ፦ ይህ የትርጉም ጽሑፍ በጸሐፊው ሙሉ ፍቃደኝነት የተተረጎመ መሆኑን እንገልጻለን።]

ለሌሎች ያጋሩ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top