አርጌንስ እና የአዲስ ኪዳን ጥንታዊ ቅጂዎች
ጽሑፍ፦ Samuel Greenትርጉም፦ David Yeshua ይህ መጣጥፍ፣ በሊቁ አርጌንስ ድርሳን ውስጥ ስለ አዲስ ኪዳን የሰፈረውን ንግግር መሠረት በማድረግ የሚያብራራ እና በሙስሊሞች መካከል ለሚደረገው ውይይት እንዴት በጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት የሚተነትን ነው። ከሙስሊም ወገኖች ጋር በሚደረጉ ውይይቶች መካከል የአዲስ ኪዳን ቅጂ ተዓማኒነት በተደጋጋሚ የሚነሳ ጉዳይ ሲሆን፣ አንዳንድ ሙስሊሞች የአዲስ ኪዳን ጽሑፍ ተዓማኒ አለመሆኑን ለማስረዳት የአርጌንስን ጽሑፍ በማስረጃነት ያቀርባሉ። በዚህም ጽሑፍ የእስክንድሪያው አርጌንስን(ከ184 – 253 ዓ.ም) የኖረ የቤተክርስቲያን ሊቅ ሲሆን እውን ስለ አዲስ ኪዳን ጥንታዊያን ቅጂች የተዛባ ምልከታን ያምናልን? የሚለውን በመተንተን የማስቀምጥ ይሆናል። የሊቁ ጽሑፍ እንዲህ ይነበባል፦ “The differences among the manuscripts [of the Gospels] have become great, either through the negligence of the copyists or through the perverse audacity of others; they either neglect to check over what they have transcribed, or, in the process of checking, they lengthen or shorten, as they please.”1 “በእደ ክታባት ገልባጮች ቸልተኝነት አልያም በሌሎች እኩይ አላማ የተነሳ በወንጌላት እደ ክታባት ቅጂዎች መካከል ያለውን ልዩነት እጅግ የጎላ መሆን ችሏል። የገለበጡትን ጊዜ ሰጥተው ለመርመር ቸል ይላሉ አልያም ደግሞ በሚመረምሩበት ወቅት እንደ ልባቸው ፈቃድ ያስረዝሙታል ወይም ያሳጥሩታል።” ከዚህ ከአርጌንስ ጽሑፍ በመነሳት ሙስሊም ወገኖች የአዲስ ኪዳን እደክታብ በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ላይ ከባድ ችግሮች እንደነበሩበት እና በዚህም ምክንያት ዛሬ ላይ በእጃችን የሚገኙ ምንባባት ተዓማኒ እንዳልሆነ ይደመድማሉ፤ ጨመርም አድርገው ቁርዓን እንዲህ ዓይነት የጽሑፍ ግድፈቶች እንደሌሉበት ይደመድማሉ። አንድ ክርስቲያን ይህን የአርጌንስን አባባል እንዴት ሊረዳው ይገባል? ለዚህስ ሙግትና መልስ ለሚሻ ጥያቄ ምን ብሎ መመለስ አለበት? የሚለውን እኔ በሦስት የመልስ ነጥቦችን አስቀምጣለሁ። ነጥብ አንድ፦ ሊቁ አርጌንስ የአዲስ ኪዳንን ጽሑፍ ተዓማኒነትን በፍጹም አይክድም። ይልቅ በድርሳናቶቹ ሁሉ የአዲስ ኪዳን ምንባባትን በማጣመር የሚቀጥል ሲሆን፣ እንደ እስትንፋሰ እግዚአብሔር ቃሉን ይተማመንባቸዋል። ይህ ማለት፣ አርጌንስ አንዳንድ ሙስሊሞች ወደ ደረሱበት ዓይነት ድምዳሜ መሠረት በፍጹም አልደረሰም ማለት ነው። ነጥብ ሁለት፦ ችግሩ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለማወቅ አርጌንስ ስለጠቀሳቸው የምንባባት ልዩነቶች (textual variants) አንዳንድ ምሳሌዎችን ማየት ያስፈልገናል። እነዚህ ምሳሌዎች ከሌሉ፣ በቀላሉ የተጋነነ ወይም ተገቢ ያልሆነ የተሳሳተ ግንዛቤ በሊቁ ላይ ሊፈጠርብን ይችላል። እንደ መልካም አጋጣሚ ሆኖ፣ እነዚህ ምሳሌዎች በቀላሉ ይገኛሉ፤ ምክንያቱም አርጌንስ ራሱ በድርሳኑ ውስጥ ጠቅሷቸዋል። ብሩስ ሜትዝገር (Bruce Metzger) የአርጌንስ ጽሑፎች በጥልቀት በመመርመር እነዚህን የጽሑፍ ልዩነቶች ሰብስቧቸዋል። የምርምሩም ውጤት ‘Explicit References in the Works of Origen to Variant Readings in New Testament Manuscripts’ በተሰኘው ጽሑፍ ላይ ታትሟል። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ሜትዝገር አርጌንስ የጠቀሳቸውን 22 የጽሑፍ ልዩነቶች አቅርቦ ይወያይባቸዋል። ስለሆነም፣ አርጌንስ በትክክል ስለ ምን እየጻፈ እንደነበረ ማወቅ እንችላለን። አርጌንስ የጠቀሳቸው የ22ቱ ልዩነቶች ማጠቃለያ የሚከተለው ነው፦ መደምደሚያ ሐሳብ በሊቁ አርጌንስ ክታብ ውስጥ በጉልህ 22 የምንባብ ልዩነቶች ሰፍረዋል። ከእነዚህ ውስጥ በ20ቹ ላይ የታየው የእጅ ጽሑፎች ምንባባት ልዩነት በአጠቃላይ ከአንድ ቃል ጋር የተያያዙ ሲሆን፤ እርሱም ተመሳሳይ ትርጉም ያለው ሌላ ተመሳሳይ ቃል(synonym)፣ የተለየ የሰዋስው አወቃቀር፣ የተለየ ስም፣ የጎደለ ወይም የተጨመረ ቃል ተገኝቶ ሊሆን ይችላል። ጽሑፉ አንድ ዓይነት ሆኖ ሳለ፣ አርጌንስ አሁንም ጥያቄ የነበረበት ሁለት ምሳሌዎች ግን ነበሩበት። ይህም የሆነበት ምክንያት ሊቁ አርጌንስ ምሑርና ባለ ብዙ ቋንቋዎች ባለቤት እንደመሆኑ መጠን፣ የላቀ የጽሑፍ ጥራትና ወጥነትን ይፈልግ እንደነበረና ያንን ዓረፍተ ነገር የጻፈውም ለዚሁ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። በዚህም ሊቁ ከሰጣቸው ምሳሌዎች ውስጥ መረዳት የምንችለው፣ በአዲስ ኪዳን ጽሑፍ ላይ ምንም ዓይነት ጠንካራ የሚባል ችግር እንደሌለ ነው። ብዙውን ጊዜ ከአንድ ቃል ጋር የተያያዙ ጥቂት የጽሑፍ ልዩነቶች ያሉ ሲሆን፣ እነዚህንም ‘የምንባቤያዊ ሕየሳ’ (textual criticism) መስፈርትን በመጠቀም ለይቶ ማስተካከል ይቻላል። ስለሆነም፣ አርጌንስ አዲስ ኪዳንን በተመለከተ ችግሮች እንዳሉበት ያስቀምጣል ማለት እጅጉን ማጋነን ነው። የቀረበውም ማስረጃ ይህንንም በፍጹም አያሳይም። ሦስተኛውና የመጨረሻው ነጥቤ፦ የእስልምና ምሑራን ቁርዓንን በሚተረጉሙበት(በሚያብራሩበት) ጊዜ፣ ልክ እንደ ሊቁ አርጌንስ ሁሉ እነርሱም በቁርዓን ጽሑፍ ውስጥ ስላሉት የቅጂ ልዩነቶች(variants) ይወያያሉ። ለዚህም ሦስት ምሳሌዎች ላንሳ፦ አል-ጠበሪ እና ቁርዓን 2:2133፦ በዑስማን የተደነገገው(የተመደበው) መደበኛ የቁርዓን ጽሑፍ ‘የሰው ልጆች ሁሉ አንድ ማኅበረሰብ ነበሩ፤ ከዚያም አላህ ነቢያትን አስነሳ’ ይላል። ሆኖም በአብደላህ ኢብን መስዑድ የቁርዓን ቅጂ ላይ ‘የሰው ልጆች ሁሉ አንድ ማኅበረሰብ ነበሩ፤ ከዚያም ተለያዩ(ተጣሉ)፤ አላህም ነቢያትን አስነሳ’ የሚል ነበር። ሳሂህ አል-ቡኻሪ እና ቁርዓን 92:3 4፦ በዑስማን የተደነገገው መደበኛ የቁርዓን ጽሑፍ ‘ወንድና ሴትን በፈጠረው እምላለሁ’ ይላል። ሆኖም በአብደላህ ኢብን መስዑድ የቁርዓን ቅጂ ላይ ‘በወንዱና በሴቷ እምላለሁ’ የሚል ነበር። አብደላህ ዩሱፍ አሊ እና ቁርዓን 33:6 5፦ በዑስማን የተደነገገው መደበኛ የቁርዓን ጽሑፍ ‘ነቢዩ ለምእመናን ከነፍሶቻቸው ይልቅ ቅርብ ነው፤ ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው’ ይላል። ሆኖም በኡበይ ኢብን ካዕብ የቁርዓን ቅጂ ላይ ‘ነቢዩ ለምእመናን ከነፍሶቻቸው ይልቅ ቅርብ ነው፤ እርሱም ለእነርሱ አባት ነው፤ ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው’ የሚል ነበር። በታሪክ ሂደት ውስጥ በሙስሊሞች ዘንድ ለእነዚህ የጽሑፍ ልዩነቶች የተሰጡት ምላሾች የተለያዩ ነበሩ። በእስልምና የመጀመሪያዎቹ አሥርተ ዓመታት ውስጥ እነዚህ ልዩነቶች እንደ ችግር ይታዩ የነበረ ሲሆን፣ ሦስተኛው ከሊፋ ዑስማን አንድ ወጥ የሆነ መደበኛ የቁርዓን ቅጂ እንዲዘጋጅና ሌሎች የተለያዩ የእጅ ጽሑፎች በሙሉ እንዲቃጠሉ(እንዲጠፉ) አዟል።6 ሌሎች ሙስሊሞች ደግሞ እነዚህ የጽሑፍ ልዩነቶች ትክክለኛና ተዓማኒ (authentic) እስከሆኑ ድረስ የቁርዓኑ አካል አድርገው ይመለከቷቸዋል። ይህ ማለት ልዩነቶቹ መመዘንና መፈተሽ አለባቸው ማለት ነው። ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ሙስሊሞች ስለነዚህ የጽሑፍ ልዩነቶች ግንዛቤ የላቸውም። ‘The Encyclopedia of the Quranic Readings with an Introduction to Readings and Famous Readers’ የተሰኘው ኢንሳይክሎፔዲያ የ10,243 የጽሑፍ ልዩነቶችን ዝርዝር መረጃ ይዟል።7 ማጠቃለያ ሊቁ አርጌንስ ስለ አዲስ ኪዳን ምንባባት ልዩነት የተናገረውን ንግግር አንዳንድ ጊዜ በሙስሊሞች ዘንድ አዲስ ኪዳን ከባድ ችግሮች እንዳሉበት ለማሳየት ጥቅም ላይ ይውላል። ነገር ግን ከላይ እንዳየነው ሊቁ በፍጹም ወደዚህ ድምዳሜ አልደረሰም፤ ከሰጣቸውም ምሳሌዎች መረዳት የሚቻለው አብዛኛውን ጊዜ ከአንድ ቃል ጋር የተያያዙ ጥቂት የጽሑፍ ልዩነቶች ብቻ መኖራቸውን ነው። እነዚህንም የምንባቤያዊ ሕየሳ(textual criticism) መሥፈርቶችን በመጠቀም ለይቶ ማስቀመጥ ይቻላል። በተጨማሪም ቁርዓን ራሱ የጽሑፍ ልዩነቶች ያሉበት መሆኑንና ሙስሊሞች ቀደም ሲልም የያዙት፣ አሁንም ድረስ እየያዙት ያለ ጉዳይ መሆኑን አይተናል። ስለሆነም ሙስሊሞች አርጌንስ አዲስ ኪዳንን ተዓማኒነት የጎደለው አድርጎ ያስብ ነበር የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ለመፍጠር መሞከር የለባቸውም፤ እንዲሁም ቁርዓን ከጽሑፍ ልዩነቶች የጸዳ ነው የሚል ስሜት ለመስጠትም መጣር የለባቸውም። [ማሳሰቢያ፦ ይህ የትርጉም ጽሑፍ በጸሐፊው ሙሉ ፍቃደኝነት የተተረጎመ መሆኑን እንገልጻለን።] ማጣቀሻዎች የጽሑፍ ምንጭ፦ https://www.answering-islam.org/authors/green/origen.html
አርጌንስ እና የአዲስ ኪዳን ጥንታዊ ቅጂዎች Read More »



