Author name: David Yeshua

“አንድ ታሪክ ላውጋችሁ”

ከአዲስ አበባ ወጣ ብላ በምትገኝ በአንዲት ገጠራማ አካባቢ የሚኖሩ አነስተኛ ማህበረሰብ ነበሩ። አብዛኛዎቹ የአውራጃው ነዋሪዎች ጣዖት አምላኪያን የነበሩና ስለ እግዚአብሔር መኖር የማያቁ የሆኑ እንደዋዛ የሚታለፉም አይደሉም። በዛ መካከል እውነትን የሚያቁ ጥቂት ክርስቲያኖች ግን አልጠፉም ነበር፡፡ ያው ጭስ ባለበት ጥቂትም ቢሆን እሳት አይጠፋም እንደሚባለው ተረቱ አንዳንድ ቦታዎች ላይ ሰፍረው ነበር።(ከዛ በፊት ሚሶናውያን በስፍራው ተልከው ወንጌልን ያደረሱ የነበሩ ይመስላል።) በጥልቀት በማህበረሰቡ ጫና ምክንያት ግን ወንጌልን ባለማድረሳቸው ብርቱ ክርስቲያን እንቁጠር ብንል እንደ ቦዘና ሽሮ ጥቂት ሥጋ ጣል ጣል ይመስል በትግል ነው የምናገኘው፡፡ (ያው ቦዘና ስለምወድ ምሳሌ ተጠቀምኳት፤ የምትወዱ ሰዎች ካላችሁ ከአፍቃሬ ነኝ ለማለት ነው)። በአንድ ወቅት እኒያ ወንጌልን የሰሙት ሰዎች ላልሰሙ ሰዎች ለማድረስ ለሁለት ተከፍለው ለጣዖት አምላኪውና አንዱ ወገን ደሞ አምላክ የለም(እግዚአብሔርን ለማያቀው) ተበታትነው በአንድነት ማሰራጨት ጀመሩ። በማህበረሰቡ መካከል በብዙ ታወቁ፣ ክርስትና ከዛች መንደር አልፎ ቀያቸውን ሙሉ አጥለቀለቀው፡፡ የዚህ ሁሉ ብርታትና የአንድነታቸው ምክንያት ለቤተክርስቲያን ቀናኢ ሀሳብ አለን ማለታቸውና አንዱ በአንዱ ስራ ጣልቃ ሳይገባ፣ ሳይንቅ፣ የሚሰራውን አገልግሎት ሳያሰናክልና ክፉ ሳያስብ አንድነትን ስለመረጠ ነበር። የሆነው ሁሉ ግን በአንዲት ክፉ ቀን ይሄ አንድነት ብዙ ርቀው እንዳይሄዱና ተሰናክለው እንዲወድቁ አደረጋቸው፡፡ የሰላሟ መንደርም ሁከት ተጀመረ። ለዚህ ሁሉ ጉስቁልና መንስኤ ክፋት ማሰባቸው ነበር። በተጨማሪም ሐዋርያው ጴጥሮስ በክታቡ እንዲህ ያለውን መዘንጋታቸው ነበር፦ “እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።” 2ኛ ጴጥሮስ 1፥7 እግዚአብሔርን ምሰሉ በተባሉበት ቦታ ይልቅ የራስን ፍላጎትን በሰዉ ዘንድ መሳላቸው፣ ከአሻጥር ይልቅ መዋደድን ሳሉ በተባሉበት ቦታ ላይ የእኔ ወንጌል በላጭ የእግዚአብሔሩ ሀሳብም በእኔ ተገልጧልና ፍቅር እኔ ጋር ነው፤ የእርሱ ወንጌል እንዲህ…በማለት ለማህበረሰቡ አልባሌ ስብከት ማሰማት ጀመሩ። ይሄ ነበር የውድቀታቸው ምክንያቱ፡፡ ታሪኩ በዚህ አላበቃም ቢያበቃማ ጥሩ ነበር፤ እነዚያ ወንጌል የሰሙ ያመልኩበትም የነበረችው ቤት በዚህ ሽኩቻ ወደቀች፣ የመንደሪቷ ቤተክርስቲያን ፖለቲካ ስለያዛት ተናደች፣ የአንዱን ግለሰብ ትችት ለገሃዱ ዓለም መናገር የሚያመጣውን ጦስ ስላልተገነዘቡ ጣዖት አምላኪያኑ ወደ እጣናቸውና ደም ማፍሰስ፤ አምላክ የለሾቹ ወደ ቁዘማቸው ገቡ፡፡ ይሄን ሁሉ ታሪክ ያነበብክ አንባቢዬ የነገሩ መጎሳቆል ለምን የሆነ ይመስልሃል? እንዲያ እንዲህ ብለህ ልታብራራ ከቻልክ ጥያቄው ላንተ በዝርዝር ከታች ላስቀምጥልህ፦  ➞ የክርስቲያኖቹ እንዲያ መሆን መንስኤው ምንስ ይሆን? ➞ በዚህስ ዘመን ምን እየሰማህ ይሆን? ➞ በዚህ ታሪክ ላይ ቀይራለሁ ብለህ ምታስበው ነገር ይኖር ይሆን? ኦኦኦ….ጥያቄማ አላብዛ ይቅር፤ ይሄ አጭር ማስታወሻዬ ጽሑፍ ለካ ብዙ ጥያቄ ያግዳል..! ጽሑፏም ጣፍጣ ለአንባቢያን በአጭሩ አትቀርብ ይሆን በሚል አሳጥሬዋለሁ፡፡ አድማጬና አንባቢዬ ሆይ..! ስትመልሳቸው ሐዋሪያው ጨምሩ ማለት ምን ማለት ይሆን? የምትለዋን ነገር ባትረሳት ጥሩ ነው፡፡ ጨረስኩ እያልኩ ቀጠልኩ አይደል ጨርሻለሁ።[2] 1] ሰሞናዊውን የክርስቲያን ማህበረሰብ ሁኔታ ስንመለከት ይሄ ታሪክ ለመጻፍ ተነሳሁ። ከእግዚአብሔር አገልጋይ ሆነው ግን በእግዚአብሔር ዓለም ውስጥ የሌለን ማንነት ለማሳየት፣ ለማጉላት መሞከራቸውን ሳይ እግዜሩ ይፋረድ አልኩና ይሄን አጭር ታሪክ በአጭር ማስታወሻዬ አካተትኩላችሁ። 2] በመጨረሻም ይሄን የጽሑፍ ልጥፍ ለማለት የፈለገውና የተነገረው ሳይገባህ ቅርጫፉን ይዘህ በደፈናው የምትቆጣ፣ ምዕመኑን ጨፍላቂና እብሪተኛ መጋቢ ሆይ….! ቤተክርስቲያን ላይ መንግስት ለመሆን የምታስቡም ጭምር ካላችሁ…! ይቺ አጭር ፖስት ለእናተ ትቀርብልኝ ዘንድ አሳሰብኩ። እግዚአብሔር በዚህ ዘመን ከምንሰማው ነገር ሁሉ ይጠብቀን። አሜን።

“አንድ ታሪክ ላውጋችሁ” Read More »

ይገርማል…ይደንቃል….!

ድንቅ ነው!! አምላክ ሥጋን ለብሶ ወደ ምድር መጣ የሃጥያት መከራችንንና የዲያቢሎስ የሹፈት ነጋሪት ዝም ለማስባልም ተገለጠ። ነገር ግን የእኛን መከታን ነፃ አውጪያችንን፦ በአክሊል ፋንታ የእሾህ ጉንጉን፣ በፍቅር ከማቀፍ ፋንታ ሰጠነው ጅራፍ፣ በእጆቻችን። እሱም አልበቃ ብሎ አዳኙን ራሱን ራስህን አድን አልነው፤ ሙሾ በሚመስል ቅላጼ እያላገድን አሾፍንበት፤ ከዛም ብሶ ሰቀልነውም በእንጨት በችንካር አድርገን። ይሄ ሁሉ ሆነና ጀንበርም ሳትጠልቅ፣ ፀሐይም ሳትገባ ሥራው ድንቅ ነው የሚል ድምጽ ሰማይ ምድር ሁሉ መወደስ ጀመረ። የጩኸቱ ድምድምታ ምን ይሆን? ብለን ተነሳን፤ እኛም ያኔ ጎኑን የተወጋው፣ እጆቹም ተቸነከሩ፣ ሄዷልና ሞቷል የተባለው አዳኙ ራሱ ያው መሢህ መሆኑን አወቅን። በፍርሃትም ያየነውን በመገረም ድንቅ ነው አልን። ከእላፋት ጋር አእላፋት ሆነን፥ ባሾፍንበት ከንፍራችን ከሙታን በኩር፣ የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ፣ የምድር ሁሉ ባለቤት እርሱን አመሠገንን። ጨመር አድርገንም ተነስቷል በዚህ የለም መቃብሩ ባዶ ነው ተመልከቱ በዚህ የለም፤ በሚል ክብሩ ሁሉ በአርያም በምድር ይሁን ስንል ጣፋጭ መዓዛ ያለውን ዝማሬ ለታረደው በግ አቀረብን። ለአንባቢው መልዕክቴ በዚህ ወቅት ላይ የጥሞና ጊዜ ያጣህ እና ረፍት የሌለህ ሆይ “እርሱ ሰላም የሚሰጥ እረፍት ነውና በልብህ ታስገባው ዘንድ አሳሰብኩህ”። አሜን።[፩][፪][፫] መልካም የጥሞና ጊዜ ይሁንላችሁ…..! [፩] ከሚባለው በላይ ከደረሰበት መከራ አንጻር ይገርማል ጥቂት ሆና ትታየን ዘንድ አንባቢው ያስተውል። [፪] ይደንቃል ስንል ከእውነት የሆነ መደነቅ እንዲሆን ሰሚው ከንግግል ባለፈ ከልብ በኾነ ፍቅር ትል እንደሆን አሳሰብኩህ። [፫] ምንጭ፦ አጭር ማስታወሻ በወንድም David Yeshua, ያልታተመ በጽሑፍ ላይ ካለ መጣጥፍ የተወሰደ።

ይገርማል…ይደንቃል….! Read More »

ሆሣዕና <አሁን አድን….!>

ደጉ ጌታ መጣ ተገለጠ ሰዎችም ተቀበሉት። ከተቀበሉት መካከል ሰው ብቻ ሳይሆን ከምድር ፍጥረታት መካከል ያለች አንዲት ውርጭላ ከአህያይቱም ጋር ነበረች። አህያይቱም ተነሳች ክብሯን አየች፣ ንጉስም ተቀመጠባት፤ አምላክ ሥጋን ለብሶ መጣ ወደ ምድር አቤቱ ዛሬ አድን ሆ…ሆ ብለን ሆሣዕና[፩] እንድል። የቀደመው ተተንብዮ የነበረው ትንቢቱ ተፈፀመ ሆ…! እያልን ከተገኘው የዘንባባ ዝንጣፊ ከእግሩ ሥር እያቀረብን። ንጉሡም ተራመደ[፪] አለፈ የትንቢቶቹ ምጻሜ ሊቃረብ ሆነ…! ይኼን ለመረዳት ጥሞና መውሰዱ ሳያሻን አይቀርም ከበፊቱ ይልቅ ሆሣዕና እንድልን።   መልካም የጥሞና ቀን እና ምሽት…! [፩] ሆሣዕና|Hosanna፦ ዋሴ ና፣ አዳኜ ና፣ ጠባቂዬ ድረስ ማለት ነው። ‘ዋስ’ እና ‘ና’ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ቃል ነው።[…አድነን፡ እባክኽ አድነን…መድኅኒትነት፤ መሆን ወይም መባል።] [፪] ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ህጻናት ካዜሙት ቃል፥ ሆሣዕና ፥ “…ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።” (ማቴ 21፡9)

ሆሣዕና <አሁን አድን….!> Read More »

“ጣዕመ ዜማ የሌለው እንቢተኛ ልብ…!”

መናፍቃን እና እንቢተኛ ልብ አንድ ናቸው። ሁለቱም ስተው ሳሉ ጭብጨባ ይሻሉ፤ መናፍቅ ሁሌ የሳተ ስለሆነ ከቅዱሳት መጽሐፍት መውጣቱ በቀላሉ ያሳብቅበታል። እንቢተኞቹ ግን ተበጥረው ከመናፍቃኑ መለየቱ የሰሚው ድርሻ ነው። በዚህች አጭር ጽሑፍ ግን የምታደምጥ እና የምትሰማ አንባቢ ሆይ ዕቡይ[፩] ልብ ያላቸውን ሰዎች በዚህ ለያቸው፦ “የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ ቃናው ጠፍቶባቸው፤ አቃቢነ ክርስትና ዕቡይ ሰው ልሁን ልደመጥ ማለታቸው መሠረታዊ መለያቸው ነው። በመጨረሻም አንባቢ ሆይ..! ያው ዕቡይ ዕቡየ ልብ ነው። ዕቡየ መንፈስም።[፪] እኒህን ዕቡያን ከመናፍቃኑ ለመቆንጠር ቢያዳግትም…. ሥነ-ምግባራቸውን በሚያስተምሩት አስተምህሮ ከቅዱሳት መጽሓፍት እና ከቤተክርስቲያን ትምህርት አፈንግጦ ወጥ መሆናቸውን በጩኸቱ፣ በሥነ-ምግባሩ እና በሚያደርገው ክዋኔ ለክተህ ታውቅ እንደሆነ እወቅ።[፫] [፩] በቁሙ ትቢተኛ፣ ኵሩ፣ ልቡ ያበጠ፣ የተነፋ፡፡ ምንጭ፤ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ) [፪] ኦ ዘያነብብ!! በእለ ምግባሮሙ ወበስብከቶሙ እም ቅዳሳት መጻሕፍት ወ ትምህርተ ቤተክርስቲያን አእምር ከመ ለሊሆሙ ውጉዛን ውእቶሙ! [፫] Tertullian,De praescriptione haereticorum (On the prescription of heretics), Chap. 43፡ You can judge the quality of their faith from the way they behave. Discipline is an index to doctrine. [፬] Erasmus, Paraphrase On Matthew, Chap. 7፡ “If you observe their lives and character more attentively, you will find them to be self-pleasing, everywhere serving their own advantage, arrogant, vindictive, envious, disparaging, thirsting for glory, often both devoted to their bellies and acting completely in their own interests, rather than in the interest of the flock or of the gospel.”

“ጣዕመ ዜማ የሌለው እንቢተኛ ልብ…!” Read More »

የቀድሞ ነብያት ክርስቲያን አልነበሩምን?

