Author name: Jonathan Jonathan

ሑባል(هبل)

እስልምና እና የአረቡ ጣዖታት ክፍል 1 እንደሚታወቀው እስልምና ሲነሳ በአእምሯችን ፈጥኖ የሚሳለው የገሚሱ ጨረቃ እና ኮከብ አርማ ነው። በትላልቅ መስጂዶች አናት ላይ በሚናራዎች[š] እንዲሁም እስላማዊ በሆኑ ኪነ ህንጻዎች ላይ የሚስተዋል ምልክት ነው። በሰባተኛው መቶ ክ/ዘ መጀመሪያዎቹ አካባቢ የእስላማዊ አገሮች መገበያያ የጨረቃ እና ኮከብ ምስል ያለው ሳንቲሞችን እንደሚጠቀሙ አርኪዎሎጂስቶች ያትታሉ።[²] በ11ኛው መቶ ክ/ዘ ግብጻውያን እና ሶርያውያን ይህንን ምልክት ለጌጣጌጣቸው ማስዋቢያነትም ይጠቀሙት ነበር።[Âł] በተጨማሪም አንዳንድ አገራት ማለትም እንደ አልጀሪያ፣ አዘርባጃን፣ ኮሞሮስ፣ ማሌዥያ፣ ሞሪታንያ፣ ፓኪስታን፣ ቱኒዚያ፣ ቱርክ፣ የቱርክ ሪፐብሊኳ ሰሜኒቷ ቆጵሮስ፣ ኡዝቤክስታ የምዕራብ ሰሐል …ወዘተ  እስላማዊ አገራት ይህንኑ አርማ እንደ ሀገራዊ መለያ ሰንደቅ ማድረጋቸው ይታወቃል።[⁴] እስልምና ከጨረቃ እና ኮከብ ምልክት ጋር ምን ግንኙነት አለው? ይህንን ግንኙነት ለመረዳት ዲነል ኢስላም ከመጀመሩ በፊት ጥቂት አመታት እልፍ ብለን ስንመለከት በመካ ይመለኩ ከነበሩ ጣዖታት መካከል አንዱ ሑባል(هبل)  የጨረቃ እና የከዋክብት አምላክ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያትታሉ።[⁾] ሑባል(هبل) የአሏህ ቤት ተብሎ በሚጠራው በካዕባ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የነበረው እና ለነገደ አረቡ ጣዖት አምላኪያን ሐያል አምላክ እና ታላቁ ጣዖታቸውም ነበር።[⁜] የሑባል ሌላኛው ስሙ “ሏህ” በመባል ይታወቅ ነበር። እንደ ሮበርት ሞሪ ያሉ ስኮላሮች ጥናት መሠረት ከአርኪዎሎጂስቱ ተመራማሪ ሁጎ ዊንክለር ጥናት በመነሳት “አሏህ” የሚለው ስም ለቅድመ እስላማዊ የአረብ ማህበረሰብ አፈታሪክ ውስጥ ለጨረቃ አምላካቸው ስያሜ እንደዋለ ይነግረናል።[⁡] ጁሊየስ ዌልሃውሰንም ጨምሮ የእስልምና ሐይማኖት ከማንሰራራቱ በፊት የአሏህ ቤት ተብሎ የሚጠራው ካዕባ በጣዖቱ ሑባል ሐውልቶች ቁሳቁሶችና ስዕላት ተሞልቶ እንደነበርና ሑባል የአሏህ የመጀመሪያ ስሙም እንደነበር ይናገራል።[⁸] ነገር ግን በእስልምናውም ላሉ ሊቃውንቶች ሆነ ለለዘብተኛ የታሪክ አጥኝዎች ጥያቄ የሆነው ክስተት አሏህ ስለዚህ ታላቅ የአረቦች ጣዖት በሐዲሱ ላይ አንድ ሱፍያን ኢብን ሀርብ የተባለ የቁረይሽ የጦር መሪ ከባድር ጦርነት በኋላ ድልን እንዲሰጣቸው እንደተጣራና ሑባልን እንዳመሰገነ[⁚] ከመጥቀሱ ባለፈ በቁርአኑ ውስጥ በስሙ ተጠቅሶ አለመነሳቱ ነው። እንደ እነ አል ላት አል ኡዛ እና እንደ እነ አል መናት ያሉ ጣዖቶች በቁርአኑ ውስጥ ተጠቅሰው ሳሉ ጣዖቱ ሑባል አለመጠቀሱ አጠያያቂ ጉዳይ ነው። እንደ አንዳዶች አባባል ቁርአን በካዕባ ስለነበሩ ሶስት መቶ ስልሳ ጣዖቶች እያንዳንዱን ስም እየጠቀሰ ግድ መናገር የለበትም ይላሉ። ነገር ግን ቁርአን በቁረይሾች ነገድ እንደ ሑባል በገነነ መልኩ የማይመለኩትን በስም ጠቅሶ ከገለጠ ሾለ ሑባል አለማውራቱ አግራሞትን የሚያጭር ጉዳይ ሁኖ እናገኘዋለን። ይህ የሆነበት እንደምክንያት የሚነሳው የእስልምናው ሐይማኖት ቆርቋሪ እና መስራች የሆነው መሐመድ ከጣዖቱ ሑባል ጋር የተቆራኘ ታሪክ ስላለው ነው። ነብይ ተብዬው ከመወለዱ በፊት አያቱ አብዱል ሙጠሊብ የጣዖቱ ሑባል አምላኪ እንደነበር የእስልምና ታሪክ መዛግብት ይናገራሉ።[š⁰] አብዱል ሙጠሊብ ከልጆቹ መኻል እጣው የወደቀበትን ልጅ በአሁኑ ጊዜ ቅዱስ ስፍራ ተብሎ በሚጠራው በካዕባ ለጣዖት ሑባል መስዋዕት አድርጎ ለማቅረብ በደጋን እጣ በልጆቹ ላይ ይጥላል። የደጋኑም ጫፍ የመሐመድ አባት በሆነው በአብደላህ ላይ ያመልክታል። የመሐመድም አያት ልጁን ለመሰዋት ማረጃ እንዳነሳና ነገር ግን ቁረይሾች፣ ከመኸዙም ጎሳ የሆነው አጎቱ እና ወንድሙ ልጁን እንዳይሰዋ አሳምነው አብዱል ሙጠሊብ በመሐመድ አባት አብደሏህ ምትክ የሚሆን የግመል መስዋዕት ለሑባል እንዳቀረበ እንመለከታለን።[šš] እንደውም እንደ ጠበሪ ዘገባ አብዱል ሙጠሊብ መሐመድ ጨቅላ እንደነበር ወደ ጣዖቱ ሑባል ፊት ያመጣው እንደነበር ይተርካል።[š²] ይህ ሁሉ የታሪክ ማስረጃዎች የሚያሳዩን የቁርአኑ ደራሲ መሐመድ ከሑባል ጣዖት ጋር ገና ከመወለዱ ጀምሮ ህጻንም እያለ ጥብቅ ቁርኝት እንደነበረው ያሳያል። ምንም እንኳን መሐመድ በካዕባ የሚገኙትን የሑባልን ጣዖት እና መገልገያዎችን ለማጥፋት ቢሞክርም የሑባል ጣዖት የአምልኮ ስርአቶችን ለምሳሌ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግን(የቅድመ አረባውያን የጣዖት አምላኪዎች ልምምድ ነበር ለጣዖት ሑባልም ይህንኑ የአምልኮ ስርአት አምላኪዎቹ ይከውኑ ነበር) የጣዖቱ ስም ከአምላኩ ስም ጋር ማመሳሰሉ(ቀደምት እስልምና የጣዖት አምላኪያውያን አምላካቸውን ላህ ወይም ሑባል በማለት ይጠሩት እንደነበር እና የእስልምናው አምላክ ስም ከጣዖታውያኑ ጋር ጥልቅ ቁርኝት ነበረው) በተጨማሪም የአሁኑ የሙስሊም  ማህበረሰብ የሚጠቀምበት የእምነት መለያ አርማቸው ያደረጉት በጥንቱ የአረብ ጣዖት አምላኪያን ዘንድ ለሑባል የተሰጠ የጣዖታቸው መለያ መሆኑ ይህ ሁሉ የሚያሳየን እስልም የቅድመ አያቶቹን የአረብ ጣዖታውያንን የሐይማኖት ስርአት፣ ስያሜ የማምለኪያ ቦታ(ካዕባ) እና የመለያ ምልክቱን መኮረጁ ወልደ ጣዖታውያን የእምነት መሠረት መሆኑን በግልጽ ሁኔታ መረዳት የምንችለው የሐይማኖት ቡድን እንደሆነ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳችን ግን፦ “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።”  — ዘሌዋውያን 26፥1 በማለት እንዳናመልክና እውነተኛውን ጌታ እንድንከተል ያደርገናል። እግዚአብሔር በዚህ መንገድ ይመራቸው ዘንድ ፀለይን አሜን። ማጣቀሻዎች [š] International Federation of Red Cross & Crescent Societies [²] S. Album & T. Goodwin – Syllogue Of Islamic Coins In The Ashmolean – The Pre-Reform Coinage Of The Early Islamic Period – 2002, Volume I, Ashmolean Museum: Oxford (UK), pp. 6-7 [Âł] “Pendant (Egypt) (30.95.37)”. In Heilbrunn Timeline of Art History. New York: The Metropolitan Museum of Art, 2000–. (October 2006) [⁴] Islamic flags – Flags Of The World, October 18, 2008 [⁾] Karen Armstrong (2000,2002). Islam: A Short History. pp. 11 [⁜] ዝኒ ከማሁ [⁡] Morey, Robert(1994)The Moon-god Allah in Archeology of the Middle East. Newport, Research & Education Foundation. [⁸] Wellhausen, Julius. Reste Arabischen Heidenthum, pp. 75/ Hawting, Gerald R.(1999). The Idea of idolatry & the emergece of Islam: from polemic to History. pp. 112 [⁚] Winckler, Hugo(1901) Arabisch, Semitisch, Orientalisch: Kulturgeschichlich-Mythologische Untersuchung.Berlin:W. Peiser pp. 83 [š⁰] Ibn Hisham 1/151-155; Rahmat-ul-lil’ alammeen 2/89, 90 [šš] ዝኒ ከማሁ [š²] Mohammed ibn Jarir al-Tabari, The History of the Prophet & Kings,1:157

ሑባል(هبل) Read More »

