Author name: David Yeshua

ሱራ 15:9 እና የቁርኣን አጠባበቅ

ጽሑፍ፦ Samuel Greenትርጉም፦ David Yeshua መግቢያ ሱራ 15:9 እንዲህ ይላል፦ እኛ ቁርኣንን እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡ በዚህ የቁርኣን አንቀጽ መሠረት አላህ «ማስታወሻውን»(ዚክር) እንደሚጠብቅ ቃል ይገባል። «ዚክር» የሚለው ስያሜ አንዳንድ ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን የሚያመለክት ቢሆንም(ቁርኣን 16:43፣ 21:7)፣ በዚህ አውድ ውስጥ ግን ቁርኣንን የሚያመለክት ሆኖ እናገኘዋለን። ይህም ማለት በአንቀጹ ላይ ቃል የሚገባው አላህ ቁርኣንን እንደሚጠብቅ ነው። ይህን አንቀጽ መሠረት በማድረግ፣ የእስልምና ሊቃውንት አላህ ቁርኣንን በማይለወጥ፣ ተዓማኒ በሆነ ሁኔታ እና ፍጹምም በሆነ መንገድ ለመጠበቅ ቃል ገብቷል ሲሉ ይሞግታሉ። እንዲህ ይነበባሉ፦ ”The Qur’an is the only scripture which has been preserved in its exact original form, in its entire content, as it was revealed to the Prophet fourteen centuries ago, not a word added or removed. This is a historical fact beyond dispute. God Himself has assured us of its preservation.” ትርጓሜው “ቁርኣን በቀደመው መልኩ፣ በተሟላ ሁኔታ፣ ከአሥራ አራት ክፍለ ዘመናት በፊት ለነቢዩ በተገለጠው ሁኔታ፣ አንድ ቃል ሳጨመርበትና ከላዩ ላይ ሳይቀነስ ተጠብቆ የሚገኝ ብቸኛው መጽሐፍ ነው። ይህ ምንም የማያከራክር ታሪካዊ ሃቅ ነው። ጥበቃውን አምላክ ራሱ አረጋግጦልናል (ቁርኣን 15፡9)። ስለዚህ ከነቢዩ ዘመን ጀምሮ በዘመናት ሁሉ በመላው ዓለም አንድ ዓይነት የቁርኣን ቅጂ ብቻ ነው ያለው።”(Al-Ahsa Islamic Center, Before you start reading the Qur’an…, Hofus, no date, p. 4) Its text has remained exactly as it was revealed by God, providing a challenge to every would-be perpetrator of distortion. This is irrefutable testimony to the fact that this Qur’an is God’s own book and He is the One who guarantees its preservation. ትርጓሜው «ጽሑፉ አምላክ እንዳወረደው በትክክለኛ ይዘቱ እንዳለ የጸና ሲሆን፣ ሊበርዙ ለሚሞክሩ ሁሉ ተፎካካሪ የሌለው ፈተና ሆኖ ይኖራል። ይህም ቁርኣን የአምላክ ራሱ መጽሐፍ ለመሆኑ እና ጥበቃውን በእርሱ ዘንድ የተረጋገጠ ለመሆኑ የማያስተባብል ምስክርነት ነው።» (Sayyid Qutb, In the Shade of the Qur’an, U.K: Islamic Foundation, vol. 10, Surahs 12-15, verse 15:9, 2009, p. 253) ሱራ 15:9 እና የቁርኣን አንቀጾች መርሳት እውን በሱራ15:9 እንደምንመለከተው አላህ ቁርኣንን ከመረሳት ይጠብቀዋል ማለት ነውን? በፍጹም አይደለም፤ ምክንያቱም በቁርኣን ውስጥ አንቀጾች እንደተረሱ የሚናገሩ ሁለት አንቀጾች ይገኛሉ፦ «(ቁርኣንን) በእርግጥ እናስነብብሃለን፤ አትረሳምም፡፡ አላህ ከሻው ነገር በስተቀር፡፡(ሱራ 87፡6-7) «ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን።»(ሱራ 2:106) ሐዲሳት በሙሐመድ ሕይወት ዘመንም ሆነ ከእርሱ ሞት በኋላ ቁርኣን እንደተረሳ ወይም እንደተሻረ ምስክርነቶችን ይሰጣሉ። ከእነዚህም ውስጥ፦ Narrated Aisha: The Prophet heard a man reciting the Qur’an in the mosque and said, “May Allah bestow His Mercy on him, as he has reminded me of such-and-such verses of such a Surah.” አይሻ እንዳስተላለፈችው፦ የአላህ መልእክተኛ የሆነ ሰው በመስጊድ ውስጥ ቁርኣን እየቀራ ሰሙና እንዲህ አሉ፦ «የአላህ እዝነትና ምህረት በርሱ ላይ ይሁንና፤ ይህ ሰው የረሳሁትን እንዲህ እና እንዲያ የተባሉትን የቁርኣን አያዎች እና ምዕራፎችን አታወሰኝ።» (Sahih al-Bukhari 5037; vol 6, bk 61, no 556) Narrated Abdullah: The Prophet said, “Why does anyone of the people say, ‘I have forgotten such-and-such Verses (of the Qur’an)?’ He, in fact, is caused (by Allah) to forget.”  አብደላህ እንደተረኩት፦ ነቢዩ እንዲህ አሉ፦ «ከሰዎች መካከል አንዱ ‘እንደዚህ እና እንደዚያ ያሉትን የቁርኣን አንቀጾች ረስቼአለሁ’ ለምን ይላል? በእውነቱ እርሱ እንዲረሳ የተደረገው (በአላህ) ነው።» (Sahih al-Bukhari 5039; vol 6, bk 61, no 559) We used to recite a surah which resembled in length and severity to (surah 9) Bara’at. I have, however, forgotten it with the exception of this which I remember out of it: “If there were two valleys full of riches, for the son of Adam, he would long for a third valley, and nothing would fill the stomach of the son of Adam but dust.” በርዝመትና በጥንካሬ ከሱራ በረዓት ጋር የሚነፃፀር ሱራ እናነበንብ ነበር፡፡ ነገር ግን ከተከታዩ ውጪ የተቀረውን ረስቼዋለሁ፡- ‹‹የአደም ልጅ በኃብት የተሞሉ ሁለት ሸለቆዎች ቢኖሩት ሦስተኛውን ይመኛል፡፡ ከአፈር ውጪ የአደምን ልጅ ሆድ የሚሞላ ምንም ነገር የለም፡፡›› (Sahih Muslim 1050; bk 5, no 2286) ‘Abdullah bin ‘Umar reportedly said: “Let none of you say, ‘I have got the whole of the Qur’an.’ How does he know what all of it is? Much of the Qur’an is gone. Let him say instead, ‘I have got what has survived.’” አብደላህ ቢን ኡመር እንዲህ ማለታቸው ተዘግቧል፦ “ከእናንተ መካከል ማንም ሰው ሙሉውን ቁርኣን አግኝቼዋለሁ ብሎ መናገር የለበትም፡፡ የቁርኣን አብዛኛው ክፍል የጠፋ ሆኖ ሳለ ሁሉን አውቃለሁ ብሎ መናገር እንዴት ይቻላል? ከዚህ ይልቅ የተረፈውን አግኝቼዋለሁ ብሎ ይናገር፡፡” (Jalal ad-Deen as-Suyuti, al-Itiqan fee ‘Uloom al-Qur’an, Cairo: al-Halabi, 1935, vol. 2, p. 25) ስለዚህ የቁርኣን አንቀጾች ተረስተዋል፤ ኡመርም ቢሆን ማንም ሰው ሙሉውን ቁርኣን አውቃለሁ ማለት እንደሌለበት ተናግረዋል። በሱራ 87:6-7 እና 2:106 ላይ ሁለቱም አላህ የሻው ብቻ እንደተረሳ ቢናገሩም፣ ዋናው ነጥብ ግን የአላህ መጠበቅ አንቀጾች ከመረሳት ወይም ከመጥፋት እንዳላገዳቸው ያሳያል። ሱራ 15:9 እና የቁርኣን መለወጥ በ15:9 ማለት አላህ ቁርኣንን ከመለወጥ ይጠብቀዋል ማለት ነውን? አይደለም፤ ምክንያቱም በቁርኣን ውስጥ አንቀጾች እንደተለወጡ የሚናገሩ ሁለት አንቀጾች አሉ። በአንቀጽም ስፍራ አንቀጽን በለወጥን ጊዜ አላህም የሚያወርደውን ነገር አዋቂ ነው፡፡ «አንተ ቀጣፊ እንጂ ሌላ አይደለህም» ይላሉ፡፡ (ቁርኣን 16:101) «ከአንቀጽ ብንለውጥ ወይም እርሷን ብናስረሳህ ከርሷ የሚበልጥን ወይም ብጤዋን እናመጣለን።» (ቁርኣን 2:106) ይህ ብቻ አይደለም አንድ ቁርኣን እንደተለወጠ የሚያሳይ ምሳሌ ልጨምር፦Narrated Al-Bara: There was revealed:  “Not equal are those believers who sit (at home) and those who strive and fight in the cause of Allah.” (Qur’an 4.95) … and at that time ‘Amr bin Um Maktum, the blind man was sitting behind the Prophet. He said, “O Allah’s Apostle! What is your order for me (as regards the above verse) as I am a blind man?” So, instead of the above verse, the following verse was revealed:  “Not equal are those believers who sit (at home) except those who are disabled and those who strive and fight in the cause of Allah.” (Qur’an 4.95) “አል-በራ እንዳስተላለፉት፡- ‹ተቀማጮቹና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የሚታገሉት አይተካከሉም› የሚል ሱራ ወርዶ ነበር (4፡95)። ነቢዩ እንዲህ አሉ፡- ‹እስኪ ዘይድን ጥሩልኝ መጻፍያ ሰሌዳ፣ የቀለም ገንቦና (እንደ ብዕር የሚያገለግል) አጥንት ያምጣልኝ…› ከዚያ፡- ‹ተቀማጮቹና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የሚታገሉት አይተካከሉም… ብለህ ጻፍ› አሉት። በዚህ ጊዜ ዓይነ ስውሩ አምር ቢን ኡም መክቱም አጠገባቸው ተቀምጦ ነበር። እርሱም እንዲህ አለ፡- ‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ! ለኔስ የሚሰጡት ትዕዛዝ ምንድነው? እኔ ዓይነ ስውር ሰው ነኝ።› ስለዚህ በዚህኛው አንቀፅ ፋንታ ተከታዩ አንቀፅ ወረደ፡- ‹ከምእመናን የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር ተቀማጮቹና በአላህ መንገድ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የሚታገሉት አይተካከሉም።›”(ቁርኣን 4፡95) (Sahih al-Bukhari 4990; vol 6, bk 61, no 512, underline added) እዚህ ጋር እንደምናየው የ4፡95 ቀዳሚ ቅጂ ታርሞ “የጉዳት ባለቤት ከኾኑት በቀር” የሚል ተጨምሮበታል። ሱራ 2:106 እና 16:101 ስለሚለወጡት ነገሮች አላህ ባለቤቱ እንደሆነ ቢገልጹም፣ ነገር ግን ዋናው ነጥብ አሁንም አለ፦ የአላህ መጠበቅ አንቀጾች ከመለወጥ አላገዳቸውም። መደምደሚያሱራ 15:9 አላህ ቁርኣንን እንደሚጠብቅ ይናገራል፤ የእስልምና ሊቃውንትም ይህንን «አላህ ቁርኣንን በማይለወጥ እና በተስተካከለ መንገድ ፍጹም በሆነ ሁኔታ ይጠብቀዋል» በማለት ይተረጉሙታል። ሆኖም ቁርኣን ራሱ ስለራሱ የሰጠውን ማብራሪያ ስንመረምር፣ ይህ ጥበቃ አንቀጾች ከመረሳት ወይም ከመለወጥ እንዳልጠበቃቸው እንረዳለን። በሙሐመድ ሕይወት ዘመንም ሆነ ከእርሱ በኋላ አንቀጾች ከተረሱ ወይም ከተለወጡ፣ ቁርኣን የእስልምና ሊቃውንት እንደሚሉት በሆነ መንገድ አልተጠበቀም። ይህ ማለት በሱራ15:9 ሊቃውንቱ ቁርኣን ራሱ ያላለንን ሀሳብ እንዲናገር በማስገደድ ላይ ናቸው።