ለሙስሊም ሰባኪያን ሙግት ምላሽ የእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ የተገለጠ አምላክ መሆኑንና ከእርሱም በፊት የነበሩት ነብያት እና የእምነት አባቶች ከዛም በመቀጠል በሐዲስ ኪዳን የነበሩት ሐዋርያቶች እርሱን እንደተከተሉ የክርስትና መሠረት እምነት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። በተጻራሪው ግን ቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፈው ከተጠናቀቁ ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ የመጣው እስልምና ደግሞ በቀድሞ ነቢያት ተወርቶ እና ተሰብኮ የማይታወቅ አምላክ አስተዋወቀን፤ ከዛም አልፎ ተርፎ ተከታዮቹ ሙስሊም እንጂ ክርስቲያን አይደሉም ብሎ ብቻውን ቆሞ ያስተምራል። ኢስላም ናቸው እንጂ ክርስቲያን አይደሉም የሚለው ንግግር በብዙ ሙስሊሞች ዘንድ እንደ ትልቅ ርዕስ አድርገው ክርስቲያኖችን ጋርም በጥያቄ መልክ ሲቀርብ ይስተዋላል። እኛም ይህን አስተምሮታቸው ከሆነው ከቁርኣን የመነጨ እና ጥያቄያቸው በራሱ ማስረጃ የሌለው ኪስ ወለድ ሙግት ሀሳብ መሆኑን እንመለከታለን። በመጀመሪያ ግን ክርስቲያን እና ደቀመዛሙርት ማለት ምን ማለት ነው? ክርስቲያን(Χριστιανούς/ክሪስትያኑስ)፦ ማለትም የክርስቶስ ተከታይ ወይም በክርስቶስ ህግ እና ትምህርት የሚመራ ማለት ነው። የእርሱ አቻ ቃል የክርስቶስ ደቀመዝሙር/μαθητής  ሲሆን ጥቅልል ትርጉሙ “ የክርስቶስ ተማሪ ”ወይም” የክርስቶስ ተከታይ” ማለት ነው። የሐዋርያቶች ደቀመዝሙር የነበሩት ከማን እግር ስር እንደተማሩ ለመግለፅ ይህንን ቃል ይጠቀሙትም ነበር። ለቅምሻ ታህል ደቀመዝሙር በሚለው ቃል ላይ አንድ ምሳሌ ላሳይ፦ ጶሊቃርጶስ በ70ዓ.ም ተወልዶ በ155 ዓ.ም ወይም በ160 ዓ.ም የሞተ የሐዋሪያው ዮሐንስ ደቀመዝሙር(ማቴቴስ/μαθητής) እንደነበር የቤተክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት ያወሱናል። በተጨማሪ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ዘአቴንስ ደግሞ ስሙም በሐዋ17:34 ላይ የተጠቀሰ ሲሆን ይህ የቤተክርስቲያን አባት ደግሞ የሐዋርያው ጳውሎስ ደቀመዝሙር (ማቴቴስ/μαθητής) እንደነበር ይነገራል። ይህ ማለት ጶሊቃርጶስ የሐዋርያው ዩሐንስ ተከታይ ሲሆን፤ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ዘአቴንስ የቅዱስ ጳውሎስ  ደቀመዝሙር እንደሆነና የአስተማሪያቸው ማቴቴስ ተብለው መጠራታቸውም ከታሪክ ክታባት እንረዳለን። በአንዳንድ የሙስሊም ተሟጋቾች የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት እንዲሆኑ እንጂ ክርስቲያን እንዲሆኑ ኢየሱስ ሐዋርያትን አላዘዘም ይላሉ። ነገር ግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር ማለት እና ክርስቲያን ከሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው። ስለዚህ ደቀመዛሙርቴ ካለ( ዮሐ 15:8፣ 13:35፣ ማር 14:14፣ ሉቃ 22:11፣ ማቴ 26:18…) የእርሱ ተከታይ(ክርስቲያን) መሆናቸውን ምንም ሳናቅማማ እንቀበላለን ማለት ነው። ስለ ክርስትና እና ደቀመዝሙር ይህን ያህል ካየን ነብያቱ ክርስቲያን ነበሩ ወይ? ክርስቲያን ከነበሩስ ምንድነው ማስረጃቹ? የሚለውን በመመለስ እንዝለቅ። የክርስቶስ ምስክርነት በማቴዎስ ወንጌል 5፡3-13 ላይ በተለምዶ ይህ ክፍል የተራራው ስብከት በመባል የሚታወቅ ሲሆን ሙሉ ዐውደ ምልከታ እያነበባቹ ስትወርዱ ቁጥር 11-12 ላይ አንድ አስደናቂ ንግግር እንመለከታለን እንዲህ ይላል፦ “ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።”  ማቴዎስ 5፥11 እዚህ ክፍል ላይ ኢየሱስ እርሱን በመከተላቸው ስለሚደርስባቸው ነቀፌታ፣ ስደትና ችግር ሁሉ መፍራት እንደሌለባቸው፤ ጨምሮም ብፁዓን እንደሆኑ ይነግራቸዋል። ስደቱም በክርስቶስ ያለ መሆኑን በቁጥር 11 ላይ በእኔ ምክንያት የሚል ንግግር ያስቀምጣል። በዚህም አላበቃም ይቀጥልና በቁጥር 12 ላይ እንዲህ ይለናል፦ “ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”  ማቴዎስ 5፥12 ክርስቶስን የሚከተሉ ሰዎች ዋጋቸው ታላቅ እንደሆነ! እርሱንም መከተል የዚህ ስደት እና እንግልት ከንቱ እንዳልሆነ፤ ይልቁንም “ከእናተ በፊት የነበሩትን ነብያቶች እንዲሁ አሳድዷቸዋልና በማለት በረከቱን ይነግራቸዋል። ምክንያቱም በክፍሉ ዐውድ ሲብራራ እነርሱ ተነቅፈዋል፣ ያላቸው ነገር አጥተዋል፣ ስለ እርሱ ሲሉ መረባቸውን ጥለው ተከትለውታል መሠደዱ እና ማጣቱ “በእኔ ምክንያት ነው ይላቸዋል” ነገር ግን እኔን መከተላችሁ ከንቱ አይደለም፤ ብሎ ይቀጥልና፦ ከእናተ በፊት የነበሩትን ነብያት እንዲሁ አሳድዷቸዋልና በማለት ከቀድሞ ነብያት ጋር አገናኝቶት የቀድሞዎቹም መሠደዳቸው በእርሱ መሆኑን ይነግራቸዋል። በተጨማሪም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 23፥34-37 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የኦሪት ህግ መምህራንን እና ፈሪሳውያንን ሲነቅፍ እንዲህ ብሎ ሲናገር እንመለከታለን፦ ማቴዎስ 23 ³⁴ ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤³⁵ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።³⁶ እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል።³⁷ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም። ትኩረት ሰጥታቹ ተመልከቱ፤ ቅዱሱም ማቴዎስ የክርስቶስን ንግግር አጽንዖት ሰጥቶ ነው እየጻፈልን ያለው። የጌታችን የኢየሱስ ንግግርም ዝም ብሎ ሀይለ ቃል አይደለም ይልቁን የርዕሳችን ዋና ማገር እንጂ። እንዲህ ነው ነገሩ፦ ጌታችን እሱን ባለመቀበላቸው የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በራሳቸው ላይ ሊደርስባቸው ያለውን መከራ ተናግሯል ነገር ግን ከዛ መከራ ያርፉ ዘንድ ዶሮ በክንፎቿ ስር እንደ ምትሰበስብ ሲጠራቸው እንመለከታለን። በዛው ክፍል ላይ፦ “እኔ ወደ እናንተ ነቢያትን እልካለሁ” ስለዚህ ያለ ጥርጥር እዚህ ነብያትንን፣ ሐዋርያትን እና ሌሎች የእሱን ተከታዮች መሆኑን እየገለፀ ነው። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? በድጋሚ ወደ ማቴዎስ ተመልሳቹ ጌታችን የተናገረውን እና ያለውን አስተውሉ፦ “ከአቤል…እስከ ዘካሪያስ” ስለ አቤል ሞት ተጽፎ የሚገኘው በዘፍ 4፥8 ላይ ሲሆን፣ ስለ ዮዳሄ ልጅ ስለ ዘካሪያስ ሞት ደግሞ በ2ዜና 24፥20-22 ተጽፏል። ጌታችን ኢየሱስ በዚህ ላይ ምን እያለ ነው ከተባለ በአይሁድ የቅዱሳት መጻሕፍት ቅደም ተከተል መሠረት፣ መጽሐፈ ዜና መዋዕል የብሉይ የመጨረሻ መጽሐፍ ነው። “ከአቤል እስከ ዘካሪያስ” የሚለው አባባል እኛ “ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ” ከምንለው ጋር ተመሳሳይ ነው። ታዲያ ጌታችን ይህን ሀይለ ቃል መጠቀሙ የብሉይ አጠቃላይ ሰማዕታን የሆኑ መልዕክተኞች እርሱ እንደላካቸው ማስገንዘቡን እንመለከታለን። አስተውሉ እኔ ልኬ ነበር ገደላችሁ እያላቸው ነው። የትኛው ነብይ እንዲህ ሊናገር ይችላል? ለዚህም ነው ከጌታችን ንግግር ተነስተን ኢየሱስ ያህዌ ነው፣ የቀድሞም ነብያት እርሱን ሲከተሉ ነበር የምንለው። የእነዚህ ክፍል ማብራሪያ ከሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት ጋር በማመሳከር ከእነርሱ(ከሐዋርያቶቹ) በፊት የነበሩት ነቢያትና የእምነት አባቶች ጨምሮ ክርስቶስን እንደተከተሉ ስለ እርሱም ሲሉ መከራን እንደተቀበሉ እናም እንደተነቀፉ ከዚህ በመቀጠል በቅድመ ተከተል እንመለከታለን። የሌሎች ሰዎች ምስክርነት ቅዱሳት መጻሕፍት ከዚህ ርዕስ አንፃር ምን ያስተምራሉ? የሚለውን ለመመለስ በዕብራውያን መልዕክት ምዕራፍ 11:1-40 ያለውን መመልከት ለዚህ ጥያቄ ጥሩ ምላሽ የምናገኝ ይሆናል። በዚህ የታሪክ ምዕራፍ ስለ እምነት አባቶች ከሚያወሳ ክፍል ከሆነው ዕብራውያን ምዕራፍ 11:25-26 የሙሴ ያሳለፈው የህይወት ውጣውረድ እንዲህ እንዲህ በማለት ያስቀምጣል፦ “ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና።”  — ዕብራውያን 11፥25-26 በደንብ አስተውሉ የዚህን ክፍል ጥቅስ ከማቴዎስ ወንጌል 5:11-12 ጋር ስናነፃፅረው ጥልቅ መልዕክት ይነግረናል። ከላይ በተራራው ስብከት ላይ እርሱን በመከተል ስለሚደርስ መከራ ከነገራቸው በኋላ በዚህም ሳያበቃ እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ በእርሱ ምክንያት መከራው የበዛባቸው የቀድሞም ነቢያቶችም ጭምር በመከራ ውስጥ ማለፋቸውንና የቀኝ እጃቸውን አሻራ አሳርፈው እንዳለፉ ይነግረናል። ታዲያ ከቀድሞ ነብያት ውስጥ ታላቁ ነቢይ የነበረው ሙሴ <<ከግብፅ ጮማ እና ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መከራን መቀበል>> እንደመረጠ የዕብራውያን መጽሐፍ ይነግረናል። ስለዚህ ክርስቲያን በሚለው የቃሉ ትርጓሜ መሠረት በመነሳት ከቀድሞ ነብያት ውስጥ ሙሴ ክርስቲያን ማለትም የክርስቶስ ደቀመዝሙር (μαθητής/ማቴቴስ) እንደነበረ እንመለከታለን ማለት ነው። ታዲያ ታላቁ የብሉይ ኪዳን ነቢይ ሙሴ እንዴት ሆኖ ነው ክርስቶስን ተከትሎ ሙስሊም የሚሆነው? ሙስሊም ማለትስ ክርስቶስን መከተል ነውን? መልሱን ለአንባቢ ልተወው። የዕብራውያን መልዕክት ጸሐፊ በዚህ አላበቃም ተጨማሪ ጥልቅ ጠቢብ ሚስጥር እንዲህ በማለት ለተደራሲያኑ ይገልፅላቸዋል፦ “እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና።”  ዕብራውያን 11፥39-40 እነዚህ ሁሉ የተባሉት በቁጥር 38 ላይ በጠቅላላ ለመተረክ ጊዜ ያጥረኛል ያላቸውን መሆኑን በክፍሉ ዐውደ ምንባቤ ላይ መረዳት ይቻላል። ከላይ ባለው ጥቅስ በመጨረሻ ቁጥር ስር