ኃልወተ መንፈስ ቅዱስ

“ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ (ἄλλον παράκλητον) ይሰጣችኋል፤”   ዮሐንስ 14፥15-16 እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ኅልው አምላክ በራሱ የቆመ ማንነት ያለውና ከሥሉሳዊ አካላት መካከል አንዱ አካል ነው። ሾለ መንፈስ ቅዱስ አካላዊ ማንነት ከማውራታችን በፊት በተወሰነ መጠን ሾለ አካል ምንነት ለመመልከት እንሞክር፦ አካል የምንለው መጠሪያ በጣም ልም ከሆነ ብናኝና በጣም ረቂቅ ከሆነ ትናኝ እጅግ በጣም ረቂቅ ከሆነ አየር ጀምሮ የመጨረሻ ጥጥርነትና ጉልህነት እስካለው ውፍረት ደንዳናነትም ድረስ በዚያ በሚገኝ ዐቅምና ብቃት እንደየ መጠኑ እንደየ መልኩ ተወስኖ እንደሚታወቅ ሁሉ፤ በዓለም ግዘፍ አካል ተብሎ ይሰየማል። በሌላም አገላለጽ በሰማይ ያለው የሚዳሰስና የሚገሰስ የሚቋጠርና በአምስቱ የስሜት ህዋሳት ተደርሶበት የሚጨበት ነገር ሁሉ በዓለመ ግዘፍ አካልነት እንዳለ ያለ መሆኑ ይታወቃልና አካል በሚል ስያሜ መጠራት ገንዘቡ ነው።[1] ነገር ግን አካል የሚለው ስያሜ በአምስቱ ህዋሳት ብቻ ለሚታወቀው ነገር ብቻ ሳይሆን ለማይታይ ለማይዳሰስ፣ ለማይገሰስ፣ ለማይቋጠር ነገር ግን በህያውነት፤ በዓለመ ነፍስ የሚኖር እኔ የሚል ነባቢ ለባዊ አለሁ ባይ ሁሉ አካል አለው ተብሎ ሊጠራ ይችላል።[2] እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የራሱ የሆነ አካል ያለው አምላክ ነው። መንፈስ ቅዱስ አካል አለው ስንል ከሌላው የስላሴ አካላት ራሱን ችሎ ለልሹ ብቁዕ የሆነ ዕውቀት ቀዋሚነት ያለው አለሁ ባይ ቁመና መሆኑን አመላካች መገለጫ ነው። ከአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ የተለያዩ የምንፍቅና አንጃዎች በመንፈስ ቅዱስ ላይ በተለያየ መንገድ አስተምህሮና ልምምዶች ተነስተው ነበር። በመንፈስ ቅዱስ ላይ ምንፍቅናዊ ዘመቻ የከፈቱትን ቡድኖች ኔውማቶማኪያውያን የሚልን ስያሜን ተሰጥተው ነበር። ኔውማቶማኪ(Pneumatomachi) ወይም በግሪኩ (Πνευματομάχοι) የሚለው ቃል ኔውማ(πνεῦμα) ማለትም መንፈስ እና ማኬ(μάχη) ውጊያ፤ በአንድ አካል ላይ በአሉታዊ ሁኔታ መነሳትን ወይም ጠበኛ መሆንን ሲገልጽ በአጠቃላይ የመንፈስ ቅዱስ ጠበኞች፣ ተቃዋሚዎች አልያም በመንፈስ ቅዱስ ማንነትና ምንነት ላይ በአሉታዊ ጎን የተነሱ ማለት ነው።[3] ለምሳሌ ያክል መቅዶናውያን (የመቅዶኒዮስን አስተምህሮተ ምንፍቅና የሚከተሉ)፣ አርዮሳውያንና ከፊል አርዮሳውያን፣ ሰባልዮሳውያ ወዘተ ተጠቃሽ ናቸው። አንዳንዶቹ የምንፍቅና ቡድኖች የመንፈስ ቅዱስን መለኮትነት ሲክዱ አንዳዶቹ ደግሞ ከነጭራሹን መንፈስ ቅዱስ ህልውና የሌለው ማለትም በራሱ የቆመ ወይም አካል የለውም ብለው ያምናሉ ያስተምራሉ። በዚህ ጽሑፍ መንፈስ ቅዱስን አካላዊ ማንነትን ለሚክዱት ቡድኖች መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምላሽን ከሰዋስው እና ከአውዳዊ ዳሰሳ አንጻር አንዳንድ ነጥቦች ለመዳሰስ እንሞክራለን፦ መንፈስ ቅዱስ የራሱ የሆነ ማንነት የለውም “እርሱ የእግዚአብሔር ሐይል ብቻ ነው” ለሚሉ መናፍቃን መጽሐፍ ቅዱሳችን መልስ አለው፦ “ወንጌላችን በኃይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ሾለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።”  — 1ኛ ተሰሎንቄ 1፥5 የተሰሎንቄን መልዕክት ጸሐፊ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ኃይልን(δυνάμει) እና መንፈስ ቅዱስን(πνεύματι េγίῳ) በማለያየት “እና(ካይ/κι὜)” በሚለው መስተጻምር ቃላቶቹን ሲሰነጥቃቸው እንመለከታለን። ይህም ማለት መንፈስ ቅዱስ ከኃይል የተለየ ማንነት እንደሆነ ያስረዳል። መንፈስ ቅዱስ በራሱ ኃይል ሳይሆን ኃይልን ባህሪው ያደረገ አምላክ ነው(ሉቃ 4፥14፣ ሐዋ 1፥18፣ ሮሜ 15፥13, 18-19)። በሐዋርያት ሾል ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የመንፈስ ቅዱስን መምጣት ሲናገር መንፈስ ቅዱስን እና ሐይልን ለያይቶ በመናገር እንጂ መንፈስ ቅዱስ ልሹ ሐይል ነው ወይም ሐይል በወረደባችሁ ጊዜ ፈጽሞ አላለም። እንዲያውም መንፈስ ቅዱስ በእነርሱ ላይ በወረደ ጊዜ ሐይልን እንደሚቀበሉ ያስረዳል። ይህም ማለት ሐይል ከመንፈስ ቅዱስ የሚወጣ ባህሪዎት ነው፦ “ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በወረደ ጊዜ ኃይልን ትቀበላላችሁ፥ በኢየሩሳሌምም በይሁዳም ሁሉ በሰማርያም እስከ ምድር ዳርም ድረስ ምስክሮቼ ትሆናላችሁ አለ።”  — ሐዋርያት 1፥8 “ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ። እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ (ἄλλον παράκλητον) ይሰጣችኋል፤”  — ዮሐንስ 14፥15-16 “ሔቴሮስ/ἕτερος” የሚለው የጽርዕ(ግሪክ) ቃል የተለየ፣ ሌላ ወይም አንድ አይነት ያልሆነ የሚል ትርጉም ሲኖረው አብዛኛውን ጊዜ በአይነትም ሆነ በአካል የተለየን ነገር የሚያመለክት ነው።[4] “አሎስ/ἄλλος” የሚለው የጽርዕ (ግሪክ) ቃል ደግሞ በአይነታቸው ተመሳሳይ የሆኑ ነገሮችን ነገር ግን በአካል ወይም በቁጥር የተለያዩ መሆናቸውን የሚገልጽ ቃል ነው።[4]ለምሳሌ፦ “በክርስቶስ ጸጋ እናንተን ከጠራችሁ ከእርሱ ወደ ልዩ ወንጌል( #ἕτερον ξὐιγγέΝΚον) እንዲህ ፈጥናችሁ እንዴት እንዳለፋችሁ እደነቃለሁ፤” — ገላትያ 1፥6 ሔቴሮን ኢዋንጌሊዮን(ἕτερον ξὐιγγέΝΚον) የሚለው ሐረግ በአይነቱም ሆነ በይዘቱ ለገላትያ ሰዎች ከተሰበከላቸው ከቀድሞው ከእውነተኛው እና ከቀጥተኛው ወንጌል ፍጹም ሌላ (ሔቴሮስ/ἕτερος) ወይም የተለየ መሆኑን የሚገልጽ ነው። “ስምዖን ጴጥሮስም ሌላውም ደቀ መዝሙር(አሎስ ማቴቴስ/ἄλλος μαθητής) ኢየሱስን ተከተሉ። ያም ደቀ መዝሙር በሊቀ ካህናቱ ዘንድ የታወቀ ነበረ፥ ወደ ሊቀ ካህናቱም ግቢ ከኢየሱስ ጋር ገባ፤”— ዮሐንስ 18፥15 በግሪኩ “አሎስ/ἄλλος” የሚለው ቃል ከስምዖን ጴጥሮስ የተለየ ማንነት እንዳለ ወይም በማንነታዊ መገለጫ ፈጽመው የተለያዩ አካላቶች እንደሆኑ የሚያሳይ ቃል ነው። ይህም ማለት ደግሞ ሁለት በአገልግሎታቸው፣ በምንነታዊ ባህሪዎታቸው(ሰው በመሆናቸው) እና የመጠሪያ ማዕረጋቸው አንድ አይነት የሆኑ ነገር ግን በአካል ሆነ በማንነታቸው ደግሞ የተለያዩ ሁለት ሰዎች መሆናቸውን ይገልጻል። የሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስን የጽሑፎቹን የሰዋሰው አወቃቀርና የቃላት አጠቃቀም በተመለከትን ጊዜ ምን ያክል ለቋንቋ ህግጋት ጥንቃቄዎችን እንደሚያደርግ እናስተውላለን። በዮሐ 14፥15-16 ላይ ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ ከእኛ ጋር ለዘላለም የሚኖረው አጽናኙ በአካል ከአብ እና ከወልድ የተለየ፤ በባህሪዎቱ እና በምንነቱ ደግሞ ከአብ እና ከወልድ ጋር ተስተካክሎተ ኑባሬ ያለው አካል መሆኑን ለመግለጽ “አሎስ/ἄλλος” የሚለው የጽርዕ (ግሪክ) ቃል እንደተጠቀመ እንመለከታለን። በተጨማሪም ቁጥር 17ን ስንመለከት፦ “ እርሱም(αὐτὸ) ዓለም የማያየውና የማያውቀው ሾለ ሆነ ሊቀበለው የማይቻለው የእውነት መንፈስ ነው፤ ነገር ግን ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር በውሥጣችሁም ስለሚሆን እናንተ ታውቃላችሁ።”  — ዮሐንስ 14፥17 በዚህ ክፍል ላይ የእውነት መንፈስ(τὸ πνεῦμα τῆς ἀληθείας/ቶ ኒውማ ቴስ አሌቴያስ) የተባለው አካል እርሱ(αὐτὸ) ሊባል የሚችል ማንነታዊ ቅዋሜ ያለው አካል እንደሆነ በግልጽ ሁኔታ ያስረዳል።[5] በተጨማሪም “..ከእናንተ ዘንድ ስለሚኖር/ὅτι παρ’ ὑμῖν μένει…” በሚለው ሐረግ ውስጥ “ስለሚኖር” ማለትም በግሪኩ ሜኔይ/ΟένξΚ በሚለው ግሳዊ ቃል በተባእታይ ጾታ የመጣ እርሱ/He የሚል ውስጠ ተውላጠ ስም እንዳለ እንመለከታለን። በተለያዩ የዮሐንስ ወንጌል ክፍሎች ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መንፈስ ቅዱስን እርሱ እያለ በተባዕታይ ጾታ ሲጠራው እንመለከታለን። ይሄ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስን አካላዊ ማንነት የሚያስረዳ ነው። መንፈስ ቅዱስ በኑባሬያዊ ማንነቱ በግዑዝ ጾታ አለመጥራቱ የራሱ የሆነ ማንነት እንዳለው አስረጂ እና አመላካች ነጥብ ነው።[6] ቀጥሎ በዮሐንስ ወንጌል ላይ መንፈስ ቅዱስ እርሱ እየተባለ በተባዕታይ ጾታ የተጠራባቸውን ክፍሎች እንመልከት፦ በዮሐንስ 14፥26 እና 15፥26 ላይ መንፈስ ቅዱስ በሶስተኛ መደብ ሰብአዊ ተውላጠ ስም ኤኬይኖስ/ἐκεῖνος “እርሱ” ተብሎ ተጠርቷል። በተጨማሪም አጽናኝ በግሪኩ ፓራክሌቶስ/παράκλητος የሚለው ስም በባለቤት ሙያ በተባዕታይ ጾታ የመጣ ስም ነው፦ “አብ በስሜ የሚልከው ግን መንፈስ ቅዱስ የሆነው አጽናኝ (ፓራክሌቶስ/παράκλητος) እርሱ (ኤኬይኖስ/ἐκεῖνος) ሁሉን ያስተምራችኋል እኔም የነገርኋችሁን ሁሉ ያሳስባችኋል።”  — ዮሐንስ 14፥26 “ዳሩ ግን እኔ ከአብ ዘንድ የምልክላችሁ አጽናኝ (ፓራክሌቶስ/παράκλητος) እርሱም ከአብ የሚወጣ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ፥ እርሱ (ኤኬይኖስ/ἐκεῖνος) ሾለ እኔ ይመሰክራል፤”  — ዮሐንስ 15፥26 በተጨማሪም በዮሐንስ ወንጌል በምዕራፍ 16 ቁጥር 7 ላይ የሚላከው አካል “እርሱን” አውቶን/αὐτὸν በማለት በሶስተኛ መደብ ሰብአዊ አገናዛቢ ተውላጠ ስም ተባዕታይ ጾታ ሲጠራው እንመለከታለን፦ ⁡ እኔ ግን እውነት እነግራችኋለሁ፤ እኔ እንድሄድ ይሻላችኋል። እኔ ባልሄድ አጽናኙ ወደ እናንተ አይመጣምና፤ እኔ ብሄድ ግን እርሱን (አውቶን/αὐτὸν) እልክላችኋለሁ።… ÂšÂł ግን እርሱ ἐκεῖνος የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል(ሆዴጌሴይ/ὁδΡγΎσξΚ)፤ የሚሰማውን (አኩሴይ/ἀκούσει) ሁሉ ይናገራል (ላሌሴይ/ΝιΝΎσξΚ) እንጂ ከራሱ (ሄአውቱ/ἑαυτοῦ) አይነግርምና፤ የሚመጣውንም ይነግራችኋል (አናንጌሌይ/ἀναγγελεῖ)።¹⁴ እርሱ (ኤኬይኖስ/ἐκεῖνος) ያከብረኛል፥ ለእኔ ካለኝ ወስዶλήμψεται ይነግራችኋልና።— ዮሐንስ 16፥7፣13፣14 በቁጥር 13 እና 14 ላይ ያሉት ግሶች ስንመለከት(ይመራችኋል፣ የሚሰማውን፣ ይናገራል፣ ይነግራችኋል …ወዘተ) “እርሱ” የሚል ተባዕታይ ውስጠ ተውላጠ ስም አለ። ይህ ሁሉ የሚያሳዩት ወይም አመላካች የሆኑት የመንፈስ ቅዱስን አካላዌ ህያውነት ወይም ኅልወትን እንደሆነ እንረዳለን። ስለዚህ መንፈስ ቅዱስ

ኃልወተ መንፈስ ቅዱስ Read More »

ዘላለማዊ ቃል ወልድ ከአብ በኑባሬው ያነሰ እና ለአብ የሚገዛ ነውን?