ሱራ 15:9 እና የቁርኣን አጠባበቅ Read More »

አርጌንስ እና የአዲስ ኪዳን ጥንታዊ ቅጂዎች

ጽሑፍ፦ Samuel Greenትርጉም፦ David Yeshua ይህ መጣጥፍ፣ በሊቁ አርጌንስ ድርሳን ውስጥ ስለ አዲስ ኪዳን የሰፈረውን ንግግር መሠረት በማድረግ የሚያብራራ እና በሙስሊሞች መካከል ለሚደረገው ውይይት እንዴት በጥቅም ላይ መዋል እንዳለበት የሚተነትን ነው። ከሙስሊም ወገኖች ጋር በሚደረጉ ውይይቶች መካከል የአዲስ ኪዳን ቅጂ ተዓማኒነት በተደጋጋሚ የሚነሳ ጉዳይ ሲሆን፣ አንዳንድ ሙስሊሞች የአዲስ ኪዳን ጽሑፍ ተዓማኒ አለመሆኑን ለማስረዳት የአርጌንስን ጽሑፍ በማስረጃነት ያቀርባሉ። በዚህም ጽሑፍ የእስክንድሪያው አርጌንስን(ከ184 – 253 ዓ.ም) የኖረ የቤተክርስቲያን ሊቅ ሲሆን እውን ስለ አዲስ ኪዳን ጥንታዊያን ቅጂች የተዛባ ምልከታን ያምናልን? የሚለውን በመተንተን የማስቀምጥ ይሆናል። የሊቁ ጽሑፍ እንዲህ ይነበባል፦ “The differences among the manuscripts [of the Gospels] have become great, either through the negligence of the copyists or through the perverse audacity of others; they either neglect to check over what they have transcribed, or, in the process of checking, they lengthen or shorten, as they please.”1 “በእደ ክታባት ገልባጮች ቸልተኝነት አልያም በሌሎች እኩይ አላማ የተነሳ በወንጌላት እደ ክታባት ቅጂዎች መካከል ያለውን ልዩነት እጅግ የጎላ መሆን ችሏል። የገለበጡትን ጊዜ ሰጥተው ለመርመር ቸል ይላሉ አልያም ደግሞ በሚመረምሩበት ወቅት እንደ ልባቸው ፈቃድ ያስረዝሙታል ወይም ያሳጥሩታል።” ከዚህ ከአርጌንስ ጽሑፍ በመነሳት ሙስሊም ወገኖች የአዲስ ኪዳን እደክታብ በሦስተኛው ክፍለ ዘመን ላይ ከባድ ችግሮች እንደነበሩበት እና በዚህም ምክንያት ዛሬ ላይ በእጃችን የሚገኙ ምንባባት ተዓማኒ እንዳልሆነ ይደመድማሉ፤ ጨመርም አድርገው ቁርዓን እንዲህ ዓይነት የጽሑፍ ግድፈቶች እንደሌሉበት ይደመድማሉ። አንድ ክርስቲያን ይህን የአርጌንስን አባባል እንዴት ሊረዳው ይገባል? ለዚህስ ሙግትና መልስ ለሚሻ ጥያቄ ምን ብሎ መመለስ አለበት? የሚለውን እኔ በሦስት የመልስ ነጥቦችን አስቀምጣለሁ። ነጥብ አንድ፦  ሊቁ አርጌንስ የአዲስ ኪዳንን ጽሑፍ ተዓማኒነትን በፍጹም አይክድም። ይልቅ በድርሳናቶቹ ሁሉ የአዲስ ኪዳን ምንባባትን በማጣመር የሚቀጥል ሲሆን፣ እንደ እስትንፋሰ እግዚአብሔር ቃሉን ይተማመንባቸዋል። ይህ ማለት፣ አርጌንስ አንዳንድ ሙስሊሞች ወደ ደረሱበት ዓይነት ድምዳሜ መሠረት በፍጹም አልደረሰም ማለት ነው። ነጥብ ሁለት፦ ችግሩ ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ለማወቅ አርጌንስ ስለጠቀሳቸው የምንባባት ልዩነቶች (textual variants) አንዳንድ ምሳሌዎችን ማየት ያስፈልገናል። እነዚህ ምሳሌዎች ከሌሉ፣ በቀላሉ የተጋነነ ወይም ተገቢ ያልሆነ የተሳሳተ ግንዛቤ በሊቁ ላይ ሊፈጠርብን ይችላል። እንደ መልካም አጋጣሚ ሆኖ፣ እነዚህ ምሳሌዎች በቀላሉ ይገኛሉ፤ ምክንያቱም አርጌንስ ራሱ በድርሳኑ ውስጥ ጠቅሷቸዋል። ብሩስ ሜትዝገር (Bruce Metzger) የአርጌንስ ጽሑፎች በጥልቀት በመመርመር እነዚህን የጽሑፍ ልዩነቶች ሰብስቧቸዋል። የምርምሩም ውጤት ‘Explicit References in the Works of Origen to Variant Readings in New Testament Manuscripts’ በተሰኘው ጽሑፍ ላይ ታትሟል። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ሜትዝገር አርጌንስ የጠቀሳቸውን 22 የጽሑፍ ልዩነቶች አቅርቦ ይወያይባቸዋል። ስለሆነም፣ አርጌንስ በትክክል ስለ ምን እየጻፈ እንደነበረ ማወቅ እንችላለን። አርጌንስ የጠቀሳቸው የ22ቱ ልዩነቶች ማጠቃለያ የሚከተለው ነው፦ መደምደሚያ ሐሳብ በሊቁ አርጌንስ ክታብ ውስጥ በጉልህ 22 የምንባብ ልዩነቶች ሰፍረዋል። ከእነዚህ ውስጥ በ20ቹ ላይ የታየው የእጅ ጽሑፎች ምንባባት ልዩነት በአጠቃላይ ከአንድ ቃል ጋር የተያያዙ ሲሆን፤ እርሱም ተመሳሳይ ትርጉም ያለው ሌላ ተመሳሳይ ቃል(synonym)፣ የተለየ የሰዋስው አወቃቀር፣ የተለየ ስም፣ የጎደለ ወይም የተጨመረ ቃል ተገኝቶ ሊሆን ይችላል። ጽሑፉ አንድ ዓይነት ሆኖ ሳለ፣ አርጌንስ አሁንም ጥያቄ የነበረበት ሁለት ምሳሌዎች ግን ነበሩበት። ይህም የሆነበት ምክንያት ሊቁ አርጌንስ ምሑርና ባለ ብዙ ቋንቋዎች ባለቤት እንደመሆኑ መጠን፣ የላቀ የጽሑፍ ጥራትና ወጥነትን ይፈልግ እንደነበረና ያንን ዓረፍተ ነገር የጻፈውም ለዚሁ እንደሆነ ምንም ጥርጥር የለውም። በዚህም ሊቁ ከሰጣቸው ምሳሌዎች ውስጥ መረዳት የምንችለው፣ በአዲስ ኪዳን ጽሑፍ ላይ ምንም ዓይነት ጠንካራ የሚባል ችግር እንደሌለ ነው። ብዙውን ጊዜ ከአንድ ቃል ጋር የተያያዙ ጥቂት የጽሑፍ ልዩነቶች ያሉ ሲሆን፣ እነዚህንም ‘የምንባቤያዊ ሕየሳ’ (textual criticism) መስፈርትን በመጠቀም ለይቶ ማስተካከል ይቻላል። ስለሆነም፣ አርጌንስ አዲስ ኪዳንን በተመለከተ ችግሮች እንዳሉበት ያስቀምጣል ማለት እጅጉን ማጋነን ነው። የቀረበውም ማስረጃ ይህንንም በፍጹም አያሳይም። ሦስተኛውና የመጨረሻው ነጥቤ፦ የእስልምና ምሑራን ቁርዓንን በሚተረጉሙበት(በሚያብራሩበት) ጊዜ፣ ልክ እንደ ሊቁ አርጌንስ ሁሉ እነርሱም በቁርዓን ጽሑፍ ውስጥ ስላሉት የቅጂ ልዩነቶች(variants) ይወያያሉ። ለዚህም ሦስት ምሳሌዎች ላንሳ፦ አል-ጠበሪ እና ቁርዓን 2:2133፦ በዑስማን የተደነገገው(የተመደበው) መደበኛ የቁርዓን ጽሑፍ ‘የሰው ልጆች ሁሉ አንድ ማኅበረሰብ ነበሩ፤ ከዚያም አላህ ነቢያትን አስነሳ’ ይላል። ሆኖም በአብደላህ ኢብን መስዑድ የቁርዓን ቅጂ ላይ ‘የሰው ልጆች ሁሉ አንድ ማኅበረሰብ ነበሩ፤ ከዚያም ተለያዩ(ተጣሉ)፤ አላህም ነቢያትን አስነሳ’ የሚል ነበር። ሳሂህ አል-ቡኻሪ እና ቁርዓን 92:3 4፦ በዑስማን የተደነገገው መደበኛ የቁርዓን ጽሑፍ ‘ወንድና ሴትን በፈጠረው እምላለሁ’ ይላል። ሆኖም በአብደላህ ኢብን መስዑድ የቁርዓን ቅጂ ላይ ‘በወንዱና በሴቷ እምላለሁ’ የሚል ነበር። አብደላህ ዩሱፍ አሊ እና ቁርዓን 33:6 5፦ በዑስማን የተደነገገው መደበኛ የቁርዓን ጽሑፍ ‘ነቢዩ ለምእመናን ከነፍሶቻቸው ይልቅ ቅርብ ነው፤ ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው’ ይላል። ሆኖም በኡበይ ኢብን ካዕብ የቁርዓን ቅጂ ላይ ‘ነቢዩ ለምእመናን ከነፍሶቻቸው ይልቅ ቅርብ ነው፤ እርሱም ለእነርሱ አባት ነው፤ ሚስቶቹም እናቶቻቸው ናቸው’ የሚል ነበር። በታሪክ ሂደት ውስጥ በሙስሊሞች ዘንድ ለእነዚህ የጽሑፍ ልዩነቶች የተሰጡት ምላሾች የተለያዩ ነበሩ። በእስልምና የመጀመሪያዎቹ አሥርተ ዓመታት ውስጥ እነዚህ ልዩነቶች እንደ ችግር ይታዩ የነበረ ሲሆን፣ ሦስተኛው ከሊፋ ዑስማን አንድ ወጥ የሆነ መደበኛ የቁርዓን ቅጂ እንዲዘጋጅና ሌሎች የተለያዩ የእጅ ጽሑፎች በሙሉ እንዲቃጠሉ(እንዲጠፉ) አዟል።6 ሌሎች ሙስሊሞች ደግሞ እነዚህ የጽሑፍ ልዩነቶች ትክክለኛና ተዓማኒ (authentic) እስከሆኑ ድረስ የቁርዓኑ አካል አድርገው ይመለከቷቸዋል። ይህ ማለት ልዩነቶቹ መመዘንና መፈተሽ አለባቸው ማለት ነው። ይሁን እንጂ አብዛኞቹ ሙስሊሞች ስለነዚህ የጽሑፍ ልዩነቶች ግንዛቤ የላቸውም። ‘The Encyclopedia of the Quranic Readings with an Introduction to Readings and Famous Readers’ የተሰኘው ኢንሳይክሎፔዲያ የ10,243 የጽሑፍ ልዩነቶችን ዝርዝር መረጃ ይዟል።7 ማጠቃለያ ሊቁ አርጌንስ ስለ አዲስ ኪዳን ምንባባት ልዩነት የተናገረውን ንግግር አንዳንድ ጊዜ በሙስሊሞች ዘንድ አዲስ ኪዳን ከባድ ችግሮች እንዳሉበት ለማሳየት ጥቅም ላይ ይውላል። ነገር ግን ከላይ እንዳየነው ሊቁ በፍጹም ወደዚህ ድምዳሜ አልደረሰም፤ ከሰጣቸውም ምሳሌዎች መረዳት የሚቻለው አብዛኛውን ጊዜ ከአንድ ቃል ጋር የተያያዙ ጥቂት የጽሑፍ ልዩነቶች ብቻ መኖራቸውን ነው። እነዚህንም የምንባቤያዊ ሕየሳ(textual criticism) መሥፈርቶችን በመጠቀም ለይቶ ማስቀመጥ ይቻላል። በተጨማሪም ቁርዓን ራሱ የጽሑፍ ልዩነቶች ያሉበት መሆኑንና ሙስሊሞች ቀደም ሲልም የያዙት፣ አሁንም ድረስ እየያዙት ያለ ጉዳይ መሆኑን አይተናል። ስለሆነም ሙስሊሞች አርጌንስ አዲስ ኪዳንን ተዓማኒነት የጎደለው አድርጎ ያስብ ነበር የሚል የተሳሳተ ግንዛቤ ለመፍጠር መሞከር የለባቸውም፤ እንዲሁም ቁርዓን ከጽሑፍ ልዩነቶች የጸዳ ነው የሚል ስሜት ለመስጠትም መጣር የለባቸውም። [ማሳሰቢያ፦ ይህ የትርጉም ጽሑፍ በጸሐፊው ሙሉ ፍቃደኝነት የተተረጎመ መሆኑን እንገልጻለን።] ማጣቀሻዎች የጽሑፍ ምንጭ፦ https://www.answering-islam.org/authors/green/origen.html

