ድንቅ ነው!! አምላክ ሥጋን ለብሶ ወደ ምድር መጣ የሃጥያት መከራችንንና የዲያቢሎስ የሹፈት ነጋሪት ዝም ለማስባልም ተገለጠ። ነገር ግን የእኛን መከታን ነፃ አውጪያችንን፦ በአክሊል ፋንታ የእሾህ ጉንጉን፣ በፍቅር ከማቀፍ ፋንታ ሰጠነው ጅራፍ፣ በእጆቻችን። እሱም አልበቃ ብሎ አዳኙን ራሱን ራስህን አድን አልነው፤ ሙሾ በሚመስል ቅላጼ እያላገድን አሾፍንበት፤ ከዛም ብሶ ሰቀልነውም በእንጨት በችንካር አድርገን። ይሄ ሁሉ ሆነና ጀንበርም ሳትጠልቅ፣ ፀሐይም ሳትገባ ሥራው ድንቅ ነው የሚል ድምጽ ሰማይ ምድር ሁሉ መወደስ ጀመረ። የጩኸቱ ድምድምታ ምን ይሆን? ብለን ተነሳን፤ እኛም ያኔ ጎኑን የተወጋው፣ እጆቹም ተቸነከሩ፣ ሄዷልና ሞቷል የተባለው አዳኙ ራሱ ያው መሢህ መሆኑን አወቅን። በፍርሃትም ያየነውን በመገረም ድንቅ ነው አልን። ከእላፋት ጋር አእላፋት ሆነን፥ ባሾፍንበት ከንፍራችን ከሙታን በኩር፣ የነገስታት ንጉስ፣ የጌቶች ጌታ፣ የምድር ሁሉ ባለቤት እርሱን አመሠገንን። ጨመር አድርገንም ተነስቷል በዚህ የለም መቃብሩ ባዶ ነው ተመልከቱ በዚህ የለም፤ በሚል ክብሩ ሁሉ በአርያም በምድር ይሁን ስንል ጣፋጭ መዓዛ ያለውን ዝማሬ ለታረደው በግ አቀረብን። ለአንባቢው መልዕክቴ በዚህ ወቅት ላይ የጥሞና ጊዜ ያጣህ እና ረፍት የሌለህ ሆይ “እርሱ ሰላም የሚሰጥ እረፍት ነውና በልብህ ታስገባው ዘንድ አሳሰብኩህ”። አሜን።[፩][፪][፫]
መልካም የጥሞና ጊዜ ይሁንላችሁ…..!
[፩] ከሚባለው በላይ ከደረሰበት መከራ አንጻር ይገርማል ጥቂት ሆና ትታየን ዘንድ አንባቢው ያስተውል።
[፪] ይደንቃል ስንል ከእውነት የሆነ መደነቅ እንዲሆን ሰሚው ከንግግል ባለፈ ከልብ በኾነ ፍቅር ትል እንደሆን አሳሰብኩህ።
[፫] ምንጭ፦ አጭር ማስታወሻ በወንድም David Yeshua, ያልታተመ በጽሑፍ ላይ ካለ መጣጥፍ የተወሰደ።