“…በዚያን ጊዜ ልጁ ልሹ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ይገዛል።”1ኛ ቆሮንቶስ 15፥28 “…τότε ÎşÎąá˝ś Îąá˝Ď„ὸς ὁ υἱὸς ὑποταγήσεται Ď„ῡ‌”1Cor 15:28 ሃይፖታጌሴታይ/ὑποταγήσεται የሚለው ቃል ሃይፖታሶ/ὑποτάσσω ከሚለው ስርወ ቃል የመጣ ሲሆን መታዘዝ፣ መተናነስ ወይም ደግሞ መገዛትን የሚያመለክት ነው። አንዳንድ ሐያስያንና የክርስቶስን አምላክነት የሚክዱ(ሙስሊሞችንም ያጠቃልላል) መናፍቃን በ1 በቆሮንጦስ ምእራፍ 15 ላይ አብ ሁሉን ነገር ለወልድ ካስገዛለት በኋላ ወልድ ልሹ ደግሞ ሁሉን ላስገዛለት ለእርሱ እንደሚገዛ የሚናገረውን ክፍል በመጎንተል ክርስቶስ ኢየሱስ አምላክ አይደለም ለማለት ይዳዳቸዋል። መገዛት ወይም መተናነስ (subordination) የሚለው ቃል በምን አግባብና አገባብ እንደሚውል ከማየታችን በፊት ሾለ ነባቤ እንሰተ ቃል (subordination view) በትንሹ እንመለከታለን። በSubordinationism ዙርያ እስከ 4 መቶ ክፍለ ዘመን አጋማሽ ብዙ ሀሳቦችንና አስተምህሮቶች ተሰንዝረውበታ። በዚህም ዙሪያ የሁለት ጎራዎችን ምድብ ነጥብ በነጥብ እንመልከት፦ አንደኛው፦ ሆሞዮስዮስ/ὁμοιούσιος ሆሞዮስዮስ የሚለው የግሪክ ቃል”ሆሞዮስ/ὅμοιος” “ተመሳሳይ” ወይም “ተቀራራቢ” ከሚለውና “ኡሲያ/οὐσίι” “ኑባሬ” ወይም “ባህሪ” ከሚሉት ጥምር ቃላቶች የተገኘ ሲሆን ኢንግሊዘኛው ontological subordination ሲለው የአማርኛው የቁም ፍቺው ደግሞ “ኑባሬያዊ እንሰት” ወይም “በባህሪ መተናነስን” ያመላክታል። በዚህ መርሆተ ቃል በነገረ ክርስቶስ(christology) ዙሪያ ብዙ የኑፋቄ ትምህርቶች ተነስተዋል። ከእነዚህም መካከል እውቁ የኑፋቄ መምህር የአሌክሳንድሪያው ጳጳስ አርዮስ ከክርስትናውና ከቅዱሱ መጽሐፍ ያፈነገጠ አስተምህሮ በመለኮታዊ በኑባሬ ወይም በባህሪ አንጻር ያለን መተናነስን ወይም መበላለጥን (ontological subordination) አስተማረ። በአሁኑ ጊዜ ለተነሱት የኑፋቄ ትምህርቶች ለጅሖቫ ምስክሮች ለኢብዮኒዝም(Ebionism) አስተምህሮ እንደውም ለመሐመዳውያን ለእስልምና መነሳሳት ትልቅ ጠባሳ ጭሮ ያለፈ እንደሆነ ይገመታል። ሁለተኛው፦ ሆሙስዮስ/ὁμοούσιος ሆሙስዮስ ማለት “ኡሲያ/οὐσίι” “በኑባሬ” ወይም “በባህሪ” አንድ አይነት ወይም እኩል መሆንን ያሳያል። በ325 አ.ም በኒቂያው ጉባኤ ላይ በተደረገው ጉባኤ የአርዮስን የተሳሳተ የሰቦርዲኔሽናል ፈርጅ ማለትም የወልድን ለአባቱ መገዛቱ  ontological subordination ወይም “ኑባሬያዊ እንሰት” በማውገዝ የክርስቶስ ለአባቱ መገዛቱ ግብራዊ እንሰት/functional subordination ያመላክታል በማለት ወልድ ከአብ ጋር በባህርዮቱና በኑባሬው ከአባቱ ጋር እኩል ወይም አንድ አይነት (ሆሙስዮን ቶ ፓትሪ/ὁμοούσιον τῷ Πατρί) መሆኑን ገልጸውልናል። በመጨረሻም ወልድ ለአባቱ መገዛቱ፤ መታዘዙ እና ያባቱን ፈቃድ ማገልገሉ በአባትና በልጅ መካከል ያለውን የማንነትና በባህሪም ሆነ በኑባሬ መተናነስን ሆነ መበላለጥን ፈጽሞ አያመለክትም። ቅዱስ ባስልዮስ በክታቡ፦ “…አብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ አንዲት ሰዓት እንደ ዓይን ጥቅሻ ያህል ስንኳ አልነበረም ሁል ጊዜ ከነርሱ ጋር የነበረ የሚኖር ነው እንጂ።…”[1] በማለት በሥላሴ መካከል አንዳች ብልጫ ወይ መተናነስ እንደሌለ ይሄ አባት ያስቀምጠዋል። የቆሮንቶስን መጽሐፍ ለመረዳት ከቅዱሳት መጽሐፍት ምሳሌ እንጠቀም። በሉቃስ ወንጌል ምእራፍ 2 በቁጥር 51 ላይ ጌታችን ክርስቶስ ኢየሱስ በናዝሬት ከተማ ለቤተሰቡ ይታዘዛቸው እንደ ነበር ቅዱስ ቃሉ ይነግረናል። በዚህ ክፍል ላይ ይታዘዝላቸዋል የሚለው የግሪክ ቃል ከ1ኛ ቆሮንቶስ 15፥28 ወልድ ለአባቱ እንደሚገዛ በሚናገረው ክፍል ጋር ተመሳሳይ ቃልን ነው የተጠቀመው፦ (ሃይፖታሶ/ὑποτάσσω) “ከእነርሱም ጋር ወርዶ ወደ ናዝሬት መጣ፥ ይታዘዝላቸውም (ὑποτασσόμενος) ነበር። እናቱም ይህን ነገር ሁሉ በልብዋ ትጠብቀው ነበር።” ሉቃስ 2፥51 ከዚህም የምንረዳው ክርስቶስ ኢየሱስ ለቤተሰቡ ሲታዘዝ ከእነርሱ በማንነት፤ በባህሪዎትና በኑባሬ ተናንሶ ወይም ዝቅ ማለቱን ሳይሆን በልጅና በወላጅ መካከል ያለውን መታዘዝ ወይም የመከባበር መስተጋብር በሚያሳይ ረገድ መሆኑ እውቅና ቅቡል ነው። በሌላ በኩል ደግሞ በኤፌሶን ምእራፍ 5 በቁጥር 21-22 ሐዋርያው ጳውሎስ “…ለባሎቻችሁ ተገዙ(ሃይፖታሶ/ὑποτάσσω)…”  ብሎ ሲል ሴቶች ከወንዶች እንደሚያንሱ እየገለፀ እንዳልሆነ ለገላትያ የጻፈውን መልእክት በምእራፍ 3 በቁጥር 28 ላይ ባለው በቀላሉ እንረዳለን፦ “አይሁዳዊ ወይም የግሪክ ሰው የለም፥ ባሪያ ወይም ጨዋ ሰው የለም፥ ወንድም ሴትም የለም፤ ሁላችሁ በክርስቶስ ኢየሱስ አንድ ሰው ናችሁና።”— ገላትያ 3፥28 በሴትና በወንድ መካከል ያለው መተናነስ ኑባሬያዊ(ontological) ሳይሆን ግብራዊ መተናነስን(functional subordination) ነው የሚያመለክተው። ስለዚህ በቆሮንቶስ 15፥28 ጥቅስ መሠረት ወልድ ከአብ ያንሳል ማለት በፍፁም አይቻልም ማለት ነው። ጸጋ ሰላም ይብዛላችሁ። ዋቢ ምንጭ 1] ሐይማኖት አበው ምዕራፍ ፴፫ ክፍል ፭

ዘላለማዊ ቃል ወልድ ከአብ በኑባሬው ያነሰ እና ለአብ የሚገዛ ነውን? Read More »

ማርያም የሐሩን እህት?