አርጌንስ እና የአዲስ ኪዳን ጥንታዊ ቅጂዎች Read More »

የሥላሴ ሥነ አመክንዮአዊ ችግር(LPT)

የሥላሴ አስተምህሮ በተለያዩ ሰዎች በተለያዩ ዘመናትም ትችት ሲደርስበት መስማት የተለመደ ነው። ይህንንም ትምህርት በሰዎች አእምሮ ዘንድ ፈጽሞ መረዳት የማይቻልና በተለይም “አምላክ/God/” የሚለውን ቃል በተለያዩ አይነት በመጠቀም በሥነ አመክንዮ ዘንድ መሠረታዊ ችግር እንዳለበት ለማሳየት ይሞክራሉ። ሙግቱ እንዲህ ይቀርባል፦ 1) ክርስቲያኖች አብ አምላክ ነው፣ ወልድ አምላክ ነው፣ መንፈስ ቅዱስ አምላክ ነው ይላሉ። 2) ነገር ግን “አምላክ” የሚለው ቃል በአንድ ጊዜ አብን፣ ወልድን እንዲሁም መንፈስን የሚያመለክት ከሆነ አንድን ምንነት ያለውን አምላክ በቋሚነት ሊያመለክት አይችልም። 3) ስለዚህ ይህ አስተምህሮው ከአመክንዮአዊ ወጥነት ይልቅ አሻሚ የሆነ ግራ አጋቢ ትርጉም ላይ እንዲሆን ያደርገዋል። መልስ ይህ ሙግት መሠረት ያደረገው እኛን(ክርስቲያኖችን) “አምላክ” የሚለውን ቃል የተለያዩ አካላትን በተለያየ መንገድ መገለጫ እንደሆነ በማመልከት እንደምንል አድርጎ ሙጉቱን በሥሑት ነጥቦች ላይ ገንብቶ የጀመረ ነው። ማለትም “አምላክ” አብን በአንድ መንገድ፣ ወልድን በሌላ ፣ እንዲሁም መንፈስ ቅዱስን በሌላ እንደማለት ነው። ነገር ግን ይህ አይነቱ መረዳት በሥላሴ የአምላክነት ባሕርይ ወይም “ግጻዌ መለኮት” መረዳት ውስጥ የማያታወቅ ነው። ታዲያ አምላክ ማለት ግን በኑባሬው ያለማቋረጥ አንድ፣ የማይከፋፈል መለኮታዊ ማንነትን የሚያመለክት መለኮታዊ ባህርይ የሚል ቃል ነው። ስለዚህ ክርስቲያኖች “አብ አምላክ ነው”፣ “ወልድ አምላክ ነው” እንዲሁም “መንፈስ አምላክ ነው” ሲሉ የአምላክነት ባህርይን ያለውን አካላቶቹ አሏቸው በዚህም እያንዳንዱ አካል ያንን የመለኮትነትን ባህርይ ሙሉ በሙሉ ይጋራሉ ማለታቸው ነው። ይህም አንድ አምላክ ብቻ አለ ሲባል፣ አንድ ምንነት እንዳለ እያረጋገጡ ነው። አንዱ አምላክ በሦስት አካል የተገለጠ ነው ሲሉ ደግሞ አንድ አምላክ በአካል ሦስት ነው እያሉ ነው። አብ፣ ወልድ እና መንፈስ አንድ አምላክ ናቸው ሲሉ እያንዳንዱ አካል መለኮታዊ ባህርይ እንዳለው እያስረገጡ ነው። ስለዚህ፣ ከላይ በሥላሴ ላይ በተነሳው የሶስቱ ነጥብ ሙግቶች፣ “አምላክ” የሚለውን ቃል ውይይት ከመገባቱ በፊት ከተብራራ፣ የሚመጣውን የትኛውንም ጥያቄ ይመልሳል ማለት ነው።

የሥላሴ ሥነ አመክንዮአዊ ችግር(LPT) Read More »