የቀድሞ ነብያት ክርስቲያን አልነበሩምን? Read More »

የጥንቱን ሃይማኖት!

የዚህን ታላቅ ፕሮቴስታንት ሐዳሲ ንግግር ያስተዋለ የትኛውም በፕሮቴስታንት ጥላ ውስጥ ያለ ሰው በቀጣይ ሚያስተውለው ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት የገቡበትን ችግር ታሪካዊነቱ ቀርቶ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ የአምልኮ ስርአት ችግር ነው።[ይህ ችግር በተለያዩ ቦታዎች የሚደረጉ ቅጥ ያጣ ፈንጠዝያን ጨምሮ የሚያካትት ነው።] ይህን ችግር ግን በታሪካዊው ወይም በክላሲካል ፕሮቴስታንት መነጽር ስናየው የቀድሞው መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት ባለው በቤተክርስቲያናዊ አስተምህሮ የበለጠገ አምልኮ እንዲሁም ለእነዚህ ቅጥ ላጡ አካላት እጅግ የታመነ የእምነት አቋም እንዳለው ቢታወቅም ልንክድ ማንችለው እውነት ግን ወንጌላዊያን አብያተክርስቲያናት ውስጥ ሚታየው ስረአት አልባ የአምልኮ ስርአት አግባብ ያልሆነ ብቻ ሳይሆን እጅግ ስህተት የሆነ ልምምድ መሆኑን ነው።(መታረምና መታየት ያለበት መሆኑን ይህ ጽሑፍ አጥብቆ ይናገራል) እንዲያው የዚህን ጉዳይ ጉድለት ትኩረት ሰጥተን ብንመለከተው ችግር ሆኖ ምናገኘው የእውነት ጉድለት ሳይሆን፥ ለድህረ ዘመናዊነት እጅግ የተጋለጥን መሆናችን፣ ቃሉን ሳይረዱት “ሃይማኖት አያድንም” የሚሉና የአስተምህሮን አስፈላጊነት የጣሉ ሰባኪያንና መምህራንን በተሃድሶው ክርስቲያን ማህበረሰብ ዘንድ ምስባክ ላይ ማቅረባችን፤ ይህንንም ተከትሎ አጥንትን ከመጋጥ ይልቅ ወተት መጋትን የሚወድ፣ በእምነቱ በቆየበት ልክ እውቀትንና ብስለትን ያጣ ምእመን ማፍራታችን ለዚህም የልጆች ፈንጠዝያ ሥርአተ አምልኮ መፍያና ማሟያ እንዲሆኑ ጆሮአችንን ለማከክ የፈቀዱን ሰዎች መሪዎችና እረኞች እንዲሁም መጋቢያን ዝም ማለታቸው ነው።(አጥብቀው የሚቃወሙና አጥብቀው የሚገስጹ እንዳሉ መዘንጋት የለብንም) መፍትሔ፦ መፍትሔው ሐዳሲያኑ የቆሙበትንና እኛም የተነሳንበትን እውነት አለመጣል ነው። ምክንያቱም ጌታን ለምን እንደተከተልነው እናውቅ ዘንድ ይገባናልና። ስለዚህ እውነትን በሙላት ልንካፈል እንጂ እምነትን አስታከን ለወደቀው አዳማዊ ማንነታችን ነፃነትን በመስጠት አለማዊነትን ልንለማመድ አይደለም። መሰረታችና አስተምህሮአችን የሆነው“የእግዚአብሔር ቃል ብቻ” “የእምነት መግለጫችንም” ብቻ ሳይሆኑ ምስባኮቻችንን፣ ልምምዶቻችንንና አምልኮአችንን የቆምንበት እውነት ሊገልጹ ይገባል። የዚህ ችግር ጉዳት “ውሃ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው” እንዲሉ አበው እንደ ምእራባዊያን ሳይታወቀን ቀስ እያልን ለዘብተኞች እንዳንሆን። ወንድምና እህት ክርስቲያኖች ሁላችን ለምን እንደተጠራን ካወቅን እንግዲህ እንንቃ። ከራሳችን፣ ከቤተክርስቲያን ጣዕመ ዜማ ካለው አምልኮ፣ ከቅዱሳን ስብስብ(ማህበር) አስበልጠን የተሸከምነውን አለማዊነትንና ለአለማዊነት ያዘመመን ለዘብተኛ ክርስትናን ፈፅመን እናስወግድ፥ ማን እንደሆንን እናውቃለንና። ➠ የተሐድሶአችን ጥሪ ወደቀደመው እምነት እንመለስ እንደሆነ ሁሉ፥[2] ➠ እንደ ቀድሞው የአምልኮአችንን ማእከል፥ ቅዱሳት ምስጢራትንና የእግዚአብሔርን ቃል መሠረታችን እናድርግ። ➠ ሥላሴያዊ የሆኑ መዝሙሮችና ስብከቶች ስርአትና ልምምድ ይሁኑልን፥ ➠ እንደ እምነታችን እንዘምር፣ እንስበክ፣ እናስተምር። ይህ ሁሉ ሲሆን በመንፈስ ቅዱስ ሃይል፥ በልጁም በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል ለእግዚአብሔር አብ ክብር ይሆን ዘንድ። ቅዱስ ባስሊዮስ ዘቄሳርያ በእንተ መንፈስ ቅዱስ መጽሐፉ ላይ፦ “…ቤተ ክርስቲያን የጠበቀችው ሐይማኖት በሐዋርያት የተላለፈውን ነው፣ የተቀበልነው እንዳናጠፋ ከአባቶች እምነት ጋር ጸንተን እንኑር !..” በማለት የተሐድሶ አበው እንዳስቀመጡት ባስልዮስ ያስቅምጠዋል። ታዲያ ቤተክርስቲያን ከዚህች ወጥመድ ታመልጥ ዘንድ የተሐድሶውን ወቅት በማየት መነጽራችንን ወደ ቀደመው አምልኮዎቻን እንመለስ ስንል ይህን ጽሑፍ እንቋጫለን። በአሚነ ሥላሴ ያጽናን። አሜን! ማጣቀሻ [1] The first book of discipline, Volume 3 page 34 [2] ተሐድሶ ማለት አዲስ ክርስትና መመሥረትና መቀጠል አይደለም። ይልቅ ወደ ቀደመው ውብ ክርስትና ቃሉ ብቻ የበላይ ወደ ሆነባት ክርስትና እንመለስ እንጂ።

የጥንቱን ሃይማኖት! Read More »