“የእንበረም(አምራም/עַמְרָם) ሚስት ስም ዮካብድ(ዮኬቬድ/יוֹכֶבֶד) ነበረ። እርስዋ በግብፅ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች፤ ለእንበረምም አሮንንና(አኻሮን/אַהֲרוֹן) ሙሴን(ሞሼኽ/מֹשֶׁה) እኅታቸውንም ማርያምን(ሚርያም/מִרְיָם) ወለደችለት።”— ዘኍልቁ 26፥59 በመጽሐፍ ቅዱሳችን መሰረት የአሮን (አኻሮን/אַהֲרוֹן)፣ የሙሴና(ሞሼኽ/מֹשֶׁה) የነብይቷ ማርያም(ሚርያም/מִרְיָם) አባታቸው እንበረም(አምራም/עַמְרָם) ነው።እንበረም በእብራይስጡ አምራም/עַמְרָם በ ፊደል ሜም “ם” ሲያበቃ በአረበኛው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አምራም(عمرام) በፊደል ሚም(م) የሚጨርስ ቃል ነው፦ أبْناءُ عَمْرامَ هُمْ هارُونُ وَمُوسَى وَمَرْيَمُ የእንበረምም ልጆች አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም።”— 1 ዜና 6፥3በቁርአኑ ላይ ደግሞ ኢምራን(عمران) በፊደል ኑን(ن) በሚያበቃ ስም ተጠቅሶ እናገኘዋለን[š]። ذكع نسب موسى بن عمران (የአት-አጠበሪ ታሪክ ቅጽ3) ቀዓት(ቀኻት/קְהָת) ልጅ የሆነው  እንበረም(1 ዜና 6፥2) የመጀመሪያ ልጁ ነብይቷ ማርያም ስትሆን ሙሴ እና ወንድሙ አሮን የተወለዱት 1400-1500 ዓ.ዓ እንደሆነ ይታሰባል[²]። ከዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ በዘመነ አዲስ ኪዳን ጊዜ የጌታችንና የመድኃኒታችን እናት የሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም ኢየሱስን እንደወለደች ቅዱሱ መጽሐፋችን ይነግረናል። መጽሐፍ ቅዱስ የቅድስት ድንግል ማርያምን አባትና እናት ባይጠቅስልንም ብዙ ድርሳናትና ታሪካዊ መጽሐፍት ኢዮአቄም(Joachim) እና አና(Anne) እንደሆኑ ይነግሩናል[Âł]።ባጭሩ የሙሴ እህት ነብይቷ ማርያም ጺን ምድረ በዳ እንደሞተች በኦሪት ዘኍልቁ ም.20 ቁ.1 ላይ እንመለከታለን። ቅድስት ድንግል ማርያም ከሙሴ እህት ማርያም ጋር በማንነት ሆነ በነበሩበት ጊዜ ይለያያሉ። እንደዚህ ያክል የመጽሐፍ ቅዱሱን በንጽጽራዊ ትንተና ከተመለከትን ወደ ቁርአኑ እንለፍና የመሐመድን በታሪክ ላይ የፈጸመውን ወንጀል እንመልከት፦መሐመድ በቁርአኑ ላይ የኢሳ እናት ማርያምን እና የነብዩ ሙሴ እና የአሮን እህት ማርያምን እንደ አንድ ሴት አድርጎ ማስተማሩ ነው!!!የብዙ ዘመናት ልዩነት ያላቸው በሁለት ታሪኮች መካከል ያለ መመሳሰልን ማለትም፦ ➙ የሙሳ ወንድም ሃሩን እና የኢሳ እናት ወንድም ሃሩን ➙የሙሳ አባት ኢምራን እና የኢሳ እናት አባት ኢምራን ➙ ልሡ ባለ ታሪኳ የኢሳ እናት መርየመ እና የሙሳ እህት መርየም ያለውን መመሳሰል ስንመለከት በይበልጥ ታሪኩን እንድንመረምር አድርጎናል። በዚህም ጉዳይ በርከት ያሉ ዳዒዎችና ለእስልምናና ለመሐመድ ዘብ(ጥበቃ) እቆማለሁ የሚሉት ዳዕዋጋንዲስቶች የሙግት ነጥብ ይሆኑናል ብለው የሚሰነዝሯቸውን ነጥቦች እንመልከት፦ የስም መመሳሰል፦ በዚህ የሙግት ነጥባቸው ላይ የኢሳ እናት የሆነችው የመረየም ወንድም ሃሩንና የሙሳ ወንድም ሃሩን ሁለት የተለያየ ማንነትና በተለያየ ጊዜ የነበሩ ሰዎች ናቸው ይላሉ። ይሄን የሙግት ነጥባቸውን ይደግፍልናል ብለው የሚጠቅሱት ሐዲስ አል-ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባ የሚባል ሰው ወደ ነጅራን በሄደ ጊዜ በዛ አካባቢ ያሉ ክርስቲያኖች በሱረቱል መርየምን (19:28) ላይ የተጠቀሰውን «…የሃሩን እኅት ሆይ!…» የሚልን ጽሑፍ እንዳነበቡና ሙሳ ደግሞ ከዒሣ ብዙ ጊዜ በፊት እንደነበር በነገሩት ጊዜ ጥያቄውን ይዞ ለመሀመድ አቀረበላቸው። መሀመድም በመልሳቸው “የድሮ ሰዎች ከራሳቸው በፊት ከነበሩት የነቢያቶች ስሞች ከነቢያቱ ህልፈት በኋላ ይጠቀሙ ነበር” ብሎ ነገረው(ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 38 ሐዲስ 13)። አስተውሉ፦ በሐዲሱ መሠረት የመጽሐፉ ባለቤቶች የሚባሉት ክርስቲያኖች ሾለ ኢየሱስ እናት የማርያም ወንድም ስለሆነው አሮን የሚባል ወንድም እንዳላት በጭራሽ የማያውቁ እንደሆኑና አል-ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባ የሚባለው ሙስሊም ሙእሚን ግራ ተጋብቶ ጉዳዩ ጥያቄ እንደፈጠረበት እንመለከታለን። በተጨማሪም የምእመናን እናት የሆነችው አዒሻ (ኡም አል-ሙእሚኒን/أمّ المؤمنين‎) እንኳን እንደማታውቅ ከከዓብ (ረዐ) ጋር ባደረገችው ንግግር እንረዳለን[⁴] “…’የሃሩን(የአሮን) እህት!’ (የሱራ 19 28) የሙሴን ወንድም አሮንን አያመለክትም። ዓኢሻ(ረዐ) ለከዓብ(ረዐ) “ #ዋሽተሃል” በማለት መለሰችለት።….”(ተፍሲር ኢብን ከሲር 19:28) በእነዚህ ሁሉ ሰዎች ማለትም ለአንዳንድ ሙስሊሞች እንግዳ የሆነና በመሐመድ ዘመን የነበሩት የተማሩ ዐረብ ክርስቲያኖች(የመጽሐፉ ባለቤቶች) የማየታወቅን ታሪክ መሐመድ ከየት አምጥቶ ነው አሮን(ሃሩን) የሚባል የማርያም(መርየም ) ወንድም አለ ያለን? በተጨማሪም የኢሳ እናት የሆነችው የመረየም ወንድም ሃሩንና የሙሳ ወንድም ሃሩን የተለያዩ ሰዎች ናቸው ካሉን አንድ ወሳኝና አነጋጋሪ ጥያቄ መጠየቃችን አይቀሬ ነው በታሪክ ስለማይታወቀው ሰውዬ(የኢሳ እናት የመረየም ወንድም ሃሩን ተብዬው) እንደዚህ ያክል አስፈላጊና የኢሳ እናት መረየም በእርሱ እስከምትጠራ ስላስደረገው ሰው እንዴት ቁርአን ችላ ብሎ አለፈው እናም ሾለሹ የሚናገሩ የታሪክ መዛግብት እንዴት ልናጣ ቻልን? ወይም ደግሞ የሙሴ (ሙሳ) ወንድም የሆነውን አሮንን(ሃሩን) የኢሳ እናት ለሆነችው ማርያም(መርየም) ወንድም መስሎት እንደነበር ይሄም ደግሞ የመሐመድ አላዋቂነት ማለትም በታሪክ ላይ የሰራው ወንጀል መሆኑን ማወቅ ይጠበቅብናል። ኢኽዋህ(إِخْوَة) የሙሳ ወንድም እና የመርየም ወንድም አንድ ማንነት ናቸው ስንል አማኞች ወንድም እና እህት ናቸው በሚል ቀመርና ስሌት ነው ይሉናል። ይሄም የሙግት ነጥባቸው መፍለክለኪያ(ማምለጫ) ያጣ ሰው ለማምለጫ ከሚፈጥረው ቀዳዳ ተለይቶ አልታየኝ። በሃገሬው አባባል “…ከቀዳዳ ይሻላል ጨምዳዳ…” እንደሚባለው ነጥቦቻቸው የመሐመድን ስህተት መደበቅ ሳይችልላቸው ሲቀር ከአንዱ ወደ አንዱ በይሻላል መንፈስ ይራወጣሉ። ለማንኛውም በአማኞች መካከል ኢኽዋህ(إِخْوَة) ማለትም ወንድማማችነትና እህትማማችነት ቢኖርም አሁንም የሱረቱል መርየም(19:28) ከጥያቄ አያመልጥም። ቁርአኑ ሾለ ሙሳ ከወንድሙ ሃሩን ይልቅ በስፋት ነግሮን ሳለ ሙሳ ሳይጠቀስ ሃሩን የተጠቀሰበት አግባብ ግልጽ አይደለም።ደግሞስ መርየም አባቷ ኢምራን እያለ በሙሳ ወንድም በሃሩን ስም መጠራቷ ምንን ያመለክታል? ደግሞም በሌላ ክፍል በሱራ 33 እና 66:12 ላይ “የኢምራን ሴት ልጅ” በመባሏ ወደ ሹል 19:28 ስንመጣ ከሩቅ ዘመን ባለ ሰው ስም መጠራቷ ጉዳዩን የበለጠ ብዥታንና እና ችግርን አስከትሏል። ለዚህ ሁሉ ጥያቄ መልስ የሚሆነው የመሐመድን ስህተት መቀበል ነው። በተጨማሪም መሐመድን ለዚህ ትልቅ ስህተት ያበቃው አንዳንድ ምንጫቸው በቅጡ ከማይታወቁ በክርስትናው ላይና በአይሁዳውያን መጽሐፍት ላይ ከሚጨመሩ አፈታሪኮች የሰማውን በራሱ አገላለጽ ስለሚዘግብ ነው። ሱረቱ መርየም የተወሰኑ ክፍሎች የአፖክሪፋን ታሪኮች እንደ የያዕቆብ ፕሮቶቫንጄሊየም (Protoevangelium of James) እና የሐሰተኛው-ማቴዎስ ወንጌል(gospel of Pseudo-Matthew) ካሉ አፈ ታሪኮች የአዋልድ ታሪኮች ተመሳሳይነት ያለው ታሪክ እናገኝበታለን። ለምሳሌ የቴምር ዛፉ ሾር የተፈጠረው ታሪክ[⁾] ሾለ መርየም ወላጆች ታሪክ[⁜] ለአብነት ተጠቃሽ ናቸው። በተጨማሪም በአረባዊቷ ምድር በፍልስጤም ውስጥ በቅድስት ድንግል ማርያም የተሰየመ የባይዛንታይን ቤተክርስቲያን አለ። ይህ ቤተክርስቲያን ከእስልምና ወግ ጋር ጥልቅ እና የተወሳሰበ ግንኙነት አለው እንዳለው ታሪክ ይነግረናል። በመሐመድ ዘመን አካባቢ ይህች ቤተክርስቲያን የክርስትና አምልኮ ማዕከል ነበረች። በቅዳሴ ወቅት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ áŠ¨áˆšáŠá‰ á‰ á‹ ከካቶሊክ እና ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተቃራኒ በዚህ ጊዜ ለንባብ ከአፖክሪፋ እና ከሌሎች ቀኖናዊ ያልሆኑ መጽሐፍት መነበቡ የተለመደ ነው። በተጨማሪም የተለያዩ የክብረ በዓላት የምታከብር ቤተ ክርስቲያን ነበረች። ለምሳሌ ላይ በነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ ቀን 14 ከነብዩ ኤርምያስ ሕይወትም ከአዋልድ መጽሐፍት ይነበብ ነበር። በምንባቡ ላይ መሐመድ በሱረቱል በመርየም ላይ እንዳሰፈረው አይነት ማለትም ሃሩን(አሮን) የማርያም (መርየም) ወንድም በማለት የተጠቀሰን ጽሑፍ እናገኛለን[⁡]፦ “ነቢዩ [ኤርምያስም] እንዲህ አለ – መምጣቱ ለእርስዎ እና ለሌሎች ልጆች በዓለም ምልክት መጨረሻ ይሆናል ።57 እንዲሁም የተደበቀውን ታቦት ከዓለት ላይ የሚያወጣ የለም ከማርያም ወንድም አሮን በስተቀር ።(The Lection of Jeremiah) በተመሳሳይ ሁኔታ ቁርአኑ ሾለ ማርያም (መርየም) ሲናገር ሃሩን(አሮን) የማርያም (መርየም) ወንድም እንደሆነ ዘግቦልን አግኝተናል፦ 19፥28 ÂŤ የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት፡፡ يَا أُخْتَ هَارُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ امْرَأَ سَوْءٍ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّا በመጨረሻም ለመሐመድ ዘብ እንቆማለን ባዮቹ አብዱሎች ታሪክን በመደበቅ የመሐመድን ስህተቶችና አላዋቂነቱን ለመደበቅ መፍጨርጨራቸው የሚያዋጣ አይደለም። መሐመድ ከታሪክ አንጻር ሲሳሳት ይሄ የመጀመሪያው እንዳልሆነ ከታሪክ መዛግብት ዘንድ ብዙ መረጃዎችን ስንበረብር የሚጋለጥ ሐቅ ነው። እስከምንገናኝ በክርስቶስ ፍቅር ቸር ሰንብቱ! ማጣቀሻዎች እና ማስፈንጠሪያዎች [š] https://al-maktaba.org/book/9783/383 [²] á‹¨á‰°áˆˆá‹Ťá‹Š የታሪክ ተመራማሪዎች እና ጸሐፊዎች ሾለ ሙሴ የውልደት ዘመን ላይ የተለያየ አስተያየቶችን ሰንዝረዋል። በአማካይ ከወሰድነው ሙሴ እና ወንድሙ አሮን የተወለዱት 1400-1500  ዓ.ዓ ገደማ እንደሆነ አብዛኞቹ ምሁራን ይስማሙበታል(Seder Olam Rabbah,Jerome’s Chronicon (4th century) gives 1592 for the birth of Moses,The 17th-century Ussher chronologycalculates 1571 BC (Annals of the World, 1658 paragraph 164) [Âł] The gospel of the birth of Mary, 1:1-2, Gambero, Luigi (1999). Mary and the Fathers of the Church: The Blessed Virgin Mary in Patristic Thought. Ignatius Press.ISBN 978-0-89870-686-4. [⁴] https://quran.al-islam.com/Page.aspx?pageid=221&BookID=11&Page=1 [⁾] The Gospel of Pseudo-Matthew Chapter 20 [⁜] Protoevangelium of James Gospel

ማርያም የሐሩን እህት? Read More »

የመስዋዕቱ ልጅ ኢስሐቅ ወይስ ኢስማኢል?