ኑ መጽሐፍ ቅዱስን እንተዋወቀው

ሰላም። በመጀመሪያ ከእኛ ጋር መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ዝግጁና ፍቃደኛ በመሆናችሁ እግዚአብሔርን እናመሰግናለን። ምናልባት ይህን በእጃችሁ ያለውን መጽሐፍ አዲስ እና እንግዳ ሆኖባችሁ ይሆናል። ዛሬ በዚህ ጽሑፍም በእጃችሁ የሚገኘው መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው መጽሐፍ ምንድነው የሚለውን በአጭሩ የምንተዋወቅ ይሆናል። ክርስቲያኖች 66ቁጥሮች ርዝማኔ ያላቸው መጻሕፍ አላቸው። እነዚህም መጻሕፍትበሁለት ክፍል ይቀመጣሉ። እነርሱም ብሉይ ኪዳን እና አዲስ ኪዳን በማለት ይከፈላሉ። ብሉይ ኪዳን 39 አዲስ ኪዳን ደግሞ 27 መጻሕፍትን ይዘዋል። መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ቃል የእንግሊዝኛው አቻ ትርጉም “ባይብል” የሚለው “ቢብሊያ” ከሚለው የጽርእ(የግሪክ) ቃል የመጣ ሲሆን “መጻሕፍት” ማለት ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በአንድ ግለሰብ እንዲሁም በጥቂት ዓመታት ውስጥ የተጻፈ መጽሐፍ ሳይሆን፣ በብዙ መቶ ዘመናት ውስጥ በተለያዩ ቋንቋዎች ከ40 በላይ ጸሐፊያን ያሉትና በ1500 ዓመታት ውስጥ የተጻፉ የተለያዩ መጻሕፍት ስብስብ ነው፡፡ በእርሱም ውስጥ እግዚአብሔር በቀጥታ ከህዝቡ ጋር ይነጋገራል፣ በሌላ ጊዜ ደግሞ በቅዱሳን ሰዎች ሐሳብና ቃል አማካኝነት ሲናገር፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በዘመን መጨረሻ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ተግልጦ ተናግሮናል። በመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን የጊዜ አመዳደብ መሰረት የመጀመርያው ክፍል ከክርስቶስ ልደት በፊት በ1400 ዓ.ዓ. አካባቢ እንደሆነና የመጨረሻው ደግሞ ከክርስቶስ ልደት በኋላ በ90 ዓ.ም. አካባቢ እንደተጻፈ ይታመናል። መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ማወቅ ካሉብን ልዩ ሁኔታዎች መካከል መጽሐፍ ቅዱስ እንደ ቁርአን እና ሌሎች አይነት መገለጥ እንዳልሆነ ነው። ይህን ለመረዳት ጳውሎስ ለመንፈሳዊ ልጁ ለጢሞቴዎስ በላከው 2ኛ ጢሞቴዎስ 3፥16-17 እንዲህ ሲል ይናገራል፦ “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” በዚህ ክፍል ላይ ጳውሎስ የእግዚአብሔርን ቃል፣θεόπνευστος “ቴኦፕኔውስቶስ” መሆኑን ሲናገር የቃሉ ፍቺ θεό “ቴኦ” ማለት “እግዚአብሔር” እና πνευστος “ፕኔውስቶስ” ማለትም “መንፈስ” ከሚሉ ሁለት የጽርእ ቃል የተገኘ ነው፤ በአንድ ላይ ሲነበቡም “እስትንፋሰ እግዚአብሔር” የሚል ነው። ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስ ሁሉ በእግዚአብሔር መንፈስ እስትንፋስ የተጻፈ ነው፤ የሰዎችን ልብ ሁሉ የሚቀይር እንዲሁም በእምነት የሚያነብ የእርሱን ድምፅ ይሰማል። በግልጽ ልብና አእምሮ ካነበብነው፣ እግዚአብሔር እኛ በማናቀው መንገድ ሲናገረን እንገኛለን። ስለዚህ ይህ የያዛችሁት መጽሐፍ ሌሎች ጋር እንዳለ አይነት መጽሐፍ እንዳልሆነ በእነዚህ መንገዶች ትረዳላችሁ። የመጻሕፍቱ ዝርዝር # መደቦች የመጽሐፍቱ ብዛት መጻሕፍቱ 1 የሙሴ ሕግ (ፔንታቱክ) 5 ዘፍጥረት – ዘዳግም 2 የታሪክ መጻሕፍት 12 እያሱ – አስቴር 3 ቅኔ/ግጥም 5 እዮብ – መኃልየ መኃልይ ዘሰሎሞን 4 አበይት ነብያት 5 ኢሳይያስ – ዳንኤል 5 ደቂቅ ነብያት 12 ሆሴዕ – ሚልኪያ       ➡ አጠቃላይ ብሉይ ኪዳን 39 6 ወንጌላት 4 ማቴዎስ – ዮሐንስ 7 የታሪክ መጽሐፍ 1 ሐዋርያት ሥራ 8 የጳውሎስ መልእክታት 13 ሮሜ – ፊልሞና 9 አጠቃላይ መልእክታት 8 ዕብራውያን – ይሁዳ 10 ራዕይ(አቡቀለምሲስ) 1 ራዕይ ➡ አጠቃላይ አዲስ ኪዳን 27 ➡ ጠቅላላ ድምር 66 መጽሐፍ ቅዱስ በአጭሩ የመጽሐፉ ዋና ዋና መልእክቶች፦ በኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 ላይ ዓለምን የፈጠረ እግዚአብሔር እንደሆነ ገልጾ በማሳየት ይጀምራል። በዚህም እግዚአብሔርም ፍጥረታትን በስድስት ቀን እንደፈጠረ በሰባተኛው ቀን እንዳጠናቀቀ እንመለከታለን። በዚህም ውስጥ “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር” በማለት ሰው የሚለውን ከፍጥረቱ ሁሉ መካከል ልዩ አድርጎ እንደሰራው፣ ስማቸውንም አዳም እና ሔዋን እንደነበሩ እንመለከታልን። በዚህም የፍጥረት መጽሐፍ ላይ የምንረዳው የዓለማትና የእኛ ሠሪ አንዱ እግዚአብሔር ብቻ እንደሆነ አስተዋውቆ ይጀምራል። ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ በቅድስና የተመሰገነውን አምላክ አዳምና ሔዋን ኃጢአት ሰርተው እንዳሳዘኑት በዚህም ከእግዚአብሔርም ጋር የነበራቸው ግንኙነት ሲያጡ እንመለከታለን። ከዚያም እግዚአብሔርም በሙሴ በማስነሳት(ዘፀአት 7) በእርሱ በኩል አሥርቱን ትእዛዛት(በዘፀአት 20) እንዴት እንደሰጣቸው እንመለከታለን። በታሪክ መጻሕፍት ውስጥ የኪዳኑ ሕዝብ ኪዳን ከሌላቸው ጣኦት አምላኪያን ጋር የነበራቸውን ውጣ ውረድና የእግዚአብሔርን ፍቅሩ ጽድቁን ባደረጉት የቁጣው ፀሐይ ደግሞ ባልፈለጉት ላይ እንደወጣች በሰፊው ተከትቦ እናገኛለን። በእያንዳንዱ ታሪኮችን ውስጥ የምንገነዘበው ነገር እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለው የታመነ ፍቅሩ ነው፤ እርሱም በደንዳናው ሕዝበ እስራኤል ላይ ምን ያህል ታጋሽ የሆነ ፍቅር እንዳለው በስፊው ተቀምጦልናል። ለምሳሌ፦ እንደ ኖኅ፣ አብርሃም፣ ሙሴ፣ ኢዮብ፣ ዳዊት እና ሌሎች ያሉ የተወሰኑ ሰዎችን በልዩ መንገድ ጠርቶ ይህ ኃያል አምላክ በየዘመናቱ ፍቅሩን ሲገልጥ እናገኘዋለን። እነዚያ የመረጣቸው የኪዳኑ ሕዝብ በኋላም ከአመጻቸው የተነሳ ለእግዚአብሔር ሕግ መታዘዝ እንዳቃታቸው ስለዚህም እግዚአብሔር በመጨረሻው ዘመን የሰው ልጆች ያፈረሱትን የድሮውን ኪዳን ለመፈጸም እና አዲስን ኪዳን ከህዝቡ ጋር ለማቆም አንድያ ልጁን የላከው። ይህ አዲሱ ኪዳን ግን በደካማ የሰው ልጆች ሥራና ታዛዥነት ላይ የተመሰረተ ሳይሆን፣ በሰማያዊው አዳኝ፣ በዘላለማዊው ቃል በሆነው በመሲሕ ላይ ነው። ይህ መሲሕ በብሉይ ኪዳን ዘመን ጌታችን ኢየሱስ ከድንግል ከመወለዱ ከ700 ዓመት በፊት በነብዩ ኢሳይያስ ላይ ተነግሮለታል። አሁን የትንቢቱ ፍጻሜው ቀረበና እርሱ ራሱ በትልቁ የሮም ግዛት እጅጉን ደሳሳና አናሳ በሆነች ቤት የተወለደ ሆኖ መጣ።(ዮሐንስ 1፥14) አዎን ከላይ እንዳልነው እግዚአብሔር ኃያልና የከበረ ነው፣ ነገር ግን እርሱን እንድናውቀው ግን የባሪያን መልክ ያዘ።