መጽሐፍ ቅዱስ ብቻን እንጠያየቅ – ክፍል 2

ጥያቄ፦ እሺ ይሄን ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ያልከውን እንደ ሙግትህ ልቀበልህና መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እየተባለ የተለያየ ሥነ-አፈታት ላይ የተለያየ ምልከታ ትደርሳላችሁ? ለዚህ ስነ አፈታት ዳኛችሁ ማነው? መልስ፦ በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው። ይሄ እኮ ጥያቄ ቢነሳ በእናተም ዘንድ ያለ ነው።(ትውፊት ያላችሁ እናተም ይሄንን ተመሳሳይ ክሌም ማንሳት እንችላለን።) እኛ ነገሩን ሥነ መለኮታዊ ክፍፍሎሽ(Theological Triage) ብንሰራለት እንኳን። ወደፊት የማስረዳህ ይሆናል። አሁን ግን ወደ ጥያቄህ መልስ ልለፍልህ። ጥያቄ፦ እሺ መልስ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እያላችሁ ሥነ አፈታት ላይ ብዙ ትለያያላችሁ። የሚል ጥያቄ ነው የተነሳው። ያው የሥነ-አፈታት መርሖ በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ መነጸር ሲታይ የራሱ የሆነ መንገድን አለው። ለሶላ ስክሪፕቹራ አማኝ መጠየቅ የሌለብህና ማሶገድ ያለብህ ጥያቄ፦ ስህተት1፦ እንደው ሰው እንደፈለገ እየፈታ እየተረጎመ መጠቀም አለበት የሚል እሳቤ አለው። ስህተት2፦ የመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ችግር ይሄን ያስከትላል። ስህተት1 እና ስህተት2፦ የሁለታችሁ ዳኛችሁ ማነው ታዲያ? ለስህተት1 እና ለስህተት2 ድምዳሜህ ምላሻችን፦ መልስ፦ እነዚህ ነገሮች ለመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ አማኝ ለሆነ ሰው የሚቀርብ ጥያቄ ነው ብዬ አላምንም።[እንዴት የሚለውን ወደ በኋላ እናየዋለን] ታዲያ ለዚህ መነሾ የመጀመሪያው መፍትሄ መርሕ የምንለው የሥነ አፈታት መርሖ በመባል ይታወቃል። ይህ ደግሞ አንደኛው መንገድ ነው(አውዳዊ ንባብ ንፅፅራዊ ምልከታ ነው።) ጥያቄ፦ ቆይ ቆይ ይህንን ታዲያ ሌላኛው ጎራም እነሱም ክሌም ያደርጉታል ግላዊነት አይደለም ወይ? መልስ1፦ ጥሩ ጥያቄ ነው። ግን የተሳሳትከው ነገር በተለይ በተለይ HGL(ጽሑፋዊ፣ ሰዋሰዋዊ እና ታሪካዊ ዳሰሳ) እንደነ ዲኤ ካርሰን የመሳሰሉ ምሑራን ይህ አይነቱ ትርጓሜ መጠቀም ይበልጥ ከግላዊነት ይልቅ ወደ ጽኑ ትርጓሜ እንደሚያመጣ ያስረዳሉ። ምክንያቱም ይሄ አይነቱ መንገድ ሥነ አፈታቱ በአውዱ ሲታይ፦ ➙ አውዳዊ ያልሆነው ተሟጋችህ ይወድቃል ➙ ከዛም ሻገር ስትል ሰዋሰዋዊ መንገድ በመጠቀም ታርመዋለህ፣ ➙ታሪካዊ መንገድን ትጠቀማለህ። ይሄ አይነቱ ሥነ አፈታት ለግላዊነት ወጥመድ ነው ማለት የማይቻልበትን መንገድ ቀጣይ ከማነሳቸው ካልኩህ ጋር አያይዤ አቀርባቸዋለሁ። መልስ 2፦ ሌላው በእነ R.C Sproul እና John Piper ተቀባይነት ያለው ሲሆን ይህህም መንፈሳዊውን ትርጓሜ ነው። ይሄ የሚወሰደው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ነው። እንደ R.C Sproul እና John Piper አይነቱ የሚሉት መንፈስ ቅዱስ ለመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜ እንዳንስት ትልቁን ሚና በአማኞች ዘንድ ከጥናት አንጻር እንደሚሰራ ይናገራሉ። ➙ ታሪካዊ የጉባኤዎች ውሳኔ እና መግለጫዎች ለሥነ አፈታት ቀጥተኛ ተዛምዶ ባይኖራቸውም(ማለትም በእነርሱ ተጠቅሞ በቀጥታ መተርጎምን ማድረግ ባይችሉም) በሉተራኑ ሥነመለኮቱ ላይ ባሉ እንደነ Robert Kolb እንደሚሉት ክሪዶች እና ኮንፌሽኖች ለመጽሐፍ ቅዱስ ስነ አፈታት አቅጣጫ ጠቋሚዎች ናቸው ይላሉ። ይህም ለቅዱሳት መጻሕፍት የበላይ ባለሥልጣንነት እንዲሁም በቂ እንደ መረታዊ አስተምህሮ ማለታችንም ነው። መልስ 3፦ በሥነ አፈታት ላይ ጥያቄህን በመራሕያነ ተሐድሶዎች በኩል ዘንድ የሚነሱ ሙግቶች ቢሆኑ ለምሳሌ፦ ካልቪኒዝም እና አርሜኒያን የሚል ቢሆን በቀላሉ ከትውፊት ጋር ካልሆነ የምትሉም ራሳችሁ ተከፋፍላችሁ ሳለና ወደ አበው ጎራ መካከል ጠጋ ስንል ራሱ ከሥነ አፈታት ጀምሮ ሁለት አይነት ቤተ እውቀቶች አሉ ብሎ ሀሳብህን መሞገት ይችላል። ምክንያቱም በእስክንድርያ ያለው ቤተ እውቀት እና አንጾኪያ ያለው ቤተ እውቀት መካከል የሥነ አፈታት ልዩነቶች ይስተውላሉ። የእስክንድርያው አመስጥሮታዊ ፍቺ(allegorical interpretation) ሲጠቀም የአንጾኪያው ደግሞ ቁማዊ(literal) ይጠቀማል። በተለይ በነገረ ክርስቶስ ዶክትሪን አንጻር ከተመለከትነው ጎራ መደብ ልዩነቶች ይስተዋላሉ(Hypostatic Union & two nature of Christ)። የእኛ ጥያቄ የሚሆነው ስለዚህ የትኛው የትምህርት ቤተ እውቀት መጽሐፍ ቅዱሳዊውን ስነ አፈታት ተጠቅሟል? የሚባል ጥያቄ ቢነሳ በቀላሉ የሚታለፍ አይደለም።[ማንሳትም እንችላለን ለማለት ነው] ስለዚህ መልስ1፣ መልስ2 እና መልስ3 ሲቀመጡ፦ ድምዳሜ 1፦ ከላይ እንዳልነው በእኛ ምሑራን ዘንድ የሚባለው የቅዱሳት መጽሐፍ ትርጓሜ ከማንኛውም ግላዊነት የጸዳ መሆን ይኖርበታል። ነገር ግን በቤተክርስቲያን ታሪክ ስንመለከተው ሁለቱ ቤተ እውቀቶች ተጽዕኖ ያሳደረባቸው የየራሳቸው ነገሮች አላቸው። የእስክንድርያው ቤተ እውቀት(Alexandria school) ለምሳሌ በፕላቶኒዝም በሃይል የተጠቃ ሆኖ እናየዋለን። ለዚህም የእስክንድርያው አርጌንስ ስለ ነብስ የሚያብራራው ከባሲል ቄሳርያው ሊለይ ይችላል(የተለየም ነው) አርጌንስ ስለ ነብስ ያለውን ቴዎሪ ለጥጦ ፕላቶኒክ በሆነ መልኩ መጽሐፍ ቅዱስን መፍታትን ሊያደርግ ይችላል። ይሄም ደሞ ምናልባት ወደ ስህተት ሊያመጣውም ይችላል(ስለ soul የሰጠውን ኮንሰፕሽን ስለምናውቀው) ስለዚህ ነው ያለንበት አካባቢ ያስተማሩን ሰዎች ወይም የግል ምልከታ በራሱ ለመጽሐፍ ቅዱስ ሥነ አፈታት መርህ ሆነው ይመጣሉ።[እንደውም የአበውን ሥልጣን ከመጽሐፍ ቅዱስ እኩል ካደረግነው ግላዊ ሥነ-አፈታት ሚነግስ አይደመስልህም?] ስለዚህ አንድ ትክክለኛ የሆነ የሥነ አፈታት መርሖ ያስፈልገናል። ይህም ሁሉም የሚዳኝበት HGL የምንለው መርህ ላይ አይመስልህም? ያው እንደ ጥያቄ ከተነሻ መወያየት እንችላለን ለማለት ነው። ድምዳሜ 2፦ ስለዚህ በሥርአት ከተጠናና ቋንቋውን እና ታሪካዊ አውዱ ከታየ ወደ ትክክለተኛው ሥነ አፈታት ይመራናል። መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ምንም እንኳን ግላዊን ትውውቅ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ያለንን ሕብረት ቢያበረታታም ከትርጓሜው እጅጉን ያርቀናል ማለት አይደለም። ስለዚህ በዶክትሪናል ነገሮች ሆኑ በአንዳንድ ውይይቶች ቤተክርስቲያን ውስጥ መታቀፍና ቅዱሳት መጻሕፍትን ለመተርጎም አማኞች ተጠያቂ ቢሆኑ የሚልን ነገርን መርሳት የለብንም። ይሄም ደሞ ግላዊነትን ይቀንሳል። በተለይ እንደ አማኝ አጥብቀን መያዝ ያለብን መንፈሳዊው ላይ ነው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ለአማኞች የተላከው ለማስተማር ለማቅናት እና አቅጣጫን ለመስጠት እንደሆነ ሁሉ በጸሎት እና በትጋት በህብረትም ሆነ በግል በቤተ ክርስቲያን ጥላ ውስጥ የእግዚአብሔርን ቃል ማንበብ ጠቃሚ ነው እንላለን። ይህም የመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ አስተምህሮን አይቃረንም።