ኢድ አል አድሃ(عيد الأضحى) ኢድ(عيد) ማለት በአል፣ ድግስ ወይም ለመታሰቢያነት የሚከበር ነገር ማለት ሲሆን áŠ á‹ľáˆƒ (أضحى) ወይም ቁርበን (قربان) ወይም ደግሞ የእብራይስጡ አቻ ቃል ቆርባን(קׇרְבָּן) ማለት “መስዋዕት/መባ” ማለት ነው። ኢድ አል አድሃ ሁለተኛው የሙስሊም ወገኖቻችን ክብረ በአል ነው። በዚህም ክብረ በአል ሙስሊም ወገኖቻችን ለመስዋዕትነት የሚሆነውን የበግ፣ የግመል፣ የፍየል ወየም የጠቦትን…ወዘተ የመሳሰሉትን የእንስሳትን ደምን ያፈሳሉ። የበአሉ እርሾ ወይም ጅማሮ በቁርአን ውስጥ የኢብራሂም(ዐሰ) ልጁን ለአምላኩ ለመሰዋት የታዘዘበትን ቀን ለማሰብ ሲባል የሚከበር በአል ነው። በቁርአን ላይ አላህ በሱረቱ አልሷፍፋት (የተሰላፊዎቹ ምዕራፍ) ላይ ሾለ ተሰላፊዎች እምነት በሚናገርበት ክፍል በቁጥር 83 ላይ ከአማኞች መካከል የሆነው ኢብራሂም (ዐሰ) አንደኛው እንደሆነ ይናገራል። በዛው ክፍል በቁጥር 100 ላይ ደግሞ ኢብራሂም (ዐሰ) አንድን ጸሎትን ሲጸልይ እንመለከታለን፦ As-Saffat 37:100ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡(رَبِّ هَبْ لِى مِنَ ٱلصَّلِحِينَ) የኢብራሂምም አምላክም ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም ባሪያውን አበሰረው። ኢብራሂም (ዐሰ) ከባዱ ፈተና የሚጀምረው በቁጥር 102 ላይ ነው። አምላኩ የሰጠው ልጅ ለሾል በደረሰ ጊዜ ኢብራሂም (ዐሰ) በራዕይ አንድ ልጁን እንደሚያርድ ሁኖ ያልማል። እርሱም ለልጁ ሾለ ራዕዩ ምን እንደሚያስብ በጠየቀው ጊዜ “የታዘዝከውን ሼል” ብሎ ሲፈቅድለት እንመለከታለን። አሁን ዋናው ጉዳይና ጥያቄ ያ ለኢብራሂም (ዐሰ) የተበሰረው የመስዋዕቱ ልጅ ማነው? የሚለው ንግርት ነው! የዘመናችን የሙስሊም ኡስታዞች ሽንጣቸውን ገትረው በመከራከር በቁርአኑ ላይ የመስዋዕቱ ልጅ ኢስማኢል  ለማስመሰል የቁርአኑን አያህ የማይቀባቡት ነገር የለም። ከሁሉም በላይ ደግሞ አጃኢብ የሚያስብለው ጥርት እና ጥንፍፍ ብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተነገረለትን የቃል ኪዳን ልጅ ይስሐቅን በእስማኤል ተክተውና አንሻፈው የመስዋዕቱ ልጅ እስማኤል እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል ማለታቸው ነው። “..የያዙት ነገር..” እንደሚሉት አበው በእኛ ዘንድ የሙስሊም ኡስታዞች መካከል ይሄንን ዜማ መስማቱ የተለመደ ነው። ሲጀመር ኡስታዞቹ የማይሆን የማይሆን የሙግት ነጥቦቻቸውን እየሰካኩ ለሙስሊሙ ተደራሲያን እየፈተፈቱ ሲያጎርሷቸው እኛንም (የክርስቲያኑን ማህበረሰብ) ለማታለል መጣጣራቸው ሳስብ ይገርመኛል። ለማንኛውም የኡስታዞቻቸውን ድርሳነ ባልቴት ወይም የአሮጊቶች ተረት የሆነውን የሙግት ሐሳባትን በሁለት ጎራዎች ከፍለን ሾለ መስዋዕቱ ልጅ ማንነት እንመለከታለን፦ የቁርአናዊ ሙግት በመጀመሪያ ኢስማኢል ነብይ መሆኑ ለመስዋዕትነት የተዘጋጀው ልጅ እርሱ ነው የሚያስብለን አንድምታ የለም። ምክንያቱም እንዲሁ ኢስሐቅም ነብይ መሆኑን ቁርአናቸው ይነግረናል(Al-‘Ankabut 29:27)።[1] ስለዚህ ሾለ ኢስማኢል ነብይነት መጥቀስና ማጠቃቀስ ጉንጭ ማልፋት ካልሆነ በስተቀር ለሙግቱ እንብዛም ውጤት የለውም። ለማንኛውም ኡስታዞቹ ያነሷቸውን ዋና ዋና ነጥቦችን እንመለከታቸዋለን። ቀጠሮ አክባሪው የዘመናችን የሙስሊም አቃብያነ እምነት ነን የሚሉት በሱረቱ መርየም 54 ላይ የተጠቀሰውን ክፍል ከሱረቱ አልሷፍፋት 102 ጋር በማጣመር የተሳሳተ ምስስሎሽን (wrong analogy) በመፍጠር ለመስዋዕትነት የቀረበው ኢስማኢል መሆኑን ለማሳየት ሞክረዋል። ነገር ግን በክፍሉ ላይ አውዳዊ ምልከታ ስናደርግ ሙግታቸው የሚያስኬድ ሁኖ አናገኘውም፦ Maryam 19:54በመጽሐፉ ኢስማዒልንም አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡(وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ إِسْمَٰعِيلَۚ إِنَّهُۥ كَانَ صَادِقَ ٱلْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا ) በዚህ ክፍል ላይ አላህ የኢብራሂምን ልጅ ኢስማኢልን ሲያመሰግነው እንመለከታለን። ኢስማኢል የአረቦች ሁሉ አባት ነበር። በተጨማሪም እርሱ ለቃለ ማሐላው እውነተኛና ታማኝ እንደነበር የሙስሊም ሊቃውንት ይናገራሉ።[2] የክፍሉን አውደ ሕታቴ ለመረዳት ቁጥር 55ን መመልከቱ አስፈላጊ ነው፦ Maryam 19:55ቤተሰቦቹንም በሶላትና በዘካ ያዝ ነበር፡፡ እጌታውም ዘንድ ተወዳጅ ነበር፡፡(وَكَانَ يَأْمُرُ أَهْلَهُۥ بِٱلصَّلَوٰةِ وَٱلزَّكَوٰةِ وَكَانَ عِندَ رَبِّهِۦ مَرْضِيًّا ) ኢስማኢል በጌታው ዘንድ ተወዳጅ የሆነበትና ከላይ ደግሞ አላህ ኢስማኢልን እንዲያስቡ ለምእመናን ሲናገር በኢስማኢል የግብር ጉዳይ ረገድ መሆኑ ግልጽ ነው። ኢስማኢል ለአላህ ለሆኑ ስራዎች ላይ ታማኝና አክባሪ ነብይ መሆኑን ከክፍሉ አውድ መረዳት እንችላለን። እንደውም የእንግሊዘኛው ትርጉም ቁጥር 54ን የሚገልጸው “he was true to his promise” ለቃለ መሐላው እውነተኛ ወይም ታማኝ እንደሆነ በሚያሳይ መልኩ ነው። And mention in the Book, Ishmael. Indeed, he was true to his promise, and he was a messenger and a prophet./English – Sahih International (Maryam 19:54)/ በተጨማሪም ኢብን ጁረይጅ ሾለ ኢስማኢል ሲናገሩ፦ “He did not make any promise to his Lord, except that he fulfilled it./የሚፈጽመውን ካልሆነ በቀር ኢስማኢል ምንም አይነት ቃለ መሐላ ለጌታው አይገባም “Ibn Jurayj ስለዚህ ኢስማኢል ለቃለ መሐላው እውነተኛ፣ ታማኝና አክባሪ መሆኑን የሱረቱ መርየም ቁጥር 54 አውዳዊ አንድምታው ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ቀጠሮ ከሚለው ፍታቴ ይልቅ ቃለ መሐላ ወይም ቃልኪዳን(promise) እንደሆነ የክፍሉ ዙሪያ ገባ ይነግረናል። “ቀጠሮውን አክባሪ” የሚለው ኃይለቃል በተጨማሪም የማያስኬደው በመጀመሪያ አላህ በሱረቱ አልሷፍፋት 102 ላይ ራዕይን ያሳየው ለኢብራሂም (ዐሰ) እንጂ ለልጆቹ ለኢስሐቅ ወይም ለኢስማኢል ፈጽሞ አይደለም። فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰۚ قَالَ يَٰأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّبِرِينَ ከእርሱ ጋርም ለሼል በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?Âť አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ በተጨማሪም አላህ የመስዋዕቱን ቀጠሮ የሰጠው ለአባቱ ለኢብራሒም(ዐሰ) እንጂ ለልጁ አልነበረም። ምክንያቱም የራዕዩና የትእዛዙ አክባሪ አባቱ እንጂ ልጁ አይደለም። በተጨማሪም በቀጠሮው ቀን ለመሰዋት ልጁን የወሰደው አባትየው እንጂ ልጁ አይደለም። ስለዚህ ለመስዋዕትነት የተቀጠረው ኢስማኢል የቀጠሮው አክባሪ ነበር የሚለው አንድምታ ኪስ ወለድ እንጂ አውዳዊ አለመሆኑን ለመረዳት አያዳግትም። የኢብራሒም ጸሎት ሌላው የሙግት ነጥብ ብለው የሚያቀርቡት ደግሞ “ኢስማኢል/إِسْمَٰعِيْل”  ማለት “አምላክ ይሰማል” ማለት ስለሆነ ኢብራሒም ደግሞ በቁጥር 100 ላይ ወደ አላህ በጸለየው መሰረት ልጅን ሰጠው የሚል ነበር። ነገር ግን ከአውዱ ተነስተን ስንመለከት አላህ ለኢብራሒም በጸሎቱ መሰረት የተሰጠው ልጅ ኢስሐቅ እንጂ ኢስማኢል እንዳልሆነ እንረዳለን። ሲጀመር ኢስሐቅ(إسحاق) ወይም በእብራይስጥ ይሽሐቅ(יִשְׂחָק) ደስታ፣ ሳቅ ወይም ብስራት ማለት ነው። በቁጥር 100 ላይ ነብዩ ኢብራሂም(ዐሰ) ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ(رَبِّ هَبْ لِى مِنَ ٱلصَّلِحِينَ) ብሎ ከጸለየ በኋላ፤ በቁጥር 101 ላይ ጌታውም ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው (فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍ) ብሎ ሲናገር እንመለከታለን። አስተውሉ! የጌታው መልስ ላይ “አበሰርነው” የሚለውን ቃል ከኢስሐቅ ጋር እንጂ ከኢስማኢል የስም ትርጉም ጋር ፈጽሞ የሚገናኝ አይደለም። እንደውም ሾለ ልጁ ማንነት በዛው ሹል በቁጥር 112 ላይ ግልጽ አድርጎ የብስራቱ ልጅ ኢስሐቅ እንደሆነ ይነግረናል በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን(وَبَشَّرْنَٰهُ بِإِسْحَٰقَ نَبِيًّا مِّنَ ٱلصَّلِحِينَ)በተጨማሪ በሱረቱ ሁድ 11፡69-71 ያለውን ክፍል ስንመለከት በቁጥር 101 ላይ ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው የሚለው ንግግር ለኢስሐቅ መሆኑን ግልጽ የሚያደርግ ክፍል ነው። 11:69 – መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በ(ልጅ) ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፡፡11:70 – እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከነሱም ፍርሃት ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት፡፡11:71 – ሚስቱም የቆመች ስትኾን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም፡፡ በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)፡፡ ከኢስሐቅ ሌላ አካል በዚህኛው የሙግት ሐሳብ ላይ ደግሞበቁጥር 112 በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን በሚለው ክፍል ላይ በኢስሐቅም ስለሚል “-ም” የምትለው ጥገኛ ምእላድ ከኢስሐቅ ተጨማሪ ሌላ አካል እንዳለ ያመለክታል የሚል ሙግት ነው። ነገር ግን ይሄ ሐሳብ ፈጽሞ የሚያስኬድ አይደለም። አብዱሉ በክፍሉ ላይ ሁለት ልጅ የተባሉ አካላት እንዳሉ ይናገራል። የመጀመሪያው ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም ሲሆን ሁለተኛው በኢሥሐቅ ብሎ ከፋፍሎ እንመለከታለን። እንደዛ ከሆነ የሙግቱ ሃሳብ አጠያያቂ ይሆናል። ምክንያቱም በእርሱ ሎጂክ ከሄድን በቁጥር 101 ላይ አላህ ለኢብራሒም ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው (فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍ ) በሚለው አንቀጽ ላይ ወጣት ልጅም በሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት “-ም” የምትለው ምእላድ አሁንም በእነርሱ ሎጂክ ኢስማኢል ነው ብለው ከሚያምኑት አካል ሌላ ከእርሱ

የመስዋዕቱ ልጅ ኢስሐቅ ወይስ ኢስማኢል? Read More »

መሬትን ተሸካሚው ፍጡር  (“አል-ኑን/النون”)