(ፊልጵስዩስ 2) የክርስቶስን ሕይወትና አገልግሎት ስናነብ ሳለ በአእምሯችን ሥሑት ትርጓሜ እንዳይፈጠር ሥነመለኮታችንን የተቃኘ መሆን አለበት። በዚህም የሚያግዟችሁን ጥሩ መጋቢያን መፈለግ ጥሩ ነው። አንዳንድ መናፍቃን አምላክ አይደለም ይልቅ ሰው ብቻ ነበር በማለት ሊያስቱ ይሞክሩ ይሆናል። በዚህም ትምህርት ንፋስ ተውስደን “ኢየሱስ ሰው ብቻ ነበር” ካልን፣ ሙሉ በሙሉ እንስታለን። “ሰው አይደለም አምላክ ብቻ ነበር” ካልንም ሰውነቱን ክደናልና ከሃዲያን እንባላለን። የነገረ ክርስቶስ ጥናት ስፊ ውቂያኖስ ነው። ይህንንም ሐሳብ መምህራን ሲገልጡ “…ጥናቱም ልክ ቀጭን ምላጭ ላይ እንደመራመድ ማለት ነው። በግራ ብንወድቅ አውጣኬ አለ። በቀኝ የወደቅን የሆንን ከሆነ ድግሞ ንስጥሮስ አለ…” በማለት ያስቀምጣሉ። ታዲያ ነገረ ክርስቶሳችን ጥናቱ ያልተቃኘ ከሆነ መርማሪው እንዳይወድቅ ይፍራ። ጥሩ አንባቢ ክርስቲያን ግን በቀጭኗ ምላጭ ላይ በቀስታ ይራመዳል። ስለዚህ በዚህን መጽሐፍ ቅዱስን ጥናት ወቅት አውዱን ያልሳተ ትርጓሜ መጠቀም፣ ተዓማኒ የሚባሉ ማብራሪያውችን ማገላበጥ፣ ታሪካዊ፣ ስዋሰዋዊ እና ቁማዊን ትርጉም ምን እንደሆነ ከሥሩ ማጥናት እጅጉን ያስፈልጋል።  ማጠቃለያ በመጨረሻም አንድ ሰው ለምን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር መተዋወቁ ለሕይወቱ ምን ይጠቅመዋል? ያለ እንደሆነ አንደኛ፦ ኢየሱስ አምላኩና ጌታው እንደሆነ እንደሞተ እና በሦስተኛው ቀን ከሙታን እንደተነሳ ያምናል። ሁለተኛ፦ ክርስቶስ በከፈለው የቤዛነት ሥራ በኩል ብቻ የዘላለም ሕይወት አለህ ስለሚለው ነው። ሦስተኛ ፦ ሰው በሕግ ሥራ ፈጽሞ ሊጸድቅ ስለማይችል፣ በዚህም የተከፈለለትን የእዳ ክፍያ በክርስቶስ አምኖ ተስፋውንም በአለቱ ላይ ስለሚተክል ነው።(ሐዋ 4፥12) ስለዚህ አሁን ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያልተዋወቃችሁ ወገኖች ይህንን ታላቅ መጽሐፍ አግኝታችሁ ታነቡት ዘንድ እናበረታታችኋለን። በቃሉ ውስጥ የተገለጠውን እግዚአብሔርን ፊት ለፊት የምናይበት ሕያው መስታወት ቅዱስ ቃሉ ብቻ በመሆኑ በውጤቱ ክርስቶስ ኢየሱስን በማመን የሚገኘውን የዘላለምን ሕይወት እንደምታገኙ ባለ ሙሉ ተስፋዎች ነን፡፡

ኑ መጽሐፍ ቅዱስን እንተዋወቀው Read More »

የማርቆስ እና እስረኛው ታሪክ

በሰሞኑን በተነሳው በቻርሊ ከርክ ሕልፈት ምክንያት ሁለት ጽንፍ ጎራዎችን እንመለከታለን። አንዱ ጎራ በዚህ ሀሳቡ አልስማማውም ሲል ይኼኛው አይደለም እንዲያማ አይባልም በዚህ ሀሳቡ እጋራዋለሁ በማለት ሲወያዩ ስመለከት ነበር። በእርግጥ ቻርሊን በአንዳንድ ሀሳቦቹ ባልስማማም ነገር ግን በወጣቱ ዘንድ ያለውን ተጽዕኖ እና ወደ ኋላ ገሸሽ በማይለው አቋሙ ሁሌ የማደንቀው ሰው ነው። በሳልና አዕምሮውን የሚጠቀም፣ በልቡን የማያምንበት ከሆነ የማያደርግ ነበር። በኋላ በተለያዩ ገጾች የሚጻፉትንና ደጋግመው የሚመጡትን የተለያዩ ጽሑፎችና የምስል ቪዲዮዎችን ለመመልከት ሞክሬ ነበር። በእርሱም ህልፈት ምክንያት ብዙዎች ከኢ-አማንያን ወደ ክርስትና እንደመጡና ቤተክርስቲያንን ሥፍራ አጣን እስከማለት ደርሰው እንደተገኙ እንመለከታለን። ይኼንን ታሪክ ስመለከት በሞቱ ብዙዎችን መጥራቱን ሳስብ የማርቆስና የእስረኛው ታሪክ ጋር ከዚህ ቀደም ፊልጵስዩስን በማጠናበት ጊዜ ከጻፍኩት ጽሑፍ ጋር የቻርሊ ከርክ ታሪክ ተመሳሰለብኝ። የማርቆስ እና የእስረኛው ታሪክ በፊልጵስዩስ 1፥21 ላይ የተመሠረተ አፈ-ታሪክ ነው። ከታሪኩ በፊት ቃሉ እንዲህ ይነበባል፦ “ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና።”  — ፊልጵስዩስ 1፥21 ማርቆስ በፊልጵስዩስ የሚኖር ወጣት ለእምነቱ ታጋይ ሰው ነበር። ማርቆስ በክርስትና ምክንያት ዘወትር በሮማውያን እና በቅርብ ወዳጆቹ መገለል ከዛም ታልፎ መከራ በገጠመው ቁጥር ኹል ጊዜ ወደ እስር ቤት ይሄዳል። በዛም እስር ቤት በእምነቱ ጽኑ የሚባለውን ጳውሎስን እንዲጎበኝ ይሄድ ነበር። የእስር ቤቱ ጨለማ ክፍል ሁልጊዜ ለማርቆስ አስጨናቂው መንገዱ ነበር፣ ነገር ግን ጳውሎስ በዚያ ውስጥ ሁልጊዜ ደስታ የተሞላበት ዓይን ነበረው። አንድ ምሽት ላይ እንደተለመደው ለጉብኝት በሚሄድበት ጊዜ ማርቆስ ስለ ጳውሎስ ከሚደርስበት መከራ መደሰት ምክንያቱ ምን እንደሆነ እንዲህ ሲል ጠየቀው፦ «ጳውሎስ፣ ነገ ሊገደሉህ ሲሆን እንዴት እንደዚህ ፊትህ ላይ ደስታ ይታያል? ሞትን አትፍራም?» ይለዋል ጳውሎስም ከትከሻው ላይ እጁን አሳረፈ እና እንዲህ አለ፦ «ማርቆስ፣ ከክርስቶስ ውጪ በዚህ ዓለም ሳለህ ጥሩ ሆነ መጥፎ የሚባል ነገር የለም። ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና። ባለሁበት ዘመን ሁሉ ክርስቶስን እናገራለሁ፤ በዚህም የክርስቶስ አካል ፍጹማን ይሆኑ ዘንድ በመከራዬ ሁሉ አጽናናለሁ። በዚህስ ብሞት ግን፣ ከእርሱ ጋር እኖራለሁ። እኔ እንዴት እጎዳለሁ?» በማለት መለሰለት። ማርቆስ ተደነቀ። «እንግዲህ… በኑሮህም በሞትም ክርስቶስ ድሌ ነው የምትለኝ?» አለ። ጳውሎስም፦ «አዎን። ይህች ዓለምን እንዳልመስል በደማስቆ መንገድ ላይ ሕይወትና አገልግሎትን ሰጥቶኛል። በዛም በተቀበልኩት ሕይወት ሞት ወደ እኔ ቢመጣ አልሰጋም ምክንያቱም የምቀምሰው ጽዋ ክርስቶስን ራሱን ይሰጠኛል። ስለዚህ አንዳችም አልሰጋም።» በማለት መለሰለት። እነዚህ ቃላት በእሥረኛ ጠያቂው በማርቆስ ልብ ውስጥ በጽኑ ጠነከሩ። ከብዙ ዓመታት በኋላ፣ በፊልጵስዩስ ላይ ስደትና መከራ በክርስቲያኖች ላይ መጣ። በዛም መከራ ውስጥ ማርቆስ የጳውሎስን ቃል በልቡ አሰበ። በዚያም ሸንጎ ተይዞ ስለ እምነቱ ሞት ቅጣትን በማርቆስ ላይ ሊያደርሱበት በተሰለፉ ጊዜ፣ ቆመና እንዲህ ብሎ ቃሉን ተናገረ፦ «በህይወት መኖሬ በክርስቶስ ውስጥ አገልግሎት እና ፍሬያማ ሥራዬ ነው። ሞት ቢመጣ ደግሞ ከክርስቶስ ጋር መኖርን የሚሰጠኝ ሕያው ድልድይ ነው። ለእኔም ይህ ደግሞ የተሻለ ነው አላቸው።…» አጠገቡ የነበሩት፣ ሊገድሉት ከሚፈልጉት መካከልም አንዳንዶች የማርቆስን እምነት ምንኛ ነው? በማለት እርስ በእርሳቸው አንጎራጎሩ። ዳግመኛም ማርቆስ የመጨረሻ የክህደት ቃልህን አስፍርና ተናገር ባሉት ጊዜ « ለእኔ ሕይወት ክርስቶስ፥ ሞትም ጥቅም ነውና…» በማለት አጠናቀቀ ንግግሩን። የማርቆስም ሞት በፊልጵስዩስ ቤተክርስቲያንም በዙሪያዋ ባሉት ሁሉ ላይ ብዙዎች ጋር ደረሰ። ብዙዎች በጽናት ተመሰረቱ፣ በዛችም ከተማ ወንጌሉ ብዙዎችን እየለወጠ ሄደ። ይሄን እምነት መርሕ አድርገው የቤተክርስቲያን አባቶች ብዙዎች እንደ ሻማ ቀልጠውበታል። ለዚህም ነው ጠርጡልያንም ሲናገር The blood of the Martyrs is the seed of the Church(የሰማዕታት ደም የቤተክርስቲያን ዘር ነው) ያለው። በአጭሩ የቻርሊ ከርክ ፖለቲካ አቋም ምንድነው? የሚል ትርጉም ሳይሆን ጽሑፉ ትኩረት የሚሰጠው በእርሱ ህልፈት ምክንያት የመጣውን ሰዎች ባሰብን ቁጥር እግዚአብሔር በቃሉ ሞትም ጥቅማችን እንደሆነ የሚነግረን። በዚህ ዘመንስ እንደ እንቁ የምናያቸውን ምሑራንን ለማጥፋት ብዙዎች የሚያቅዱት። በዚህ ሁሉ ግን እግዚአብሔር ጽኑ እምነት ሰጥቷቸው የክርስቶስን ወንጌል ለማገልገል የተሰጡ ስንቶች ይሆኑ? እንጃ፤ ለእኛ ግን እግዚአብሔር በዚህ ጽኑ እምነት ይባርከንም።