መጽሐፍ ቅዱስ ብቻን እንጠያየቅ – ክፍል 2 Read More »

መጽሐፍ ቅዱስ ብቻን እንጠያየቅ – ክፍል 1

ጥያቄ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻን(Sola Scriptura) ተቀብሎ መቀጠል የቤተክርስቲያን ሥልጣናዊነትን እና የአበውን ጽሑፍ ባለስልጣንነትን እንዳንቀበል ያደርጋል። አይደል? መልስ፦ ኧረ በፍፁም! ይህን እንድንል ትንሽ ክፍተት እንኳን አይሰጠንም። ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ብቻና አይሳሳቴው ባለስልጣን ነው የሚለው አስተምህሮ እነዚህን ጨምሮም ነው፦ ➙ ቤተክርስቲያን ባለስልጣን ነች። ➙ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ስንልም የአበው ክታባት ባለስልጣን አድርገን ነው። ይህን ስንል ግን ሊሳሳት የማይችልና የሁሉ መመዘኛ ባለስልጣን የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን አምነን ነው። ለዚህም ነው አውግስጢኖስ እንዲህ በማለት የተናገረው፦ If you discover in my writing anything false or blameworthy, you may know that it is bedewed by a human cloud, and you may attribute that to me as truly my own.[1] ስለዚህ እነዚህ መጻሕፍት ማለትም የአበው ክታባት ሕጸጽ ከሌለባቸው (infallible & inerrant) ከሆኑ ከቅዱሳት መጻሕፍት ቀጥሎ ክብር የሚሰጣቸው መጽሐፍት ናቸው። ጥያቄ፦ ለዚህ ንግግርህ የአዲስ ኪዳን ድጋፋት አለህ? መልስ፦ አዎ። ጌታ ኢየሱስ ካደረገው እና ካስተማረው ማሳየትና መጥቀስ ችላለሁ። ለምሳሌ፦ ማቴዎስ 23¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¹ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው፦² ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል። ጌታችን በማቴዎስ 23:2-3 በሙሴ ወንበር ላይ ስላሉ ጻፎችና ፈሪሳውያን ለተናገሩት ቃል ለቃላቸው መታዘዝ እንደሚገባ ያስተምራል።(ይሄም ደሞ በዘመኑ ሥልጣናዊ መሆናቸውን ያሳያል። ለዛም ሥልጣን መታዘዝ እንዳለብን ይናገራል።) ይህን አይተን ረሱ ጌታችን በማቴዎስ ምዕራፍ 15፥1-39 ላይ ጻፎች እና ፈሪሳውያን የደነገጓቸውን መመሪያዎች ከዋናው ከመጽሀፍ ቅዱስ ማዕከላዊ ትምህርት ጋር ስለተቃረኑ ይቃወማቸዋል።(ይህ ደሞ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመናት ከመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን በላይ የሆነ ግዛት እንዴሌለ ያሳየናል። መልሴን በአጭሩ ሳስቀምጠው፦ መነሻ1፦ ጻሕፍት እና ፈሪሳውያን ሥልጣናዊ ናቸው። መነሻ2፦ ይህ አንድ አካል ሥልጣን አለው ማለት ግን የግድ ሊሳሳት የማይችል ሥልጣን(ከመጽሐፍ ቅዱስ እኩል የሆነ) ነው ማለት ግን ፈጽሞ አይቻልም። ስለዚህ ድምዳሜ1፦ ስለዚህ ይህ ሥልጣናዊው አካል ራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ይመዘናል። ልክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳደረገው። ድምዳሜ2፦ እነዚህ መዛኞቹ ጌታችንን ራሱ የጠየቁት እና የመዘኑት በመጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ የሚያሳየው በዘመኑ በእነርሱ አስተሳሰብ መጽሐፍ ቅዱስ የበላይ ባለስልጣን መሆኑን ጥቂት የሚያሳይ ፍንጭ ነው። በዚህ ክፍል ግን ጌታችን የበላይ ባለስልጣን ያደረገው ራሱ በነብያቱ በኩል የተናገረውን የራሱን ቃል በሕዝቡ ዘንድ ነው። በመጨረሻም ድምዳሜ1 እና ድምዳሜ2፦ መጽሐፍ ቅዱስ የማይመዘን መመዘኛ ነው። ይህ ማለት ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማለት ነው። አንተም ስትጠይቅ እኛ የምንለውን መጽሐፍ ቅዱስ ባለሥልጣን ነው ስንል ሌሎች ባለስልጣናንነታቸውን መካድ ማለት አይደለም። ይልቅ የማይመዘነው ብቸኛ የማይሳሳት መመዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ማለት ነው። መልስ፦ እሺ። አሁን የእኛን እሳብ ተረዳህ? ጥያቄ፦ ይቀጥላል… ማጣቀሻ

መጽሐፍ ቅዱስ ብቻን እንጠያየቅ – ክፍል 1 Read More »