በእስልምናው አስተምህሮት ውስጥ አፈታሪካዊ እና ተረታዊ ከሆኑት ታሪኮች መካከል አንደኛው ግዙፉ እስላማዊው አሳ ነባሪ ( الحوت الإسلامي ፣ አል-ሁት አል-ኢስላሚ) ይሄም ፍጡር ምድርን በጀርባው እንደሚሸከም የተገለጸለት  አፈታሪካዊው ፍጡር ነው፡፡ ታዳ  ይሄ እስላማዊው አውሬ/አሳነባሪ(አል-ሁት/ٱلْحُوتِ) በቁርአን ላይ “ምድር ተሸካሚ አሳ” ወይም “አል-ኑን/النون” ተብሎ ተጠርቷል። ቁርአኑ ስለዚህ ፍጡር ግልጽ በሆነ ሁኔታ አላስቀመጠልንም። በዚህም ምክንያት በአንዳንድ የሙስሊም ሊቃውንቶች መካከል እስካሁኑ ሰአት ድረስ ያልተፈታ ትልቅ ንትርክን የፈጠረ ለዘመናዊው ሳይንስ ጥናቶች እንግዳና አጠያያቂ የሆነ ጉዳይ ነው። እኔም ስለዚህ ፍጡር ጉዳይ በስፋት በመመልከት አንዳንድ እስላማዊ ጽሁፎችን ማለትም ሐዲሳትን እና የተለዩ ተፍሲራትን እያገላበጥን ለማሳየት ቀርቤያለሁ። ➙ ከላይ በጨረፍታ ለመመልከት እደሞከርነው “አል-ኑን/النون” በውሀ ውስጥ ከሚኖሩ የአሳ ዝርያዎች መካከል አንዱ ነው። በቁርአን በሱረቱል አል-ቀለመ በአንደኛው አያት ላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን። ይሄንን አያት በእስልምናው ማህበረሰብ ውስጥ እጅጉን እውቅና ካላቸው የቁርአን ተፍሲሮች (ኢብን-ከሲር፣ አል-ቁርጡቢ፣ ጃለለይን እና አት-ጠበሪ) እንደሚያስረዱን ከሆነ “ኑን” የሚባለው ግዙፍ አሳ ነባሪ እንደሆነና ምድርን የተሸከመ ፍጡር እንደሆነ ይነግሩናል። አል-ቀለም 68:1نٓۚ وَٱلْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَነ.( #ኑን)፤ በብርእ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት፡፡ ኢብን ከሲር አል-ቀለም 68:1 ተፍሲር፦ታላቁ ሙፈሲር ኢብን ከሲር በተፍሲሩ ላይ ሾለ ኑን ሲናገር፦ አላህ ‹ ኑን› የተባለውን ከፈጠረ በኋላ ምድር በኑን ጀርባ ላይ እንደዘረጋ ይናገራል፡፡ ከዛም ተረቱ ይቀጥላል #ኑን የሚባለው ፍጡር ደነበረ ወይም ተረበሸ ይለናል። በዚህ መሀል ምድር ማረግረግ ወይም መንቀጥቀጥ ጀመረች። አላህ ለዚህ ችግር ሲል ተራሮችን ፈጠረ። እነዚህም ተራሮች ምድር እንዳትነቃነቅ እንደ ችካል ቸከላቸው ይለናል። እንደውም በቁርአን 78:7 ላይ “…ጋራዎችንም(ተራሮችን) ችካሎች አላደረግንምን(وَٱلۡجِبَالَ أَوۡتَادًا)?)…”  አላህ ተራሮችን የቸከላቸው የመሬትን መንቀጥቀጥ ለማስተካከል እንደሆነ ተፍሲራት ይነግሩናል(ጃላለይን, ኢብን ከሲር ተፍሲር)። ምን ይሄ ብቻ አሁም አፈታሪካዊ ተረቱ አላበቃም አል ባግሃዊ እና ሌሎች የሙስሊም ሙህራኖች እንደተናገሩት በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ ሰባቱ መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል ብለው ያስባሉ። እስቲ ይሄን ታሪክ ከኢማም ኢብን ከሲር ተፍሲር በተወሰነ መልኩ እንመልከት፦ “…ከዚያም አላህ ‹ኑን› የተባለውን ከፈጠረ በኋላ ሰማይ የተፈጠረበት ጭስ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ከዚያም ምድር በኑን ጀርባ ላይ ተዘረጋች፡፡ ከዚያም ኑን ስለደነበረ ምድር ማረግረግ ጀመረች፤ ነገር ግን (አላህ) ምድርን እንዳትንቀሳቀስ አድርጎ በተራሮች ቸከላት… “ኢብን አቡ ኑጃኢህ እንደተናገረው ኢብን አቡ በኪር በሙጃሂድ እንዲህ ተብሎ ተነግሮት ነበር፣ “ኑን ከሰባቱ መሬቶች በታች የሚገኝ ታላቁ አሣ እንደሆነ ይነገራል፡፡” በተጨማሪም አል ባግሃዊ (አላህ ነፍሱን ያሳርፋትና) እንዲሁም ሌሎች ሐታቾች እንደተናገሩት በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ ሰባቱ መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል፡፡…”[1] ኑን ለሚለው ቃል ትርጓሜ ሲያስቀምጥ ደግሞ “…ኑን የሚባለው ትልቅ አሳነባሪ ነው(Nun is a big whale/نۤ حوت عظيم)…” በማለት ኢብን ከሲር ትንታኔውን አስቀምጧል።[2] አል-ቁርጡቢ ተፍሲር 68:1 Ů†Ű¤> الحوت الذي ŘŞŘ­ŘŞ الأرض السابعة>”…<ኑን>ከሰባተኛው(السابعة) መሬት(الأرض) በታች(ŘŞŘ­ŘŞ) የሚገኘው አሳ ነባሪ(الحوت) ነው….”[3] በአል-ቁርጡቢ ተፍሲር መሰረት ” ኑን” የሚባለው ከሰባተኛው  መሬት በታች የሚገኝ አሳ ነባሪ እንደሆነ ይነግረናል። ልብ በሉ “…ከሰባተኛው(السابعة)…” ሰባት ምድር እንዳለም ከላይ በኢብን ከሲር ተፍሲር ላይ ተመልክተናል። እነርሱም ተደራራቢ እንደሆኑ “ታሐት(ŘŞŘ­ŘŞ)” ወይም “ከታች/ከስር” የሚለው ቃል ያስረዳናል። ተፍሲር አት-ጠበሪ 68:1አት-ጠበሪ በሱረቱል አል-ቀለም 68:1 ላይ ማብራሪያ ሲያስቀምጥ እንዲህ ብሏል፦“…هو الحوت الذي عليه الأرَضُون…”“…ሰባቱ ምድሮች የተቀመጡበት ፍጡር አሳ ነባሪ(الحوت) ነው…”[4] በእስልምናው ኮስሞሎጂ መሰረት አላህ ሰባት ሰማያትን እንደፈጠረ ሁሉ ሰባት ምድሮችንም ፈጥሯል(Quran 65:12)። እነዚህም ጠፍጣፋ ምድሮች በአሳ ነባሪው ላይ ተደራርበው ተቀምጠው እንደሚገኙ ጥንታዊ የሙስሊም ሊቃውቶች ይነግሩናል። ተፍሲር አል-ከቢር(አር-ረዚ)/tefsir Al kabir(by Ar-Razi)፦ “…بالحوت الذي على ظهره الأرض وهو في بحع ŘŞŘ­ŘŞ الأرض السفلى…” በዚህም ተፍሲር ላይ በጀርባው ምድር የሚሸከመው ዓሳ ነባሪ እንደሆነና አል-ከቢር እዚህ ዓሳ ነባሪ ጀርባ ላይ ሚዛናዊ የሆኑ ጠፍጣፋ መሬቶች እንዳሉ  ይነግረናል፡፡[5] ተፍሲር አል-ቃዲር/Tafsir Al-Qadir (by Shawkani) ተፍሲር አል-ቃዲር/Tafsir Al-Qadir (by Shawkani) ይህ ተፍሲር ከ 18 ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ዓለም ዓሳ ነባሪ ጀርባ ላይ ተሸክሟል የሚል ሀሳብን በመደገፍ ያረጋግጣል። “….ምድርን የተሸከመው ፍጡር አሳ ነባሪ/الحوت ነው…..”/Fath Al-Qadir on 68:1__[6] ሐዲስ ከኢብን አባስ (ቱርጁማን ኡል-ቁርአን/ترجمان القرآن)(ሐዲስ ከአት-ጠበሪ) ኢብን አባስ እንደተናገረው፦አላህ የፈጠረው የመጀመሪያ ነገር ብእርን  ስለነበረ “ጻፍ!” አለው፡፡ እናም እስከ ሰዓቱ (የፍርድ ቀን) ድረስ ምን እንደሚሆን ጽፏል፤ ከዚያም ኑንን ከውሃ በላይ ፈጠረ ከዚያም ምድርን በእርሱም ላይ ተጫነች፡፡(ታሪኽ አት-ታባሪ) [7] ይህም ሀዲስ(ትረካ) በሀዲሳት ሰንሰለት  ትክክለኛ(ሰሒህ/صحيح) ትረካ ተደርጎ ተቆጥሯል፡፡[7] መሐመድ ለኢብን አባስ ዱዓ (ጸሎት) ስላደረገ አላህም የቁርአንን ትክክለኛ አተረጓጎም ያስተምረው ነበር፡፡እንዲሁም ኢብን አባስ (ቱርጁማን ኡል-ቁርአን/ترجمان القرآن) “የቁርአን ተርጓሚ” ተብሎ ተጠርቷል ፣ ምክንያቱም ሾለ ራእዮች ትርጓሜ (ቃል በቃል መተርጎም) የሚሰጥና ጥልቅ ዕውቀት ያለው ሰው ነበር። ኢብኑ ዐባስ (ራአ) እንደተናገሩት፦ነቢዩ (ሜ.ዐ.ወ) አቅፈውኝ “አሏህ ሆይ! የመጽሐፉን (ቁርአን) እውቀት አስተምሩት ፡፡ ”(ሳሂህ ቡኻሪ 9:92:375) ታድያ ይህ በቁርአን ጥልቅ እውቀት ያለው አሊም ተራራዎቹ በቁርአን ውስጥ እንደ ችካል እንዴት እንደተደረጉ የእርሱ ትረካ ያስረዳል፡፡ ምክንያቱም በባህላዊው እስላማዊ የኮስሞሎጂ መሠረት ምድር ከዓሣ ነባሪው ጀርባ ላይ ትነቃነቅ (ትንቀጠቀጥ) ስለነበረ አላህ ምድርን ዓሣ ነባሪው ላይ ተረጋግታ እንድትቀመጥ ተራሮችን እንደ ችካል እንዳደረጋቸው በግልጽ ሁኔታ ተርኮልናል፡፡ በመጨረሻም ከዚህ ሁሉ መረጃዎችና ማስረጃዎች የምንረዳው ነገር ቢኖር አላህ ሰባት መሬቶችን ፈጥሮ በአሳ ነባሪው(“አል-ኑን/النون” ) ጀርባ ላይ ደራረቦ በማስቀመጥ ከዛም አሳ ነባሪው(“አል-ኑን/النون” ) ሲደነብር መሬት እዳትነቃነቅ በተራሮች በመቸከል እንድትረጋጋ አድርጓል። ይባስ ብሎም በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ ሰባቱ መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል ብለው በማሰብ ይህ ለሳይንስና ለእውነታ ሆድና ጀርባ የሆነን ነገር ከአንዳንድ የመሰለኝን ልናደርግ ከሚሉ ፈላስፋዎች ቀጥታም ሆነ ተጨማምሮበት የተቀዳ አፈታሪክን የአምላክ መገለጥ ነው ብሎ መቀበል በጣም ሞኝነት ነው። አንዳንድ የዘመኔ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ስኮላሮችና ዳኢዎች ይሄ ነገር አልዋጥ ሲላቸው የውሸት የትረካ ሰነድ ወይም አምላካዊ ንግግር የሆነ ሀሳብ አይደለም ይሉናል።[8] ነገር ግን አይኑ የፈጠጠ በድሮ ዘመን በነበሩት የእስልምና ሊቃውንቶች መካከል ተቀባይነትን ያተረፈ ታሪክ እንደሆነ ከተፍሲራትና ከሐዲስ ለመመልከት ችለናል። ይሄን የመሰለ ተረትና አፈታሪክ ታቅፈው ነው እነ ዶክተር ዛኪር ናይክና ቢጤዎቹ ቁርአን ከሳይንስ ጋር አይጣረስም የሚሉን። በመሰናበቻዬም አንድ ነገር ተናግሬ ልደምድም፦ እውነት ቁርአን የፈጣሪ ንግግር ነውን? ከሆነስ ለምን ከሐቅና ከሳይንስ ጋር ላይስማማ ሊጣረስ ቻለ? እውነትን ፈልጉ እውነትም አርነት ያወጣችኋል። ማጣቀሻዎችና ማስፈንጠሪያዎች [1] Tafseer Ibn Katheer;Online Edition: http://quran.al-islam.com/Tafseer/DispTafsser.asp?l=arb&taf=KATHEER&nType=1&nSora=68&nAya=1 [2] https://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=0&tTafsirNo=7&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1 [3] https://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=1&tTafsirNo=5&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1 [4]  https://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=1&tTafsirNo=1&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1 [5]  https://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=1&tTafsirNo=4&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1 [6] https://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=1&tTafsirNo=9&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1 [7]  https://hdith.com/?s=%D8%AB%D9%85+%D8%AE%D9%84%D9%82+%D8%A7%D9%84%D9%86%D9%88%D9%86+%D9%81%D9%88%D9%82+%D8%A7%D9%84%D9%85%D8%A7%D8%A1%D8%8C+%D8%AB%D9%85+%D9%83%D8%A8%D8%B3+%D8%A7%D9%84%D8%A3%D8%B1%D8%B6+%D8%B9%D9%84%D9%8A%D9%87 [8]  https://islamqa.info/en/114861

መሬትን ተሸካሚው ፍጡር  (“አል-ኑን/النون”) Read More Âť

ሥነ አመክንዮአዊ ተቃርኖ በመጽሐፍ ቅዱስ አይሳሳቴነት – ክፍል 2

ለዘብተኛ ምሑራን ሆኑ ከክርስትና ውጪ ባሉ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ህጸጽ አልቦነትን በዚህ መልኩ ሲቃወሙ እናያለን፦መንደርደሪያ አንድ፦ በእጆቻችን ላይ ህጸጽ አልቦ የሆኑ እደ ክታባት የሉንምመንደርደሪያ ሁለት፦ እደ ክታባት ቅዱሳት መጻሕፍት ናቸው[š]ስለዚህ: መጽሐፍ ቅዱስ ህጸጽ አልባ አፊዎተ ቃለ እግዚአብሔር አይደለም።(ማሳሰቢያ የሁለተኛው አዋጅ አጽዕኖት ከክርስቲያናዊ እደ ክታባት ያፈነገጠ ተደርጎ እንዳይታሰብ) በመጀመሪያ ይሄን ሙግት ርዕቱ ነው ወይስ አይደለም? ከማለታችን በፊት ህጸጽ አልቦነትን(inerrancy) ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት። ህጸጽ አልቦነትን ማለት ከስህተት የጸዳ እውነት አዘል አልያም ዝንፈተ እውነት የሌለበት ማለት ነው። አንዳንዶች የመጽሐፍ ቅዱስን ህጸጽ አልቦ አፊዎተ ቃለ እግዚአብሔርነቱ ላይ ሒስ ለማቅረብ ሲሉ ሁለት መሰረታዊ ነባቤ ቃላትን እርስ በእርሳቸው ያጠረማምሳሉ(ለምሳሌ የኤቲስቱ ባርት ኧርማን ሙግት)፤ ይኸውም የቃል በቃል አጠባበቅ እና ህጸጽ አልቦነትን ነው። ሁለቱ መሠረታዊ ልዩነቶች ያሏቸው ሲሆኑ የአንድ ነገር ንግግር ወይም ጽሑፍ የቃል በቃል አጠባበቅ ላይ ችግር ማግኘታችን ህጸጽ አልቦነቱን ላያሳጣው ይችላል። ባጭሩ የዚህ ሙግት ችግር የመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ግልጠት ማለታችን በእደ ክታቦቹ የቃል በቃል መስማማት አለባቸው ከሚለው ቅድመ ግንዛቤ ላይ የተመረኮዘ አለመሆኑን ካለመረዳት አንጻር ሊታይ ይችላል። ለምሳሌ ያክል የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ በሁለት የግሪክ ቃላት ብቻ ልዩነት የተፈጠረ አንድ የሚስተዋል ልዩ ምንባባት አሉ፦ እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤ሮሜ 5፥1 አንዳንድ እደ ክታባት ሰላምን እንያዝ የሚለውን ሐረግ ሲያካትቱ አንዳዶቹ ደግሞ ሰላም አለን የሚልን ነባቤ ሐረግ ይጠቀማሉ(አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚሁ መልክ ሲጠቀም ይታያል)። የግሪኩ ቃል አንዱ ኤኾሜን በኦሜጋ ፊደል(ἔχωμεν) ሲጠቀም ሌላኛው ደግሞ ኤኾሜን በኦሚክሮን ፊደል (ἔχὸμεν) ይጠቀማል። ምንም እንኳን እንደዚህ አይነት የቃላት ልዩነት ቢኖርም የአረፍተ ነገሩ ዋና ሐተታዊ እውነታው የሚደበዝዝ ወይም ሊናድ አይችልም። የአረፍተ ነገሩ ትክክለኛው አቀማመጥ፦ “peace is the possession of those who have been justified” እስከሆነ ድረስ የክታቡን ህጸጽ አልቦነት በቃላት ቦታ መለዋወጥ ሆነ አለመመሳሰል ልናጣው በፍጹም አንችልም። ምክንያቱም ህጸጽ አልቦነት የሚገናኘው ከትክክለኛ ዓርፍተ ሐሳቦ ጋር ነው። ነገር ግን አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር አንዳንድ የእደ ክታባቱ ልዩ መሆን(texual variant) ችግር ሆነው የሚመጡበት ጊዜ ሆነው የሚመጡበት ሰዓት ሊኖር ይችላል። ይሄን መሠል ችግሮች አገኘን ማለት ግን እንደነዚህ አይነቱን ለመለየት አስቸጋሪ አይደለም እንደውም በቀላሉ የሚለዩ ናቸው። ሙስሊሞችም ሆኑ ለዘብተኛ ምሑራን የሚጠቅሷቸው ነጠሮች በአጥባቄው ምሑራኑ ዓለም ውስጥ መልስ ተሰጥቷቸው ያለፉ ናቸው። በምሳሌም እውቁ የምንባባዌ(ጽሑፋዊ) ሕያሴ ስኮላር ዋላስ 99 በመቶ በላይ የሚሆኑት በእነርሱ መካከል ልዩ ምንባባት እንደሌሉ ይናገራሉ። Matthew Barrett በመጽሐፉ እንዲህ ሲል ያስቀምጠዋል፦ “….textual variations in the copies do not imply that the original manuscripts contained errors. These variations are seen as part of the natural process of transmission over time, but they do not undermine the truthfulness of Scripture as it was originally given. the existence of textual variants should not shake one’s confidence in the inerrancy of the Bible, as the original text remains reliable and intact, even if minor discrepancies exist in the copies..” በዚህ መሠረት ደግሞ በመጀመሪያው ጽሑፍ መካከል ልዩነት አለና በኋላ ላይ ባሉት ኮፒዎች ልዩነት አለ በሚሉ ሰዎች ሙግት ልዩነቶቹ በራሷቸው የእግዚአብሔር ቃል ህጸጽ አልቦ መሆኑን ሊሸፍኑ አንዳች አይቻላቸውም በማለት ክታባቱን ያጠኑ ምሑራን በዚህ መልክ ያስቀምጡታል ማለት ነው። ማጣቀሻ Barrett, Matthew. God’s Word Alone: The Authority of Scripture. Zondervan, 2016