የማርቆስ እና እስረኛው ታሪክ Read More »

የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት

ክፍል 1 “እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤”  — ፊልጵስዩስ 2፥6 (አዲሱ መ.ት) አንድ አካል አምላክ ነው የሚባለው ወይም እንደ አምላክ ሊመለክ የሚገባው አምላክ ነኝ ብሎ ስለተናገረ ብቻ ወይም ብዙዎች አምላክነቱን ስላወጁለት አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አምላክ ነኝ ብለው የተነሱ ነገሥታትን እንመለከታለን። ለምሳሌ፦ የጢሮስ ንጉስ እኔ አምላክ ነኝ ማለቱን(ሕዝቅኤል 28፥2-9) ስንመለከት ይህ ንጉሥ እኔ አምላክ ነኝ ስላወጀ ብቻ አምላክ ነው ብሎ መፈረጅ ፈጽሞ አይቻልም። በሰውም አጀብ አንድ አካል አምላክ ስለተባለም አምላክ ሊሆን አይችልም። ምክንያቱም የግሪክ ጣዖታት እንዲሁ ተብለው ምንነታዊ ለውጥ ስላላሳዩን። ክርስቶስ ኢየሱስ አምላክ ለመሆኑ የአምላክነት ግብሩን፤ ባህሪዎቱንና ሐልዎቱን በተለያየ መንገድ መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር፤ ኑባሬውን ሲተርክና ሲገልጽልን እንመለከተዋለን። ከእነዚህም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ውስጥ አንደኛው የፊልጵስዩስ መልእክት ም2 ቁ6-7 ነው፦ ⁶ እርሱ በባሕርዩ አምላክ ሆኖ ሳለ፣ ከእግዚአብሔር ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም፤ ⁷ ነገር ግን የባሪያን መልክ ይዞ፣ በሰውም አምሳል ተገኝቶ፣ ራሱን ባዶ አደረገ” ፊልጵስዩስ 2 (አዲሱ መ.ት) ὃς ἐν μορφῇ θεοῦ ὑπάρχων οὐχ ἁρπαγμὸν ἡγήσατο τὸ εἶναι ἴσα θεῷ, Προς Φιλιππησιους 2:6 በጽርዑ ሞርፌ/μορφῇ የሚለው ቃል ኑባሬያዊ መገኘትን፣ ሁናቴን ወይም ባህሪዎተ መልክን የሚገልጽ ቃል ሲሆን ክርስቶስ ኢየሱስ (ወልድ) እም ቅድመ አለም በኑባሬው በባህሪዎተ መልኩ ራሱ አምላክ ሆኖ የሚኖር አካል እንደሆነ ይገልጻል። በተጨማሪም በባለቤትነት ሙያ (Nominative case) የመጣው ሁፓርኾን/ὑπάρχων የሚለው ቃል በአሁን ጊዜ አመልካች ግስ(Present participle tense) መምጣቱ ወልድ ከዘላለም ጀምሮ ከአብ ጋር አብሮ ህያው አብሮ እኩል አብሮ ዘላለማዊ እንደሆነ በሚገልጽ መልኩ እንደመጣ የክፍሉን ሰዋሰው ይነግረናል። ይህም ደግሞ ለወልድ ኑባሬ ጅማሮ አለው ፍጡር እንጂ ፈጣሪ አይደለም ለሚሉት አርዮሳውያን እና ኢብዮናውያን (Ebionite/Ἐβιωναῖοι) በተለምዶው አዶፕሽኒስቶች የሚባሉት የምን*ፍቅና የአስተምህሮቶችን መሰረታቸውን የሚንድ ክፍል ነው። ሙግታችንን ጠበቅ ለማድረግ ያክል ከተመለከትን ደግሞ ወልድ አምላካዊ ባህሪ ከጥንተ ዘላለም ጀምሮ በዚሁ መልክ ሲኖር የነበረው አምላክ ወደ ፈጠራት ጠባበ አለም የሰውን ወይም የባሪያን ባህሪ(መልክ) ይዞ መምጣቱ “ከእግዚአብሔር አብ ጋር መተካከልን ሊለቀው እንደማይገባ አድርጎ አልቈጠረውም” በማለት ብርሃነ አለም ቅዱስ ጳውሎስ ፍንትው አድርጎ የወልድን መለኮታዊ ባህሪዎት ከእግዚአብሔር አብ ጋር እኩል እንደሆነ ያሳየናል። ከአምላክ ጋር እኩል መሆን ወይም በጽርዑ ቶ ኢናይ ኢሳ ቴኦ/τὸ εἶναι ἴσα θεῷ የሚለው ሐረግ እግዚአብሔር ወልድ ከእግዚአብሔር አብ ጋር በባህሪው እኩል ወይም አንድ አይነት ሆሙስዮስ/ὁμοούσιος እንደሆነ በግልጽ ሁኔታ ሲነግረን የአርዮሳውያንን መርሆተ ቃል የሆነውን ተመሳሳይ ወይም ተቀራራቢ ባህሪዎት ሆሞዮስዮስ/ὁμοιούσιος የሚለውን ምንፍቅና አፈር ከመሬት የሚደባልቅ ክፍል እንደሆነ እንመለከታለን። በቁጥር ሰባትን አንድ በአንድ ስንመለከተው “የባሪያን መልክ ይዞ” የሚለው ሐረግ በፊት የተገለጠበት ቅድመ ኑባሬያዊ ባህሪዎት እንደነበረው ቁልጭ አድርጎ ያሳየናል፤ እርሱም በቁጥር 6 ላይ እንዳየነው የወልድ አምላካዊ መልክ (ባህሪ) ከጥንተ ዘላለም ጀምሮ ገንዘቡ የሆነ ምንነት ነው። “በሰውም ምሳሌ ሆኖ” የሚለው አገላለጽ ደሞ ወደ ምድር በመጣ ጊዜ ፈጣሪ በፍጡራን ምሳሌ ሆኖ ሰዋዊ ባህሪዎትን እንደተላበሰ ያሳየናል። ቀጥሎም “ራሱን ባዶ አደረገ” የሚለው ደሞ አንድ ነገር ባዶ ሆነ የሚባለው ያ ነገር መጀመሪያውኑ የሆነ ነገር ሲኖረው ነው። ክርስቶስ ኢየሱስ ደግሞ ራሱን ባዶ አደረገ ሲባል አምላካዊ ሙሉነት የነበረው አካል ወደ ፈጠረው፣ ወዳዘጋጀው፣ ሰዋዊ ባህሪዎት ዝቅ ብሎ በመምጣቱ ነው። ስለዚህ ክርስቶስ ኢየሱስ ሰው ሁኖ ከመምጣቱ በፊት በአምላካዊ ሙሉነት የሚኖር አምጻኤ ኩሉ አምላክ እንደሆነ እንመለከታለን። በመጨረሻም የክርስቶስን አምላክነት የማያምኑ እንዲህ ሲሉ፦”…ክርስቶስ ኢየሱስ (ወልድ) በእግዚአብሔር ወይም በአምላክ መልክ መኖሩ አዳም በእግዚአብሔር መአልክና ምሳሌ በተፈጠረበት ሒሳብና ቀመር ነው…” ይሞግታሉ። ነገር ግን የሁለቱን ክፍሎች የጽርዑን የቃላት አገባብ እና አውዳዊ ምልከታ ባደረግን ጊዜ ፈጽመው የየቅል ሐሳብ እንደሆነ እንረዳለን፦ እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር/καὶ εἶπεν ὁ θεός Ποιήσωμεν ἄνθρωπον κατ᾽ εἰκόνα ἡμετέραν καὶ καθ᾽ ὁμοίωσιν…>>  — ዘፍጥረት 1፥26 በዘፍጥረት 1፥26 መልክ ብሎ የገባው የግሪኩ ቃል ኤይኮና/εἰκόνα ሲሆን ምሳሌ የሚለው ደሞ ሆሞዮሲን/ὁμοίωσιν በሚለው የቃላት አገባብ እንደተሰደረ እንመለከታለን። ኤይኮና/εἰκόνα የሚለው ቃል ኤይኮን/εἰκών ማለትም ምስለ መልክን መመሳሰል ወይም መቀራረብ(በውጫዊ ማንነት መገለጫ) የሚል ትርጉም አለው። እግዚአብሔር አምላክ ሰውን በእኛ መልክ(ኤይኮና ሄሜቴራን/εἰκόνα ἡμετέραν) እንፍጠር ሲል በጽድቅና ቅድስና(ኤር 4:24)፤ እንዲሁም በመገንዘብ ችሎታንና እውቀትን(ቆላ 3:10) የመሳሰሉትን የምስስሎሽ መገለጫዎች በሚገልጽ አገባብና አግባብ መምጣቱ ቅብል ነው። ነገር ግን የሰው ልጅ በእግዚአብሔር መልክና አምሳል መፈጠሩ በእርግጥ የሚካፈለው ባህሪ እንዳለው ሁሉ የማይካፈለው ባህሪ አለ። በዛው በፊልጵስዩስ መልእክት 1:7 እና 2ኛ ጴጥሮስ 1፥4 ላይ የእግዚአብሔር የባህሪው ተካፋዮች እንደሆንን ይናገራል፦ “ስለ ክፉ ምኞት በዓለም ካለው ጥፋት አምልጣችሁ ከመለኮት ባሕርይ ተካፋዮች(κοινωνοὶ φύσεως) በተስፋ ቃል እንድትሆኑ፥ በእነዚያ ክብርና በጎነት የተከበረና እጅግ ታላቅ የሆነ ተስፋን ሰጠን።”2ኛ ጴጥሮስ 1፥4 ተካፋይ ወይም በግሪኩ ኮይኖኖስ/κοινωνός የሚለው ቃል የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ፈጽሞ የማይካፈለው ወይም የቀረበት ነገር እንዳለ አመላካች ነው። ይህንን ሐሳብ በሌላ ክፍል በስፋት እንመለከተዋለን። ነገር ግን ክርስቶስ ኢየሱስ ከእግዚአብሔር አብ ጋር የማይጋራው ሆነ የማይካፈለው ባህሪ የለም። ከላይ በፊልጵስዩስ መልእክት 2:6 ከአብ ጋር በመለኮተ ባህሪዎት እኩል ወይም አንድ እንደሆነ ተመልክተናል። ስለዚህ አምላክ ክርስቶስ ኢየሱስ በአምሳለ ሰውነት መገለጡ (እንደ ሰው መብላት መጠጣቱ፤ መተኛት መነሳቱ፤ መወለድ ማደጉ ወዘተ) መለኮታዊ ክብር እንደሌለው የሚያሳየን ተግባር አይደለም። እርሱ ወደዚች ወደ ፈጠራት አለምና ሰውነት ከመገለጡ በፊት አምላካዊ ምንነት፤ ክብርና መለኮታዊ ኑባሬ ከጥንተ ዘላለም ጀምሮ ገንዘቡ ያደረገ ኃያል አምላክ ነው።

የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክነት Read More »

ንጉሥ ሄነሪ ስምንተኛ እና የአንግሊካን ቤተክርስቲያን?

ክፍል አንድ አብዛኛውን ጊዜ በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ላይ ከሚነሱ ትችቶች መካከል ትልቁን ሥፍራ የሚይዘው የንጉሥ ሄነሪ ስምንተኛ(Henry VIII) ትዳር መፍረስ ምክንያት የእንግሊዝ ቤተክርስቲያን በዛ መንሥኤ የተጀመረች አድርጎ መሞገት ነው። ይሄ ደሞ የቤተ ክርስቲያንቱን ታሪክና አስተምህሮን በአግባቡ ካለማወቅ የሚነሳ ትችት ተደርጎ በብዙ ምሑራን ዘንድ የሚወሰድ ነው። ከክርስትና ውጭ ያሉ ሃይማኖታዊ ድርጅቶች(ሙስሊሞች፣ አርዮሳውያን፣ ሰባልዮሳውያን…) ክርስትና የጀመረው በንጉሥ ቆሰንጠንጢኖስ ነው ከሚል የአፈ ታሪክ የማይለይ ሙግትና በብዙ የተወሳሰበውን የታሪክ፣ የፖለቲካ እና የሥነ መለኮት እይታን ለማቅለል የሚሞከር ከንቱ ትግል ነው በማለት መግለጽ ይቻላል። በዚህ ጽሑፍ ደግሞ ከመጀመሪያው የንጉሥ ሄነሪ ስምንተኛ እና የንግሥት ካትሪን ትዳር ለመመልከት እንሞክራለን። የንጉሥ ሄነሪ ስምንተኛ ታላቅ ወንድም የነበረው አርተር በ1501 ካትሪንን አገባ። አምስት ወር ባልሞላ ጊዜ ውስጥ በሕመም ምክንያት ይሞታል። ያገባትም የ16 ዓመቷ ልጃገረድ ንግሥት ካትሪን ባልቴት ትሆናለች። የንግሥት ካትሪንንና የልዑል አርተር ጋብቻ በስፔንና እና በእንግሊዝ መሃል ጥሩ የሆነ ፖለቲካዊ ግንኙነት ፈጥሮ ነበር። ንጉሥ ሄነሪ ስምንተኛም ይህን ፖለቲካዊ ግንኙነት እንዲቀር ስላልፈለገ ካትሪንን ያገባታል። እንደ ብዙዎች ምልከታ መሠረት ዘንድ ይህ ትዳር የተሳካ አልነበረም ይባላል። ወቅቱም የህፃናት ሞት ከፍተኛ  የነበረበት ጊዜ ስለነበር ከወለዳቸው ሦስት ወንዶችና ሶስት ሴቶች ልጆች መሀል 1 ልዕልት ማርያም (Mary I “Bloody Mary”) ነበር የተረፈችው።(ስለ Mary በክፍል ሁለት በስፋት እንመለከታለን።) በዚህ ትዳር ውስጥ የሚተካውን ወንድ ልጅ በማጣቱ በትዳሩ ላይ ጥያቄ ማንሳት ጀመረ። ለዚህም ይሆነው ዘንድ በኦሪት ዘሌዋውያን 20:21፦ “ ‘ማንኛውም ሰው የወንድሙን ሚስት ቢያገባ አድራጎቱ ርኩሰት ነው፤ ወንድሙን አዋርዷልና፣ ያለ ልጅም ይቀራሉ። በሚለው ቃል ላይ በመመስረት የወንድሙን ሚስት በማግባቱ እንደተረገመና ትክክለኛ ጋብቻ እንዳልሆነ በ1527 ዓ.ም ለሮማን ካቶሊክ ቤተክርስቲያን እና ለፖፕ ቀለሜንጦስ ሁለተኛ በጥያቄ መልክ ማቅረብ ጀመረ። እዚህ ታሪክ ላይ ልብ ልንለው የሚገባን ነገር ቢኖር በአንግሊካን ቤተክርስቲያን ሆነ በሮማን ካቶሊክ ፍቺ እንደማይፈቀድ ነው። ነገር ግን የንጉሡ ሄነሪ ስምንተኛ ጥያቄ የፍቺ ጥያቄ ብቻ አልነበረም ጋብቻው መጀመርያውኑ ትክክለኛ ጋብቻ ነው ወይ የሚል ነው ።(annulment ‘a legal procedure within secular and religious legal systems for declaring a marriage null and void’) በዚህም የጋብቻውን ትክክለኛነት ጠይቆ ትክክለኛ አለመሆኑ በሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያኗ ህግ ከተረጋገጠ ጋብቻው መጀመሪያውኑ ትክክለኛ አይደለም ተብሎ ሊወሰንለት ይችላል። ለዚህም በተለያዩ ጊዜያቶች በሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ይህ ስርዐት ሲተገበር ታይቷል። ለምሳሌ ታዋቂው አሜሪካዊው ፖለቲከኛ ቴድ ኬኔዲ(Ted Kennedy) በጋብቻው ወቅት ታማኝ አለመሆኑን አምኖ የሃያ አራት ዓመት ጋብቻውን በሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ፊት ትክክለኛ ጋብቻ እንዳልነበር ተቆጥሮለት ተለያይተዋል። ሌላኛው ደግሞ ዮሴፍ ኬኔዲ  ሁለተኛ(Joseph Kennedy II, 2007 እ.ኤ.አ) እና ታዋቂው ፈረንሳያዊው ገዥ ናፖሊዮ ቦናፓርቲ እና የንጉሥ ኤድዊግ(Eadwig 959 እ.ኤ.አ አካባቢ) ለዚህ ታሪክ ተጠቃሽ ናቸው። ነገሩን ለየት የሚያደርገው ደግሞ በዚህ ዘመን እንደሚታወቀው አይነት ፍቺ በመካከለኛው ዘመን በነበሩት ሰዎች ዘንድ አልነበረም። የጋብቻን ትክክለኛነት ማረጋገጥ እና በመጀመሪያውኑ ጋብቻ እንዳልነበር ማስመስከር (Annulment / Declaration of Nullity) የተለመደ ነበር። በዚህም ዘመንም የሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን በህግዋ ውስጥ ይህ ጋብቻ ነው ለመባል ማሟላት ያለበትን ነገሮች በዝርዝር ተቀምጧል።(the code of canon of law 1095-1107) ለምሳሌ ያህል ሁለቱም ተገቢዎች በፈቃዳቸው መሆን አለበት ቤተሰብ(የደም ዝምድና) ያላቸው መሆን የለባቸውም። ማንኛውም ክህነት የተቀበለ መሆን የለበትም (ቄስ ,ጳጳስ)  የመሳሰሉትን ህጎች የያዘ ነው። ስለዚህ የንጉሥ ሄነሪ ስምንተኛ ጥያቄም ከዚህ የተለየ አልነበረም። ለጋብቻው ትክክለኛ አለመሆን እንደ ምክንያት አድርጎ ያስቀመጠው ነገር፦ የወንድሙን ሚስት ማግባት ትክክለኛ ጋብቻ አይደለም በመፅሐፍ ቅዱስ ህግ ጋር ይጋጫል። የወንድሙን ሚስት በፖፕ ጁሊየስ ሁለተኛ ፈቃድ(papal Dispensation) ማግባቱ ትክክል አይደለም። ንግሥናውን የሚተካ ወንድ ልጅ አለማግኘቱን እንደ እርግማን ይቆጥረው ነበር። እነዚህን እንደ ምክንያት አድርጎ በማቅረብ ለፖፕ ቀለሜንጦስ ሁለተኛ ጥያቄውን አቀረበ ነገር ግን የጠበቀው መልስ በተቃራኒ ሆኖ ይህን ሊፈቅድለት አልወደደም። ምክንያቶቹም ተብለው የሚነሱት፦ አንደኛ፦ የንጉሥ ሄነሪ ሚስት ካትሪን በጊዜ ኃያል የሚባለው የሮማን ገዢ የሆነው የስፔን ንጉሥ የቻርለስ አምስተኛ አክስት(Holy roman Empire) ስለ ነበረች ነበር።ንጉሥ ሄነሪ ጥያቄውን ባቀረበበት በ1527 በዛው ዓመት በቁጥር ከሃያ ሺ የሚበዙ ደሞዝ ያልተከፈላቸው ወታደሮች(አስራ አራት ሺህ የሚሆኑ ጀርመናዊ ሉተራውያን ወታደሮች እና ስድስት ሺህ ስፔናውያን እና ጣሊያንናዊ ወታደሮች) ንቅናቄ የሮማን አገዛዝና ያደከመ፣ ከሃምሳ አምስት ሺህ ወደ አስር ሺህ የሮም ህዝቡ ቁጥር የቀነሰበት፣ እስከ ሁለት መቶ የሚሆኑት ወታደሮች ፖፑን ለመጠበቅ የሞቱበት፣ ፖፑም በአማፅያኑ እጅ ገብቶ በእስር የነበረበት ጊዜና መንበረ ጴጥሮስ በትልቅ ሀዘን ውስጥ የሆነበትም ጊዜ ነበር። ከዚህም ክስተት(the sack of Rome 1527) ዘጠኝ ወር ያህል ፖፑ ታግተው ከቆዩ በኃላም ከገበሬዎች ጋር በመመሳሰል ያመለጡበት ጊዜ ነበር። በዚህ መሐልም ግን የንጉሥ ሄነሪ የጋብቻ ጥያቄ አልተመለሰም ነበር። ጋብቻውን ትክክለኛ አይደለም ቢሉ በዚያን ጊዜ የሮማን ንጉሥ የነበረው ቻርለስ አምስተኛ ስለሚያስተዳድሩአቸው ከእርሱ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ስለሚያሻክር ፈርተውም ነበር። ሁለተኛው፦ ምክንያት ንጉሥ ሄነሪና ካትሪንን ያጋባው የቀድሞ ፖፕ ጁሊየን ሁለተኛ ስለነበር የእሱን ስልጣን መቃወም ስላልነበረበት ነበር። ሦስተኛው፦ ምክንያት ደግሞ ካትሪን ከአርተር (ከንጉሥ ሄነሪ ወንድም) ጋር በጫጉላ ወቅት ስጋዊ ተራክቦ አልነበረንም ማለቷ ነው። ጋብቻ የሚፈፀመው በስጋዊ ተራክቦ ነው ተብሎ ስለሚታመንም ካትሪን የመጀመሪያ ጋብቻዋ ወቅት ስጋዊ ተራክቦ ካልነበር ከንጉሥ ሄነሪ ያላት ጋብቻ ትክክለኛ ይሆናል። ሆኖም እርሱዋ ይህንን ብትልም የልዑል አርተር የቅርብ ጓደኞች ግን ከእርሷ በተቃራኒ ቆመው ነበር የተናገሩት። በዚህ ምክንያት ለንጉሥ ሄነሪ አለመፈቀዱ ንጉሡን አስቆጥቶታል። ስለዚህም በ1534 ዓ.ም እራሱን በእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን ዋና የቤተ ክርስቲያን የበላይ ሃላፊ አድርጎ በመሾም ከፖፕ ቀለሜንጦስ ሁለተኛ ቤተ ክርስቲያኒቱን ለያት። ንጉሡ ራሱን የቤተክርስቲያን የበላይ አድርጎ በሾመበት ወቅት ብዙ ቢሾፖች ዲያቆናቶች እና መነኩሴ በመቃወማቸው ምክንያት በእምነታቸው ሰማዕታት ሆነዋል። በ1538 ዓ.ም ፖፕ ጳውሎስ ሶስተኛ ከሮማን ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አወገዘው(excommunicate) ተደረገ። ከዚያም በዚህ ሁኔታ ውስጥ እያለ ከአርክ ቢሾፕ ቶማስ ክራመር ጋር በመሆን ደግሞ ጋብቻ ትክክለኛ እንዳልሆነ አጸደቀ። ግን ብዙም ሳይቆይ ደግሞ በ1533 አናን አገባ። የሄነሪ ጋብቻ ታሪክ በዚህ አያበቃም እስከ ዘመኑ መጨረሻ ድረስ ስድስት ሚስቶች በተለያዩ ምክንያቶች ነበሩት። ቢሆንም ዘሩን የሚተካ ልጅ ከኤድዋርድ ውጭ አላገኘም ነበር። ኤድዋርድን ቢተካውም ስድስት አመት ከገዛ በኋላ በ15 ዓመቱ በህመም ሞቷል። በዚህ ሁሉ ታሪክ በስተ መጨረሻም ግን ልንረዳው የሚገባው የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያን በንጉሥ ሄነሪ ጊዜ ፕሮቴስታንት እንዳልነበረችና ሄነሪ ካቶሊክ እንደ ነበር። ሉተርንም የሚቃወም ጽሑፍ “ሰባቱ ቅዱስ ምስጥራት መከላከያ”(Defense of the Seven Sacraments/Assertio Septem Sacramentorum) በማለት ጽፎ የነበር መሆኑን ማወቅ አለብን። በዚያም ከፖፕ ሊዮ ኤክስ በ1521 ዓ.ም “የእምነት ጠባቂ”(“Defender of the Faith”) የሚል ስም ተሰጥቶት ነበር። በዚህም ካቶሊክ ሆኖ ነበርም የሞተው። በንጉሥ ሄነሪ ጊዜ በአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን ንግሡ መጥቶ የአስተምህሮ ለውጥ በምንም አይነት መልኩ አላደረገም ነበር። ስለዚህ አንግሊካን ቤተ ክርሰቲያን በንጉሡ ተመሥርታለች የሚለው አስተምህሮ በዚህ ውድቅ ይሆናል። ነገር ግን የአንግሊካን ቤተክርስቲያን በ597 ዓ.ም በፖፕ ጎርጎርዮስ አማካኝነት የካቲቤሪውን ቅዱስ አውግስጢኖስ ወደ እንግሊዝ በመላክ ወደ ሮም ቤተክርስቲያን ውስጥ ተጠቅልላ ባካተተቻት ከአንድ ሺህ ዓመታት በኃላ ቤተክርስቲያኒቱ ከሮም ውጭ ሆነች። ንጉሥ ሄነሪ የእንግሊዝ ቤተ ክርስቲያንን ከሮማን ካቶሊክ እንደ ቀድሞዋ መለየቱ ለተሐድሶው የማይካድ ጥቅም ቢኖረውም ነገር ግን ያደረጋቸው ነገሮች እና ሕይወቱ ሙሉውን የአንግሊካን ቤተ ክርስቲያንን ታሪክ ለመግለጽ የማይችል መሆኑን መገንዘብ አለብን። ምክንያቱም የአንግሊካን ቤተ ክርስቲያንን ለመረዳት ከዚህም ያለፈ የተወሳሰበ የታሪክና የስነመለኮት ጥልቀት ውስጥ ዘልቆ መግባት አለብን። የአንግሊካን ቤተ ክርስቲያን መልክ ማቆጥቆጥ የተጀመረው በ1536 ዓም የአስር የሃይማኖት አንቀጾች (Ten Articles) (የካቶሊክ እምነት ያለው ትንሽ በተሃድሶ ሃሳብ ተጽዕኖ ያለበት) ከዚያም 1539 ዓም ስድስት የሃይማኖት አንቀጾች (six articles of faith) (አጥባቂ