Soli Deo Gloria/ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ

በቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ከተወገዙ የምንፍቅና መምህራን አንዱ ፔላጄዬስ ነው። እርሱም እግዚአብሔር በሰው ልጆች የድነት ስራ ላይ በብቸኛነት ያለውን ባለቤትነት ፈፅሞ ከወደቀው ሰው ነፃ ፈቃድ ጋር የጋራ ስለነበረ ነው በማለቱ ነው።(ይህን ታሪካዊ ምሳሌ ያነሳንበት የምንሞክርበት ምክንያት ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ የሚለው ክርስቶስ ካደረገው የድነት ሥራ ጋር ስለሚገናኝ ነው።) ይህ ሰው የእግዚአብሔርንም ጸጋ ለሰው ልጆች ድነት አነሳሽ ብቻ እንጂ የድነት ምንጭ አይደለም ብሎ ያስተምራል። ይሄን ትምህርት ደሞ ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ በክታቡ ከዚህ በተቃራኒው ሆኖ እንዲህ ይናገራል፦ “ሁሉ ኃጢአትን ሠርተዋልና የእግዚአብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል፤”  — ሮሜ 3፥23 ክፍሉ የሰው ፈቃድና ባህሪይ በኃጢአት መበከል፣ ከእግዚአብሔር እንደለየው፣ የሰውም ፈቃዱም ወደ እግዚአብሔር ፈፅሞ ሊሆን እንደማይችልና እርሱንም ሚፈልግ ማንም እንደሌለ በክታቡ እንዲህ በማለት ይናገራል፦ “ጻድቅ የለም አንድ ስንኳ፤ አስተዋይም የለም፤ እግዚአብሔርንም የሚፈልግ የለም፤ ሁሉ ተሳስተዋል፥”  — ሮሜ 3፥11 ከዚህም መጽሐፍ እንደምንረዳው የሰው ድርሻ  በድነቱ ውስጥ ባዶ ቦታ እንዳለው ይናገራል። ስለዚህም ጻድቅ የሆነውን እግዚአብሔርን ሊመርጥ በሰውም በኩል ወደ እግዚአብሔር ልቡንም ወደ ፈጣሪው ሊመልስ ይህ ሙት ሰው አይቻለውም ምክንያቱም ሁሉ ኃጢአትን ሰርተዋልና። የሞተስ እንዴት ሕይወትን ይመርጥ ዘንድ ይቻለዋል? ነገር ግን በምህረቱ ባለፀጋ ስለሆነ ስለወደድን ሳይሆን ስለወደደን ብቻውን ለድነታችን ምክንያት፥ የድነታችንም ፍፃሜ ሆነልን። በቀደመው ኪዳን ተስፋ በእርሱ ላይ ባላቸው እምነት አባቶችን አዳነ፥ በዘመኑ መጨረሻ  በልጁ የቤዝዎት ስራ ህጉን መጠበቁን አውቀን በእርሱ ስላመንን ብቻ ጽድቁን ቆጠረልን። ደግሞም አለማትን በፈጠረበት በልጁ የጠፋውን ህዝብ ተቤዥቶ አለሙን አዳነ። በእርሱ ብቻ ተፈጠርን፣ በእርሱ ብቻ ዳንን ያዳነን እርሱ ይቀድሰናል፣ የቀደሰን እርሱ ራሱ ያጽናናል፣ ያጸናን እርሱ ደግሞ ያከብረናል። ወደ ፈጠረን ወደ አባታችንም እንፈፀማለን። በዚህ እንቅስቃሴ ነው የተሐድሶ አራማጆች በሮማ ካቶሊክ ያለውን የተሳሳተ ግንዛቤ ማጥራት መጀመራቸው የሚታወሰው። ታዲያ ለእኛ ምን ይሰራል? ለምን እስካሁን ተቃውሞ ታደርጋለህ? ቢባል መልሳችን እንደ ተሐድሶውያኑ መሠረት የሮማ ካቶሊክ ኢስተርን ሆነ ሌሎች ታሪካዊ ቤተክርስቲያን አማኞች በአብዛኛው ንግግራቸው ሆነ ፍለጋቸው ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ የሚል ነው ይላሉ። ነገር ግን በሚያሳዝን ሁኔታ ግን በተሐድሶ ወቅት የካቶሊኩ ምልከታ ፖፑና ቅዱሳን በሚባሉት ላይ ነው። በሌሎቹ ቤተክርስቲያን የፖፑ አለመቀብልን እናም አይሳሳቴነትን ትተው የቅዱሳን ክብር ገኗል።(ይሄን ስንል እኛ ክላሲካል ፕሮቴስታንት ለቅዱሳን ክብር አይገባም ማለት አይደለም።) ይሄን የእኛን አቋም ለመረዳት አንድ ሰው እንዲህ ሲል የጠየቀንን ጥያቄ ማንሳት ይቻላል፦ ጥያቄ፦ ማርያም የድነታችን ምክንያት ናት ወይ? መልስ፦ በሥጋዌ ምክንያት አዎ ናት እንላለን። በእርሷ በኩል ጌታ ተገኝቷል የሚለውን ነገር ብቻ ለመግለጽ ከሆነ። ለድነታችን ምክንያት ስንል(የአምላክ እናት፣ የብርሃን እናት..) ይህንን ጠቅልሎ ማለታችንም ነው። ጥያቄ፦ እና ታዲያ የምትቃወሙት ምንድነው? ኢየሱስን የድነቴ ምክንያት ብለህ እሷንም ማለትህ እኛ የተለየ ነገር አልን ወይ? ለምን ተቃወምክ? መልስ፦ በድጋሚ እኛ የተቃወምነው ድነታችንን ሆነ ወደ እግዚአብሔር መቅረባችን የራሱን ክብር በመግጡ እንጂ ሰዎች ባደረጉት ወይም በእነሱ በኩል መግባትን ወይ ያለ እነርሱ የሚልን ነገረ ድነታዊ ተፋልሶን ነው። ይሄንንም አጥብቀን ምንቃወመው ከእነዚህን ጋር ተያይዘው በCatechism of the Catholic Churchም ሆነ በሌሎች ቤተ ክርስቲያን ዘንድ የተቀመጡትን የተለጠጠ ግንዛቤዎችን እንቃወማለን፦ “By asking Mary to pray for us, we acknowledge ourselves to be poor sinners and we address ourselves to the ‘Mother of Mercy,’ the All-Holy One” (CCC 2677). “After speaking of the Church, her origin, mission, and destiny, we can find no better way to conclude than by looking to Mary” (CCC 972). ሌላም በእናተው መካከል በቀላሉ የማናልፈው ነገር፦ ” ለእኛ ድኅነት ብዙ መንገድ አለ” በማለት በየምስባኩ ሰው ሰራሽ ዶክትሪን በማሳየት፣ ይባስም ብሎ የእግዚአብሔርን የማዳን ክብሩን የሚነቅልና የሰውን የመገናኛ ድንኳን የሚተክል ትምህርት ስላለ ነው። እና ሌሎችም ነው። በድጋሚ እኛ ክላሲካል ፕሮቴስታንት ስንቃወም እየተቃወምን ያለውን ነገር አጥርቶ ማየት ያሻል። በዚህ ብርሃን መንገድ የተሐድሶ አበው ያሳደጉት ነገር አምስቱን ብቻዎችን ነው። ለዚህም መፍትሔው በቃለ እግዚአብሔር ላይ በተጨመሩ ትምህርቶች በአባቶች ትምህርት የሌሉትንና በታሪክ ዶግማ ተደርገው ያሉትን የእግዚአብሔርን ክብር የሸፈኑትን እነዚያን ተቃውመው ቆሙ። ➞ ስለዚህም ምክንያት ክብር ለእርሱ ብቻ ይገባዋል። ➞ ብቻውን የድኅነታችንን ስራ ሰርቶታልና። ➞ የማዳኑ ኪዳኑ መሰረት እርሱ ብቻ ላይ ብቻውንም አዳኝ  ስለሆነ ላዳነን ለእርሱ በብችኛነት ሌላ ሳይጨመር ሳይደመር አምልኮ ስግደት ይገባዋል። ➞ ብቻውን ሊደነቅ ሊመሰገንም የተገባው ነው እጅግ ድንቅ ግሩምም ነውና። ምክንያቱም እርሱ፦ እንደ እንቁ የተዋበ በኪሩቤልም ላይ የሚቀመጥ በመዞርም ጥላ የማይገኝበት ማንም ሊቀርበው በማይችል ብርሃን ተሰውሮ ለዘላለም ሚኖር ሰማያትን ያለ ምስሶ የዘረጋ ምድርንም በውኆች ላይ ያፀና የምድርም አህዛብ በፊቱ በገምቦ እንዳለች ጠብታ የሆኑለት በጽድቅ የሚፈርድ መሐሪ የአብርሃም የይስሃቅ የያእቆብ አምላክ  የዘላለም አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሄር ሚመስለው የለም!   በዚህም መሠረት ደሞ እርሱም የተባረከ አምላክ ነው ሰውም መድኃኒት ይሆን ዘንድ አይቻለውምና። ይሄን ሐዳሲያኑም ሲሉም ሆነ እኛም ስንለው ቅዱሳንን ክብር አንሰጥም ማለት አይደም። እነሱን ምናከብረው ግን ድነትን መንገድ በመለጠጥ ከሆነና ወይ ደሞ ለእግዚአብሔር የቀረበውን የሚቀናጅ ከሆነ ግን በእግዚአብሔር ክብር ላይ አደጋ ነው። በታሪካዊ ፕሮቴስታንቱ ተሐድሶ ውስጥ ትልቅ ትኩረት የተሰጠውና የአስተምህሮቶች ሁሉ መጠቅለያ ነው። በድጋሚ እንጠየቅ እስኪ?why it still matters(በዚህ ዘመን ላለነው ምን ፋይዳ አለው?) በአጭሩ እኛ ክላሲካል ፕሮቴስታንት በዚህ ዘመን ያለነው ይሄን ለምን እናምናለን የሚለውን ስንመልስ፦ ለእግዚአብሔር ክብር ብቻ የተሃድሶው መሠረታዊው አስተምህሮ የሁሉም ነገር የመጨረሻ ዓላማ ለእግዚአብሔር ክብርን ማስገኘት ነው የሚል ነበር። እነሱ ከመጽሐፍ ቅዱስ የወጣውንና ከቤተክርስቲያን የተገኘውን ያንን መሠረት ይህም የእግዚአብሔርንም ሉዓላዊነት አፅንተው በመጠበቅ፣ የሚሆነው ነገር ሁሉ ከሰው ወይም ከፖፑ(ካቶሊኮችን ነው) ይልቅ እንዴት ለእግዚአብሔር ክብር እንደሚሆን ያስተማሩትን ዛሬም እኛም ማስተማር ስላለብን። አንደ ተሐድሶውያኑ በዘመናቸው ለእግዚአብሔር የሚገባውን ያንን ክብር የወሰዱ አካላት ነበሩ ብለው ተቃውመዋል። በዚህ ዘመንም የእግዚአብሔርን ክብር የሸፈነ አለ። ሻገር ብንልም አምልኩ ቢባል ምን እንደሚጨመር እስከማይታወቅ ድረስ የሚሰጥ ክብር(ኤጲፋንዮስ ኮሊሪዲያንን የተቃወመውን አይነት ላቅ ያለ ክብር ለፍጥራን መስጠት) ብዙ መንገዶች አሉ፤ ለድነታችን ብዙ መፍትሔ አለ። በማለት የክርስቶስ የማዳንን ክብር ዝቅ እስከማድረግ ስለደረሱ ነው። በቀላሉ የማናልፈው ነገር ብዙ መንገድ አለ በማለት በየምስባኩ የእግዚአብሔርን የማዳን ክብሩን የሚነቅልና የሰውን የመገናኛ ድንኳን ስለሚተክል ነው። በመጨረሻም በ16ኛው ክ/ዘ የነበረው የፀጋ ልዩነቶች ነበር። ለእኛም በዚህ ዘመን ፋፍቶና በዝቶ ተቀምጧል። ስለዚህ እኛ ክላሲካል ፕሮቴስታንት ነገረ ድነት ይሁን ሌላ አሁን ላይ ከእነሱ በኋላ በብዙ አካላት መካከል በማደጉ አሁን ላይ የምንቃወምበት ብዙ መሠረታውያን ነጥቦች ይኖሩናል። እኛም እንደ ተሐድሶውያኑ Soli Deo Gloria/ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ/ ስንል ይህንን ጽሑፍ በቅዱስ አውግስጢኖስ በኑዛዜ መጽሐፉ ክፍል.10 ምእ.27 ቁ.38 ጸሎት እንቋጫለን፦ “ምነው ዘግይቼ አንተን ማፍቀሬ! ኦ ጥንታዊም አዲስም የሆንክ ውበት፥ምነው ዘግይቼ አንተን ማፍቀሬ !እነሆ አንተ በውስጤ እያለህ በፈጠርካቸው ነገሮች መካከል ያለ ማስተዋል ስጣደፍ አንተ ከእኔ ጋር ነበርክ፤እኔ ግን ካንተ ጋር አልነበርኩም። እንዚህ ነገሮች ካንተ አርቀውኛል፥ ሆኖም እነርሱም ባንተ ባይሆኑ ኖሮ መኖር ባልቻሉ ነበር።ድምፅህን ከፍ አድርገህ ጮህክልኝ፤ጠራኸኝም። ድንቁርናዬን በሃይልህ ከፈትከው። ጸዳልህን ልከህ ሸፈነኝ፤ አበራህልኝም፤ አይነ ሥውርነቴንንም ገፈፍከው።መኣዛህን ለእኔ ተነፈስክ፤ተንፍሼም ሳብኩት፤ ተከትዬህም ቃተትኩ። ቀመስኩህ፤ ተራብኩ፤ ተጠማሁም። ዳሰስከኝ ለሰላምህ ተቃጠልኩ።” እግዚአብሔርን ብቻ ፊት አድርገን መጓዝ ይሁንልን። አሜን! ለተጨማሪ ንባብና ጥናት ➞ God’s glory alone— the majestic heart of Christian faith and life: what the reformers taught . . . and why it still matters / By David VanDrunen.