ሥነ አመክንዮአዊ ተቃርኖ በመጽሐፍ ቅዱስ አይሳሳቴነት – ክፍል 2 Read More Âť

መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እና ሕጸጽ አልቦ

ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ።2ኛ ጢሞ 3፥16 (አዲሱ መ.ት) መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ለክርስትና እምነተ መርሕ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የማይሳሳትና ሊሳሳት የማይችል ባለሥልጣን እንዳለው የሚገልጽ ክርስቲያናዊ መርሕ ነው። ይሄንን ሐሳብ ብርሐነ አለም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈሳዊ ልጁ ለጢሞቴዎስ በጻፈለት መልዕክት ላይ ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ እስትንፋሰ እግዚአብሔር (ቴዎኔዩስቶስ/θεόπνευστος) መሆናቸውን ሲነግረው እንመለከታለን። በዚህም መሠረት ቅዱሳት መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔር አፊዎተ እግዚእ ማለትም በቀጥታ መለኮታዊ ግልጠት መሆናቸውን እና ከዚህም የተነሳ እውነተኛ እና ሕጸጽ አልቦ ናቸው ብለን እናምናለን። የቤተ ክርስቲያን አበው ይህንኑ ሐሳብ ሲደግፉ ይስተዋላል። የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ(John Chrysostom) ክፍሉን በድርሳኑ ላይ ሲያብራራ ቅዱሳት መጻሕፍት አፊዎተ እግዚእ መሆናቸውን እና ለአማኞች ትክክለኛ የቅድስና እና የህይወት መንገድ መሮች መሆናቸውን ይናገራል።[1] ቅዱስ ሔሬኔዎስ ዘሊዮን በመድፍነ መናፍቃን መጽሐፉ ላይ ቅዱሳን መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔር እና የበላይ ባለስልጣን መሆናቸውን በመግለፅ እውነተኛው የክርስትና አስተምህሮ መሠረት የሆኑ  እና ሐሰተኛውን አስተምህሮ የምንከላከልባቸውም (የምንመክትባቸው) ጭምር እንደሆኑ ይገልጻል (Against Heresies)።  ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር እስትንፋስ በመሆናቸው ስለ እውነት ፤ ክርስትያናዊ የሕይወት መርህ እና ድነት አስፈላጊ የሆኑትን ሥነመለኮታዊ አስተምህሮ ሁሉ በውስጡ ያካተቱ በመሆናቸው ለዚህም አስተምህሮ ብቁ ባህሪዎት እንዳላቸው እንመለከታለን። ቅዱስ አትናቴዎስ (Athanasius of Alexandria) በክታቡ እንዲህ ሲል ይናገራል፦ The Holy Scriptures, given by inspiration of God, are of themselves sufficient toward the discovery of truth.[2] ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ለክርስቲያን ሥነመለኮት ብቁ ነው ስንል በራሱ ትውፊትን የሚያገልል ወይም የሚቃወም ተደርጎ በፍጹም መታሰብ የለበትም። ይሄ አስተምህሮ ግን ማለትም የመፅሐፍ ቅዱስን በቂነት(Material Sufficiency) ልጅ የጥንት ማህበረሰብ ስምምነት(ኮንሴንሰስ ፓትረም) ያለው እምነት መሆኑ ፕሮቴስታንት በዚህ ላይ ጽኑ መሠረት እንዳለው እናውቃለን። ይሄ አስተምህሮ ግን ለትውፊት, ለአምልኮ ሥርዓት ሆኑ ለጉባኤያት አስተምህሮ እና እውነተኝነት ትክክለኛው መመዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን የሚናገርም ነው። በተጨማሪም ሁሉም ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሚለው ለመጽሐፍ ቅዱስ መገዛት እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ህብረት መፍጠር እንዳለባቸው የሚያመላክትም ጭምር ነው። ምክንያቱም ትውፊት, የአምልኮተ ሥርዓት ሆኑ, ጉባኤዎች የማይሳሳቱ ስላልሆኑ ማለትም ሊሳሳቱ የሚችሉ በመሆናቸው ምክንያት መመዘን ያለባቸው አይሳሳቴና የእግዚአብሔር እስትንፋስ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህንን ሐሳብ ቅዱስ አውግስጢኖስ ዘሒፖ(Augustine of Hipo) በመደገፍ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ዝንፈተ እውነት የሌለበት እንደሆነ ይናገራል፦ I have learned to yield this respect & honor only to the scripture, of these alone do I most firmly believe that completely inerrant (free from error) [3] ትውፊትም, የአምልኮ ሥርዓቶች ሆኑ ጉባኤያት ስህተት ሊገኝባቸው ይችላል። ምክንያቱም የትውፊት አስተላለፋቸውን በተመለከትን ጊዜ በሰዋዊ አተረጓጎም, በተፈጥሮዋቸው የሚሳሳቱ ስለሆኑ እና በባህል ተጽዕኖ የታሰረ በመሆኑ ትክክለኛው መልዕክቱ ተበላሽቶ(ተቀይሮ) ሊሆን ይችላል። በተለይም ትውፊት እና የሃይማኖት ሥርዓታዊ ድርጊቶች በዘመናት መሐል የተለያየ ብርዘት እና ለውጥ ሊገባባቸው የሚችሉ ናቸው። ለምሳሌ ያክል በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳቱ መብት እያደገ እየተሻሻለ በመምጣት ወደ የፖፑ አለመሳሳት(papal Infallibility) በመጨረሻም ወደ ስህተት መምጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም። በተጨማሪም በነገረ ማሪያም ያላቸውን ዶክትሪን እጅጉን እየለጠጡ በመምጣታቸው ወደ Immaculate conception(አንዳንድ ኦርቶዶሳውያንም ይህንኑ አስተምሮ ይቀበላሉ) እንዳመሩ እንመለከታለን። የፑርጋቶሪ ምልከታ ሌላው የሚጠቀሱ ጉዳዮች ናቸው። በኦርቶዶክሱም ሆነ በካቶሊኩም የሚስተዋለው የመጽሐፍ ቅዱስ የቀኖና ችግር ስንመለከት ትውፊት በዘመናት መካከል ሊቀያየር እና ሊበከል የሚችል ጉዳይ ሁኖ እናገኘዋለን። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በማቴዎስ ወንጌል 15:3 ላይ በመለኮታዊ ግልጠት ላይ ያልተመሠረተውን ያልሆነውን የአይሁዳውያንን ትውፊት ሲመረመር እንመለከታለን። የመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እነዚህ ሁሉ ትውፊት እና ስርዓተ አምልኮ በሕጸጽ አልቦው እና በአይለወጤው በእስትንፋሰ እግዚአብሔር ቃል መሠረት ተመዝነው መጥራት ያለባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን የሚገልጽ ክርስቲያናዊ መርህ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛው ሚዛን እና የሁሉ የበላይ ሊሳሳት የማይችል ባለስልጣን የሆነ ያለው ነው። ማጣቀሻ 1] Homilies on 2 Timothy 2] Against the Heathen, 1:3 3] Letters, 82:3

መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እና ሕጸጽ አልቦ Read More »

አስተምህሮተ ሥላሴ አሕዳዊ ወይስ መድብላዊ?

“እስራኤል ሆይ፥ ስማ፤ አምላካችን እግዚአብሔር  አንድ_እግዚአብሔር ነው፤”  — ዘዳግም 6፥4 ሞኖቴይዝም(monotheism) የሚለው ግሪክ(ጽርዕ) ቃል ከሁለት ቃላት የተዋቀረ ሲሆን ሞኖስ(μόνος) ማለት አንድ ወይም ብቸኛ ማለት ሲሆን ቴዎስ(θεός) ማለት ደግሞ አምላክ ማለት ነው። በአጠቃላይ በስነመለኮት አንጻር አሐዳዊ አስተምህሮት የሚያንጸባርቅ አመለካከት ሞኖቴይዝም (monotheism) ይባላል። ከዚህ በተቃራኒው ደግሞ የመድብለ አማልክት አራማጆች ፖሊቴይዝም(Polytheism) ይባላሉ። ፖሉ(πολύ) ወይም ፖሊ ማለት ብዙ ማለት ነው። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በፖሊቴይዝም ረገድ የሚታወቁ አገራት መካከል ሮማውያንና ግሪካውያን ግምባር ቀደም ነበሩ። ግሪካውያን ለብዙ ነገር አምላክ አላቸው። ለፍቅር፣ ለሰላም፣ ለቀን፣ ለጦር፣ ለወቅቶች፣ ለእድል….ወዘተ ለእያንዳዱ ተግባር አማልክት ነበሯቸው። ከሁሉም በላይ ደግሞ በጣም የሚገርመው የሚያመልኩት ነገር ከመብዛቱ የተነሳ ለማይታወቅ አምላክ በግሪኩ አግኖስቶ ቴዎ(Ἀγνώστῳ θξῡ) ብለው መስዋዕትን ያቀርባሉ[ሐዋ 17:23]። በሐዋርያት ሾል ም.17 ቁ.16-34 ላይ ያለውን ክፍል ስንመለከት ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የግሪክ መዲና በሆነችው በአቴና ሲዘዋወር ያገኘው ነገር ከተማውን የሞሉት የሚታወቁና የማይታወቁ የአማልክት መሰዊያዎችን ነበር። ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በቁጥር 24 ላይ አንድ ወሳኝ ንግግርን በአርዮስፋጎስ አደባባይ ላይ ቆሞ ሾለ ክርስትና አስተምህሮ ሰበከ። “ዓለሙንና በእርሱ ያለውን ሁሉ የፈጠረ አምላክ እርሱ የሰማይና የምድር ጌታ ነውና እጅ በሠራው መቅደስ አይኖርም፤”  — ሐዋርያት 17፥24 “ὁ θεὸς ὁ ποιήσας τὸν κόσμον κι὜ πάντα τὰ ័ν αὐτῷ, οὗτος οὐρινοῌ κι὜ γῆς ὑπάρχων κύριος οὐκ ័ν χειροποιήτοις ναοῖς κατοικεῖ.” (Πραξεις Αποστολων 17:24) በክፍሉ ላይ እርሱ ወይም ሆውቶስ/οὗτος የሚለው በባለቤትነት ሙያ(Nominative case) የመጣው ነጠላ መደብ ተውላጠ ስም እየገለጸ ያለው አምላክ(ቴዎስ/θεὸς) እና ጌታ(ኩርዮስ/κύριος) የሚለውን ስም ነው። ይሄ ደግሞ በክርስትና አስተምህሮት ውስጥ ነጠላ ምንነት ያለው አሐዳዊ አምላክ ወይም ጌታ እንዳለ ያሳያል። እግዚአብሔር አምላክ በምንነት ደረጃ(በስልጣን፣ አገዛዝ፣ በባህሪይ፣ በመፍጠር) አንድ ወይም ነጠላ አምላክ እንደሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በአርዮስፋጎስ አደባባይ ለአቴና ሰዎች አጥብቆ ሲናገር እናስተውላለን። ይሄ ንግግር ደግሞ አስተምህሮተ ክርስትና(ሥላሴያውያን) አሕዳዊ የመለኮት አስተምህሮ(Monotheism) እንዳላቸው የሚያረጋግጥ ነው። በሚገርም ሁኔታ ደግሞ በንጽጽር መልኩ የአቴና ሰዎች መድብላዊ አማልክት (Polytheism) አምላኪዎች እንደሆኑ በቁጥር  23 ላይ ገልጾልን እንመለከታለን፦ “ የምታመልኩትን እየተመለከትሁ ሳልፍ፦ ለማይታወቅ አምላክ የሚል ጽሕፈት ያለበትን መሠዊያ ደግሞ አግኝቼአለሁና፦ እንግዲህ ይህን ሳታውቁ የምታመልኩትን እኔ እነግራችኋለሁ።”  — ሐዋርያት 17፥23 “διερχόμενος γὰρ κι὜ ἀναθεωρῶν τὰ σεβάσματα ὑμῶν εὗρον κι὜ βωμὸν ័ν áž§ ἐπεγέγραπτο· Ἀγνώστῳ θξῡ. ὃ οὖν ἀγνοοῦντες εὐσεβεῖτε, τοῦτο ័γὟ καταγγέλλω ὑμῖν.”(Πραξεις Αποστολων 17:23) የምታመልኩትን ከሚለው አማርኛ ይልቅ የበኩረ ቋንቋው(ግሪኩን) ይበልጡን መመልከቱ ጠቃሚ ነው። ምክንያቱም ” የምታመልኩትን” ብሎ የገባውታ ሴባስማታ ሁሞን(τὰ σεβάσματα ὑμῶν) የሚል የግሪኩ ሐረግ ነው። ሴባስማታ (σεβάσματα) የሚለውን የግሪክ ቃል ነጥለን ስንመለከተው የመጣው በቀጥተኛ ተሳቢ ሙያ(Accusative case) በብዙ ቁጥር አመልካች መደብ(plural form) በግዑዝ ጾታ(Neuter Gender) የገባ ሲሆን በቀጥታ ሲተረጎም የሚመለኩ ነገሮች የሚል ትርጓሜን ይሰጣል። ይህ ማለት ደግሞ ከላይ ለማየት እንደሞከርነው መድብለ አማልክት አምላኪዎች(Polytheists) እንደሚባሉ ተመልክተናል። ስለዚህ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በአቴና የሚገኙት ጣኦት አምላኪ ሰዎች መድብለ አማልክት አምላኪዎች (Polytheists) እንደሆነ እግረ መንገዱን ሲናገራቸው እንመለከታለን። በመጨረሻም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በክርስትናና በግሪካውያን መካከል ያለውን የነገረ መለኮት ልዩነት በግልጽ ሁኔታ አሳይቷል። ደግሞ እኛ ክርስቲያኖች የክርስትናችን አስተምህሮ በሥላሴ እምነተ አምድ ላይ የተመሰረተ ነው። በታሪክም ውስጥ ነብያት በብሉይ ሐዋርያት በአዲስ ኪዳን አስተምረው አልፈዋል። ቤተ ክርስቲያንም ይህን እውነት ተቀብላና አምና ስታስተምረውና ስትጠብቀው ቆይታለች። ሥላሴ የሚለው ቃል በራሱ የእግዚአብሔር የመለኮታዊ መገለጫ ስያሜ ነው። ሥላሴ የግእዝ ቃል ሲሆን ሠለስት ሦስት፤ ሠለሰ ሦስት ሆነ ማለት ሲሆን “ሥላሴ” ማለት ደግሞ ሦስትነት በአንድነት ማለት ነው።ይህም ማለት አንድ ሲሆን ሶስትነትም እንዳለው የሚያመለክት ነው። ይህም ደግሞ እግዚአብሔር በስም፣ በአካልና በግብር በሶስትነት የተገለጠ አምላክ ሲሆን በመለኮታዊ ስልጣን፣ በአገዛዝ፣ በባህሪ፣ በመፍጠርና በፍቃድ አንድ የሆነ አምላክ ነው። ስለዚህ አስተምህሮተ ሥላሴ ፈጽሞ ሥሉስ አማልክትን (Tritheism) የሚያሳይ አይደለም። በሥሉስ አማልክት (Tritheism) የሚያምኑት ሞርሞኖች (የመጨረሻው ዘመን ቅዱሳን) የጆሴፍ ስሚዝ ተከታዮች እንጂ ሥላሴያውያን አይደሉም። ሾለ ሞርሞኖች በሰፊው በሌላ ጊዜ እንመለሳለን። ብዙ ለዘብተኛም ሆኑ አጥባቄያነ የነገረ መለኮት ሊቃውንት አስተምህሮተ ሥላሴን የአሕዳዊ የመለኮት አስተምህሮ እንደሆነ በጥናታቸው አረጋግጠውት እንመለከታለን። ለተጨማሪ ምንጮች፦ William F. Albright, From the Stone Age to Christianity; H. Richard Niebuhr; Monotheistic Religion resources; Kirsch, God Against the Gods; Woodhead, An Introduction to Christianity; The Columbia Electronic Encyclopedia Monotheism; The New Dictionary of Cultural Literacy, monotheism