ንጉሥ ሄነሪ ስምንተኛ እና የአንግሊካን ቤተክርስቲያን? Read More »

የኒቂያ ጉባኤ እና ጥንታዊያን አበው

ለሙስሊም ሰባክያን ሙግት ምላሽ ሰሞኑን በሙስሊሞች ዘንድ በማህበራዊ ሚዲያ ሲሰራጩ ከነበሩ ሙግቶች መካከል አንዱ ተከታዩ አንድ ሙስሊም የጻፈው ጽሑፍ ነው። የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ የዕውቀቱ ልክ በጽሑፎቹ ውስጥ የሚታየው ከሆነ ራሱን የማስተማር ብቃት እንዳለው ሰው በመቁጠር ለመጻፍ መድፈሩ፤ አንባቢያኑም ደግሞ ይህንን ሙግት ከቁም ነገር ቆጥረው መቀበላቸው የሚያሳዝን ነው። ሙግቱም እንዲህ ሲል ይጀምራል፦ አብዱል በአሏህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡ 112፥3 «አልወለደም አልተወለደምም»፡፡ ጥንት ላይ የነበሩ ነቢያት እንዲሁ ኢየሱስ እና ሐዋርያት አሓዳዊያን”Unitarian” የነበሩ ሲሆን ከሐዋርያት ኅልፈት በኃላ የተነሱ የቤተክርስቲያን አበው ደግሞ በሂደት “ክልዔታውያን”Binitarian” ነበሩ። ከክልዔታውያን አበው መካከል ጠርጡሊያኖስ”Tertullian” ስለ ወልድ ሲናገር እንዲህ ይለናል፦ “አብ አጠቃላይ ባሕርይ ነው፥ ነገር ግን ወልድ የአጠቃላዩ መገኘት እና ክፍል ነው” (Against Praxeas (Tertullian), Chapter 9) መልስ የብሉይ ኪዳንን ቅዱሳት መጽሐፍት ስንመለከት እግዚአብሔር አምላክ ነጠላ አንድ ነበረ ማለት አንችልም። ለዚህም ማሳያ መጽሐፍ ቅዱስ በዘፍጥረት 1፥26 እንዲህ ይላልና፦ “እግዚአብሔርም አለ፦ ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤ የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።” የእግዚአብሔርን ሥሉስ አሓዳዊነት ከሚያመለክቱ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች መካከል አንዱ ከላይ ያነበብነው ጥቅስ ነው። እግዚአብሔር አብ ዓለማትን በልጁ መፍጠሩን (ዕብ1፥2፤ ዮሐ1፥3፤ ቆላ1፥16-17) እንዲሁም ደግሞ ፍጥረትን በማስገኘት ሒደት ውስጥ መንፈስ ቅዱስ ጉልሕ አስተዋጽኦ እንደነበረው ቅዱሳት መጻሕፍት አበክረው ይነግሩናል (ዘፍ 1፥3 ፤ ኢዮ33፥4)። በዘፍጥረት 1፥26 ላይም በብዙ ቁጥር ግስ “እንፍጠር” (נַעֲשֶׂה “ናዓሴህ”)፣ በብዙ ቁጥር ስሞች “በመልካችን” (בְּצַלְמֵ֖נוּ “ቤጻልሜኑ”) እንዲሁም “ምሳሌአችን” ( כִּדְמוּתֵנוּ ”ኪድሙቴኑ”) ማለቱ አሐዱ ሥሉስን እንደሚያመለክት በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ምሑራን የሚስማሙበት እውነታ ነው፡፡ በዚህ ርዕሰ ጉዳይ ላይ በገጻችን የጻፍነው ጽሑፍ መመልከት ይቻላል።[1] ይህ ሙስሊም ጸሐፊ ቀጠል አድርጎ የቤተክርስቲያን አበው ሥላሴያውን አልነበሩም ብሎ በድፍረት ይናገራል። ነገር ግን ይህ ፍጹም ሐሰት እና ቅጥፈት ነው። ይባስ ብሎ ጠርጡሊያኖስንም ጨምሮ የጥንት ቤተክርስቲያን አባቶች “Binitarian” ናቸው ይለናል። በዚህ ንግግሩ ጸሐፊው የቤተክርስቲያን ታሪክ እውቀት የለውም ወይም ደግሞ ሆነ ብሎ አንባቢያኑን እየዋሸ ነው ማለት ነው። ሙስሊሙ ወገናችን ላነሳው ሀሳብ ምላሽ ከመስጠታችን በፊት በትምህርተ ሥላሴ ላይ የቤተ-ክርስቲያን አበው የነበራቸው አቋም ጥርት ያለ እንደነበር እስኪ በጥቂቱ እንመልከት፦ 1) ፖሊካርፕ (Polycarp):- በ70ዓ.ም ተወልዶ በ155 ዓ.ም ወይም በ160 ዓ.ም የሞተ፣ የሐዋሪያው ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበረ ሲሆን የሰምርኔስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የነበረ ሰው ነው። ትምህርተ ሥላሴን በተመለከተ እንዲህ ይላል፦ ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ሆይ…ዘላለማዊና ሰማያዊ በሆነ ሊቀ ካህናት፣ በምትወደውና ባከበርኸው ልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለአንተና ለእርሱም እንዲሁም ለመንፈስ ቅዱስ አሁንም ሆነ ለዘላለም ክብር ይሁን[2] 2) ዮስጢኖስ ሰማዕት(Justin Martyr) ፦ በቤተክርስቲያን የእምነት ተሟጋችና አቃቤ እምነት የነበረው ይህ አባት በ100 ዓ.ም ተወልዶ በ165 ዓ.ም እንደሞተ ይገመታል። ይህ አባት በአቅብተ እምነት ጽሑፉ ላይ ትምህርተ ሥላሴን በተመለከተ እንዲህ በማለት ጽፏል፦ የዓለማት ጌታ በሆነው በእግዚአብሔር አብ፣ በመድሐኒታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ ስም በውሃ መታጠብን ያገኛሉ።[3] 3) አግናጢዮስ ዘአንጾኪያ(Ignatius of Antioch) ፦ የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ የነበረና ከ98 ዓ.ም እስከ 117 ዓ.ም መካከል ሰማዕት እንደሆነ የሚነገርለት አባት ክርስትናን ከመናፍቃን በመከላከሉ ዙሪያ ብዙ የጻፈ ዐቃቤ ክርስትና ነው። ትምህርተ ሥላሴን በተመለከተ እንዲህ በማለት ጽፏል፦ በጌታችንና በሐዋርያት ትምህርት እድትጸኑ፣ የምታደርጉት ነገር ሁሉ በስጋና በመንፈስ እንዲከናወንላችሁ፣ በእምነትና በፍቅር፤ በወልድ፣ በአብና በመንፈስ ቅዱስ፣ በመጀመሪያው እና በመጨረሻው፤ ከተወደደው ጳጳሳችሁ፣ በጎ ከሆነው የሽማግሌአችሁ መንፈሳዊ አክሊል፣  እናም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ካሉ ዲያቆናት ጋር አጥኑ። በስጋችሁም በመንፈሳችሁም አንድነት እንዲኖራችሁ ክርስቶስ ኢየሱስ ለአብ በስጋው እንደተገዛለት፣ ሐዋርያት ለክርስቶስ ለአብ እና ለመንፈስ ቅዱስ እንደተገዙ፣ እናንተም ለጳጳሳችሁ እና እርስ በእርሳችሁ ተገዙ(ታዘዙ)። [4] 4) ጠርጡሊያኖስ ወይም ተርቱሊያን (Tertullian 160-215) አፍሪካዊ ዕቃቤ ክርስትና እንዲሁም የነገረ መለኮት ሊቅ ነው። የጥንቷ ቤተ ክርስቲያን አባት የሆነው ጠርጡሊያኖስ በሥላሴያዊ አስተምህሮ ላይ ለሚነሱ ኑፋቄዎች መልስ በመስጠትና በክርስቲያናዊ ሥነ-መለኮት ከሚሰሩ አቃብያነ አባቶች መካከል አንዱ ነው። ለምሳሌ በመናፍቃን ሙግት ላይ ባነሳው በፕራክሲየስ (against praxeas) የሞዳሊዝም አራማጅ የሆነው የፓትሪፓሺያን(Patripassian) ሐሳብ አንስቶ እንዲህ ሲል በሙግቱ ላይ ጽፏል፡- ሶስቱ አብ፣ ወልድና መንፈሱ ናቸው። ሶስት ናቸው። ነገር ግን በሁናቴ አይደለም በግብር እንጂ፤ በኑባሬም አይደለም በአካል እንጂ፤ በስልጣን ወይም በሐይል አይደለም በገጽታ እንጂ ሆኖም ግን እግዚአብሔር አምላክ አንድ ኑባሬ፣ ስልጣን፣ ሐይል አለው ምክንያቱም በአካል፣ በግብርና በአይነት በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ የተገለጠ አንድ አምላክ ነውና..[5] እንግዲህ ጠርጡሊያኖስ እና ሌሎች በርካታ አበው አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ ከዘላለም ያለመሽቀዳደም እንዲሁም ያለመነጣጠል አሐዱ ሥሉስ እንደነበሩ ይነግሩናል። እንደ ሮሙ ቀለሜንጦስ(30-95)፣ ሔሬኒየስ (115-190) እና ቀጰዶቃውያን አበው (Cappadocian Fathers) ያሉ የቂሳርያው ትልቁ አባት ባስልዮስ፣ ጎርጎርዮስ ዘንዚናዙ፣ ጎርጎሪዮስ ዘኑሲስ እንዲሁም ሌሎች የቤተክርስቲያን አባቶች እንዘርዝር ብንል ትምህርተ ሥላሴን በተመለከተ በድርሳናቸው የጻፉትን እልፍ መረጃ እናገኛለን። ስለዚህ ሙስሊሙ ጸሐፊ “የቤተክርስቲያን አባቶች ስለ ሥላሴ ግንዛቤ የላቸውም ይልቅ አብና ወልድን ብቻ ጠቅሰው መንፈስ ቅዱስ ህልውና የለውም ብለዋል” በማለት “ክልዔታውያን “Binitarian” ነበሩ” በማለት በጽሑፉ ያሰፈረው ፈጽሞ ከእውነት የራቀ ነው። ይህን መሠል ሙግት ደሞ ከላይ ባስቀመጥናቸው የአባቶች ትምህርት ውድቅ ይሆናል። በመቀጠል ይህ ሙስሊም ጸሐፊ ሙግቴን ይደግፋል በማለት የአርዮሳውያንን ሙግት በመውሰድ ለመሞገት ሲጣደፍ ይስተዋላል። ሙስሊሙ ጸሐፊ ይህንን ሀሳቡን ለመደገፍ የጠቀሰው የጠርጡሊያኖስ ሥራ ከሆነው “Against Praxeas” ከተሰኘው ጽሁፍ ነው። ይህ አባት በጽሑፉም ሆነ በቃል የሥላሴን ትምህርት እውነተኝነት እየተሟገተ እና የሞዳሊዝምን (አብ፣ ወልድ እና መንፈስ አንድ ነጠላ አካል ነው ለሚሉ) ትምህርት አቀንቃኝ መናፍቃን እየሞገተ የጻፈው ጽሁፍ ነው። በዚህ ዐውደ-ጽሑፍ ጠርጡሊያኖስ የሚከራከረው በሦስት አካል ስለተገለጠው አንዱ መለኮት ነው። በምዕራፍ 9 ሙሉ አውዱ እንዲህ ሲል ይጽፋል፦ “Bear always in mind that this is the rule of faith which I profess; by it, I testify that the Father, and the Son, and the Spirit are inseparable from each other, and so will you know in what sense this is said. Now, observe, my assertion is that the Father is one, and the Son one, and the Spirit one, and that They are distinct from Each Other. This statement is taken in a wrong sense by every uneducated as well as every perversely disposed person, as if it predicated a diversity, in such a sense as to imply a separation among the Father, and the Son, and the Spirit.” “እኔ የምመሰክረው የእምነት መርህ ይህ መሆኑን ልብ በሉ። በዚህም አብ፣  ወልድና መንፈስም የማይነጣጠሉ እንደ ሆኑ እመሰክራለሁ። ነገር ግን በምን መንገድ ይህ እንደሚባል አስተውሉ።  እንግዲህ የኔ ሙግት “አብ አንድ እንደ ሆነ፣ ወልድም አንድ እንደሆነ፣ መንፈስም አንድ እንደ ሆነ፤ ነገር ግን እርስ በርሳቸውም ልዩ (distinct) እንደ ሆኑ ነው። ይሄም አገላለጽ ባልተማረ ሁሉ እንዲሁም ጠማማ አስተሳሰብ ባላቸው ሰዎች ሁሉ በተሳሳተ መንገድ ይወሰዳል። በአካላቱ[በአብ፣ በወልድ እና በመንፈስ] መካከል መለያየትን እንዳለብ በሚያመለክት መልኩ ብሎም በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ መካከል  መነጣጠል እንዳለ በማሳየት አጣምመው ይተረጉማሉ።[6] ሙስሊሙ ጸሐፊም ከላይ ጠቅሶ የጻፈው በዚህ ምዕራፍ ውስጥ የተጠቀሰ ሲሆን። ከአውዱ ውጭ ገንጥሎ በማውጣት ለአንባቢያኑ ጽፎላቸዋል። የጠርጡሊያኖስ ጽሁፍ እንዲህ ይነበባል፦ “Thus the Father is distinct from the Son, being greater than the Son, in as much as He who begets is one, and He who is begotten is another; He, too, who sends is one, and He who is sent is another; and He, again, who makes is one, and He through whom the thing is made is another……..Lord

የኒቂያ ጉባኤ እና ጥንታዊያን አበው Read More »

የባሕርዩ ምሳሌ?

በማህበራዊ ድህረገጽ ላይ ሲዘዋወሩ ከነበሩ ሙግቶች መካከል አንድ ጥያቄ ተቀምጦ ነበር። ይኼም ሙግት ኢየሱስ ፍጡር ነው ከሚል ከአንድ አርዮሳዊ በተለምዶ የይሖዋ ምሥክሮች ቤተ ጎራ የሚመደብ ነው። ኢየሱስ ፍጡር ነው ያለውም ከዚህ ጥቅስ የተነሳ ነበር ጥቅሱ እንዲህ ይነበባል፦ “እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤”  — ዕብራውያን 1፥3 ምሳሌ ሲባል ሰው በእግዚአብሔር ምሳሌ ተፈጥሯል እናም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ምሳሌ ነው። ስለዚህ ፍጡር ነው የሚል ድምዳሜን አስቀምጦም ነበር። መልስ ምሳሌ የተባለበት ምክንያት ኢየሱስ በትክክል አብን የሚገልጥ መሆኑን ለማመልከት እንጂ ፍጡር መሆኑን ለማሳየት አይደለም፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔር አብ ምሳሌ መኾኑ የተጠቀሰበት አምላክነቱን ለክርክር ሊቀርብ በማይችልበት ኹኔታ የሚገልጥ ሌላ ጥቅስ በዕብራውያን መልዕክት ውስጥ ይገኛል(ዕብራውያን 1፥2 ዕብራውያን 1፥8 እና ሌሎችም)። ከጠያቂያችን ጥቅስ ግን ተነስተን በአጭሩ መልስ እንስጥ፡- “እርሱም የክብሩ መንጸባረቅና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በስልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኃጢአታችንን በራሱ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤”  — ዕብራውያን 1፥3 “የባሕርዩ ምሳሌ” ተብሎ የተተረጎመው “ሁፖስታሴዎስ ካራክቴር” የሚል የግሪክ ሐረግ ሲሆን ካራክቴር የአንድን ነገር ትክክለኛ፣ ያልተሸራረፈ፣ ከዚያኛው አካል ያላነሰ፣ እኩል የሆነ ማንነት የሚያሳይ ነው፡፡ ይህ “ምሳሌ” ከዚያኛው አካል ጋር በኹሉም ረገድ ፍጹም ተመሳሳይ ነው ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል የሚነግረን ወልድ ከአብ ልዩ መኾኑን፤ ነገር ግን ደግሞ ከአብ ጋር ፍጹም እኩል መኾኑን ከምንም ዓይነት ጥርጣሬ በፀዳ ኹኔታ የሚገልጥ ክፍል ነው፡፡[1] ስለዚህ ይሄ ክፍል ኢየሱስ ፍጡር ነው ተብሎ የቀረበው መለኮታዊ ባሕርዩን ገላጭ እና ይልቅም አምላክነቱን የሚያሳይ ሆኖ እናገኘዋለን። ማጣቀሻ [1] Vines Complete Expository Dictionary of Old and New Testament Words, Thomas Nelson Publishers, Nashville Camden New York, 1984, P. 319.

የባሕርዩ ምሳሌ? Read More »

Scroll to Top