Soli Deo Gloria/ክብር ለእግዚአብሔር ብቻ Read More »

ተሐድሶ በአጭሩ

ጊዜው ኦክቶበር 31፣ 1517 ነበር። በዚህ ወቅት ነው አንድ መነኩሴ የተነሳው። ይህ ወቅት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ትልቅ መንፈሳዊ ቀውስ የነበረበት፤ ሥልጣናዊነት በቤተክርስቲያን ላይ ትልቁን ለጳጳጻቱ አድርጎ፣ መጽሐፍትን የመተርጎም ስራ የእነርሱ መብት ብቻ የሆነበትና ትምህርተ ድነት መጽሃፍ ቅዱሳዊ ማንነቱን ያጣበት 16ኛው ክፍለ ዘመን ነበር። በዚህም በአንዲት ትንሽ የጀርመን ትምህርት ቤት ውስጥ ለመጽሐፍ ቅዱስ ሕልውና ሲል የቤተ ክርስትያን በሮች ላይ የተወሰኑ አንቀጾችን ለመለጠፍ በሕይወት ዘመኑም ለመጽሐፍ ቅዱስ ሕልውና ዘብ ለመቆም ሩቅ መንገድ የሄደበት ጊዜ የጀመረው። እነዚያ አናቅጾች የለጠፈበት ምክንያት በዚህ ዘመን እኛ ለሥራ መግለጫ ሥፍራ አሳደን ለማንበብ እንደምንታትረው የቤተክርስትያኒቱ በር ብዙዎች ቀልባቸውን ስበው የሚያነቡበት ሥፍራ ተደርጎ ስለሚወሰድ ነበር በዚያ የለጠፈው። ባስቀመጠው 95 አናቅጽ ውስጥ የኢንደልጀንስን “በጥምቀቱ ጊዜ እንደነበረው አይነት ንጽህና” ከመስጠቱም በላይ ሰዎች ለሞቱ ወገኖቻቸው ሳይቀር ይህንን ክፍያ ከፍለው ከስቃይ ሊያድኗቸው እንደሚችሉ ተሰበከ። በካቶሊኮቹም ዘንድ ፑርጋቶሪ ማለትም ነፍሳችን ወደ ገነትም ሆነ ሲዖል ከመጣሏ በፊት የምትሆንበት ስፍራ ውስጥና በሕይወት እንቅስቃሴዎቻችን እያለን ስላጠፋው ስለኃጢአቷ የሚቆይበትን ጊዜ (ወደ መንግስተ ሰማይ ከመግባቱ በፊት) በሚገዛው ኢንደልጀንስ ማቀናነስ ይችላል የሚል የኑፋቄ ትምህርት ነበር። እንግዲህ ይህ ክስተት ምን ያህል ትክክለኛውን የድህነት መንገድ እንዳጣመመ ለመረዳት የአዲሲ ኪዳናችንን መጽሐፍ ገለጥ አድርገን ብንመለከት ቅዱስ ዮሃንስ በወንጌሉ እንዲህ አለ፦ ዮሐንስ 1¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¹¹ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።¹² ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤ በማለት የመሰከረለት ድነት ለሕንጻ ማስጨረሻ በጳጳሳቱ በተዘየደው መላ ሕያው የመዳኑ መንገድ ተሻረ፤ ይህም ጳጳሳቱ ያልተገደበ ስልጣንና ህጸጽ የለሽ ማንነትን ለራሳቸው እንደወሰዱ በግልጽ ያሳየና ቃሉን ለፈለጉት አላማ ለማዋል እንደሚደፍሩ ያመለከተ ነበር። ነገር ግን ይህ አይነቱ ኢ መጽሃፍ ቅዱሳዊ አካሄድ በሁሉም ዘንድ ይሁንታን አላገኘም፤ እንደ ሉተር አይነቶቹን በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የነበሩ ምሁራን አስነስቷል። በርግጥ ወደ ቤተክርስቲያኒቱ የተወረወረው የመጀመሪያው የተሃድሶ ፍላጻ ከሉተርም ቀደም ይል ነበር። ውስጥ የተነሳው ጆን ዊክሊፍ የጳጳሱን ያልተገደበ ስልጣን በመቃወሙና መጽሃፍ ቅዱስን ማንኛውም ሰው እንዲያነበው ወደ እንግሊዘኛ በመተርጎሙ ምክንያት በኑፋቄ ተወግዟል፤ ተከታዮቹም ከስደት በቃጠሎ እስከመሞት ድረስ መከራ ተቀብለዋል። ታሪኩ ሰፊ ነው በዚህ ማያበቃ ቢሆንም እኛ ግን በዚህ እናብቃ፦ በዚህ ዘመን ያለነው ከቅዱሳት መጽሐፍትና ከአበው ትምህርት ላልተቀዱ ትምህርቶች ጎን ሳንቆም ቅዱሳት መጽሐፍትን የሁሉ የበላይ አድርገን እንድንቀጥልና የቫሌንቲነስ ኑፋቄ የሐዋርያትን ትምህርት ከአፍላጦን ፍልስፍና ጋር ያገናኘ፣ የመርቅያን ኑፋቄ የሐዋርያትን ትምህርት ከስቶይሲዝም ጋር በመቀየጥ የተገኘ ነው እንደሚለው  ዛሬም እንደ ሉተርና ተሐድሶ አበው የምንቃወማቸውን ነገሮች ከራሳችን ሳይሆን ከመጽሐፍ ቅዱስና ከአበው ክታባት እንዲሆን መሆን አለበት። ከቶ ጥለን መቀጠል የለብንም። ለማስተማር የሚነሳ ሁሉ ግለሰብ ከሁሉም አስቀድሞ ሐዋርያት ያስተማራትን የሃይማኖት ትምህርት ጠንቅቆ ማወቅ ይገባዋል።[1] ልክ ማርቲን ሉተር An Assertion of All the Articles (1520) እንደጻፈው፦ I do not want to throw out all those more learned [than I], but Scripture alone to reign, and not to interpret it by my own spirit or the spirit of any man, but I want to understand it by itself and its spirit. “[ከእኔ በላይ] የተማሩትን እነዚያን አውጥቼ ልጥላቸው አልወድም፣ ነገር ግን መጽሃፍ ቅዱስ ብቻ እንዲነግስ፤ በራሴም ይሁን በሌላ በማንም መንፈስ እንዳልተረጉመው፤ በእርሱ በራሱ መንፈስም እንደረዳው እፈልጋለሁ”[2] ከቶ አባቶችን ጥለን የምንቀጥለው ተሐድሶ የለምና ከዚህ ትምህርት ጋር የተቆራኘውን ታሪካዊውን ፕሮቴስታንት(ክላሲካል ፕሮቴስታንት) መኾን ያሻልና አንዘንጋ! ማጣቀሻ

ተሐድሶ በአጭሩ Read More »

Scroll to Top