አስተምህሮተ ሥላሴ አሕዳዊ ወይስ መድብላዊ? Read More »

የነገረ ምክንያትነት ህግ(Law of Causality) – ክፍል 1

“ሰነፍ በልቡ፦ አምላክ የለም ይላል”  — መዝሙር 14፥1 የነገረ ምክንያትነት ህግ(Law of Causality) የፍልስፍና እና የሳይንሱ መሠረታዊ መርህ ሲሆን ማንኛውም ውጤት የራሱ የሆነ መንስኤያዊ እርሾ እንዳለው የሚያትት መርህ ነው። ምክንያትነት አመላካችነቱ የሆነ ነገር እንዲከሰት የሚያደርገውን ውጤት አዘል መንስኤን የሚያሳይ ነባቤ ቃል ነው። ክርስቲያናዊው የነገረ መለኮት እና የፍልስፍናው ሊቅ ዊሊያም ሌን ክሬግ ወደ ህላዌ የመጣ አካል ሁሉ ለመገኘቱ ምክንያት የሚሆን ከሳች ሐይል እንዳለ ይናገራል። በተጨማሪም ማንኛውም ነገር ከምንም እንደማይገኝ ይናገራል[1]፦ “ከምንም ምንም ነገር ሊከሰት አይችልም አልያም አንድ ነገር ከምንም ተነስቶ ህልው ሊሆን አይችልም” አንድ ነገር ከምንም ተነስቶ ሊከሰት ካልቻለ ለህልውናው መንስኤ የሆነ አንድ ምክንያት እንዳለ አመላካች ነው።[2] ነገር ግን ይህ አይነቱ ነባቤ ቃል የማይዋጥላቸው በፍልስፍናው አለም ያሉ ሳይንቲስቶች መኖራቸው የማይካድ ሐቅ ነው። ለምሳሌ ቴዎረቲካል ፊዚሽያኑ አሌክስ ቪሌንኪን ሁሉ አቀፉ ሕዋ በቅጽበታዊ(ድንገታዊ) ክሳቴው ከወናዊ ኳንተም (quantum vacuum) የመነጨ መሆኑ እና ይህም ደግሞ ሕዋ ከምንም ነገር ሊመጣ እንደሚችል የሚያሳይ ነው በማለት ይናገራል።[3] ይህንን ሐሳብ በመደገፍ ዴቪድ አልበርት ወናዊ ኳንተም (quantum vacuum) ነገሮች ከምንም መፈጠር እንደሚችሉ ያሳያል የሚል እምነት አለው።[4] በሌላ በኩል ደግሞ በሐይማኖታዊው ፍልስፍና የሚታወቀው ሪቻርድ ስዊንበርን አንድ ነገር ድንገት ያለ ምንም ምክንያት ህልውና አገኘ የሚለው ሙግት ሕጸጻዊ እና ኢ ምክንዮአዊ ሙግት ነው ሲል የእነ ዴቪድ አልበርት እና የአሌክስ ቪሌንኪንን እሳቤ ክፉኛ ይቃወማል።[5] በተለይ እውቁ እና በሳይንሱ አለም በክኑሳዊያን ተመራማሪዎች ትልቅ ተቀባይነት ያገኘው የታላቁ ፍንዳታ ቴዎሪ(Big Bang Theory) ሕዋ ኅሉቃዊ ጅማሮ(finite beginning) ያለው መሆኑን የሚያሳየውን መርህ ስንመለከት ይበልጡን አለም ካለመኖር ወደመኖር ያመጣት ከሳች ሐይል እንዳለ አመላካች ቴዎሪ ሁኖ እናገኘዋለን። ስለዚህ ሕዋ ያልነበረበት ካለ ለመገኘቱ ውጤት ከሳች አንድ ሐይል መኖሩን አንጡራዊ ቅድመ ሁኔታ ሁኖ እናገኘዋለን። ዊሊያም ሌን ክሬግ ይህ አይነቱ ከሳች አካል በአራት ወሳኝ ባህሪያተ ነጥቦች ይገልጹታል፥[6] 1) ጊዜአልቦ ማንነት(Timeless):- በታላቁ ፍንዳታ ቴዎሪ(Big Bang Theory) ጊዜ የሚባለው መስፈሪያ በራሱ ህላዌ ያገኘ በመሆኑ ጊዜን አስገኚው አካል ከጊዜ ውጭ ወይም ዘላለማዊ የሆነ ምንነት ነው 2) ኢ-ቁሳዊነት(Immaterial):- ቁሳዊ አካላት የተፈጠሩበት ምክንያት ስለሆነ ምክንያታዊው አካል ኢ-ቁሳዊነትን ባህሪዎት ገንዘቡ ያደረገ ነው 3) ልዕለ ሀይል ያለው(Powerful being):- ይህን ለቁጥር የማይመችን ፍጥረታዊው አለም ከዚህ አካል የተፈጠሩ እንደሆኑም መጠን ምክንያት እና ውጤት ከሳቹ አካል ወደር አልባ ሐይል ያለው መሆን አለበት 4) እኔ ባይ ቅዋሜ ማንነት ያለው(Personal):- የህዋ አስገኝ አካል እኔነት ያለው አካል መሆኑ መላው ፍጥረተ አለሙን ወደ መኖር ማምጣቱ ንቃተ ፈቃድ፣ እውቀት እና ስሜት ያለው አካል መሆኑን አመላካች ነው ይህን ያለንበትን ሕዋ ስናስብ ዝም ብሎ ድንገት የተከሰተ ሳይሆን ለመከሰቱ የሆነ አካል ከጀርባ እንዳለ የተፈጥሮውን አለም ባህሪዎት ስንመለከት የምንረዳው ጉዳይ ነው። ይህ ከሳች ሐይል ደግሞ ምንም ነገር(Nothing) ሊሆን ፈጽሞ አይችልም። የክኑሳዊው ሙግት ይሄንኑ የሚያስረዳ ነው፦ ስለዚህ፦ ሕዋ ከሳች ምክንያተ መንስኤ አለው ይህ የምንመለከተው አጽናፈ አለም በሆነ ጊዜ ህልው የሆነ እና ለመገኘቱ ጅማሮ ያለው ክስተት ነው። በሕዋ ውስጥ ያለ ማንኛውም ቁሳዊ አካል፣ ህያው ፍጥረት ሆነ ማንኛውም በዚህ ክበብ ውስጥ ያለ ክስተት ሁሉ ለመገኘቱ አስገኚ ምክንያት አለው። ለምሳሌ ዛፎችን ስንመለከት ለዛፎች መገኘት የዘሮች መተከል ወይም መዘራት እንደ ዋነኛ ከሳች ግብአት ነው። ይሄም ሐሳብ በፍልስፍናውም ምክንዮ ሆነ በሳይንሱ አለም ተቀባይነት አለው። ሌላው ሕዋ እራሱ ኅልቁ አላፊ ጊዜ ሊኖረው አይችልም። ምክንያቱም በእውናዊው አለም ፍጹም ኅልቁአዊ ኑባሬ (actual infinity) የሚባል ነገር እንደሌለ የሳይንሱ እና የፍልስፍናው አለም ያምናል። ክስተቶች ሁሉ ኅልቁ መሳፍርት ቢኖራቸው አጽናፈ አለሙ አሁን ያለበት ሁኔታ ላይ መድረስ እንደማይችል ይናገራሉ። በዚህ ምክንያት ሕዋ ወይም አጽናፈ አለም በሆነ ጊዜ የተከሰተ በመሆኑ ለክስተቱ ደግም ምክንያት የሌለው መንስኤያተ ምክንያት (uncaused cause) እንደሚኖረው አረጋጋጭ እውነታ ነው። እግዚአብሔር አምላክ ክስተቶች እና ለነገሮች ሁሉ ከሳች ምክንያት የሌለው መንስኤያተ ምክንያት (uncaused cause) ነው ስንል ከላይ እንደተመለከትነው ዘላለማዊ የሆነ፣ ቁሳዊ ያልሆነ፣ የማስገኘት ልዕለ ሐይልን የተጎናጸፈ እና እኔ ባይ ማንነታዊ ቅዋሜ ያለው አካል መሆኑን የሚገልጽ ነው። ሊቁ የኒሳው ጎርጎርዮስ ሾለ እግዚአብሔር ዘላለማዊነት ሲናገር፦“የእግዚአብሔር መለኮታዊ ባህሪዎት ያልተፈጠረ እና ዘላለማዊ የሆነ፤ ምንጊዜም የነበረ፣ ያለና የሚኖር ጅማሬ እና ፍጻሜ የሌለው፤ በጊዜ እና በቦታ ያልተወሰነ፣ የማይለዋወጥ ሁልጊዜም ያው የሆነ አምላክ ነው። ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ የሌለበት ጊዜና ሁኔታ አለ ሊያስብለን የሚያስችል ምክንያት ፈጽሞ አይኖርም” ሊቁ አምላክ ዘላለማዊ እና ለጅማሮው መንስኤ የሌለው በጊዜ የማይወሰን መሆኑን ይናገራል። ቅዱሱም መጽሐፍ እንደሚናገረው ማንኛውም ነገር ከአለመኖር ወደ መኖር ከመምጣታቸው በፊት እግዚአብሔር አምላክ እንደነበር ይናገራል፦ “ተራሮች ሳይወለዱ፥ ምድርም ዓለምም ሳይሠሩ፥ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ አንተ ነህ።”  መዝሙር 90፥2 ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክ ዘላለማዊ ከሆነ ከጊዜ ውጭ የሆነ እና ጊዜ የሚባለውን መስፈሪያ አስገኚ ነው። የነገረ ምክንያትነት ህግ(Law of Causality) በጊዜ ውስጥ የተገደበ ማንኛውም ነገር ለመገኘቱ ምክንያት አለው ስለሚል ፍጥረታዊው አለም ደግሞ ለመገኘቱ  ጅማሮ እና ከጀርባው ከሳች ምክንያታዊ ሐይል እንዳለው የሚያሳይ ነው። በሌላ በኩል ከጊዜ ውጭ የሆነው ከሳች ሐይል ግን ለመገኘቱ ምክንያት ሊኖረው ፈጽሞ አይችልም። ምክንያቱም ሾለ ከሳቹ ሐይል ስናወራ ዘላለም የሚባለው ገደብ የለሽ ጊዜ ስለሚነሳ እና ከጊዜ ውጭ ስለሆነ ልሹ ምክንያት የሌለው መንስኤያተ ምክንያት(Uncaused Cause) ነው እንላለን። ይሄም ክኑሳዊው ሙግት ያረጋግጥልናል። ማጣቀሻዎች፦ [1] Craig, William Lane. The Kalam Cosmological Argument. Wipf and Stock Publishers, 2000. page 303[2] “ከምንም ነገር ምንም ሊከሰት አይችልም/ex nihilo nihil fit”[3] Alex Vilenkin (Many Worlds in One): Suggests that the universe could arise spontaneously from “nothing.” (Page 181-182)[4] David Albert (Quantum Mechanics and Experience): Critiques modern redefinitions of “nothing” in scientific contexts. (Page 142-144)[5] Swinburne, Richard, The Existence of God /Clarendon Press, 2004, Page 50-53, 138-140/[6] Craig, William Lane. The Kalam Cosmological Argument. Wipf and Stock Publishers, 2000, page 182,87,228

የነገረ ምክንያትነት ህግ(Law of Causality) – ክፍል 1 Read More Âť

Scroll to Top