Author name: admin

የህፃናት ጥምቀት | Infant Baptism

ክፍል ፊ በወንድም ዮሃንስ ብዙ ሰዎች የህፃናት ጥምቀትን አስተምህሮ ለመቀበል የሚከብዳቸውና በተደጋጋሚም የሚጠይቁት ነገር ቢኖር እንዴት ህፃናት ማመን ይችላሉ? የሚለው ነው። በእርግጥ በጠቅላላ ይህንን አስተምህሮ የማያምኑ ሁሉ ቀዳሚ ምክንያታቸው “ህፃናት ማመን አይችሉም” የሚል ነው። መቼም ሁላችንም እንደምንስማማው ሰው ለመዳን የእግዚአብሔርን ቃል ሰምቶ ማመን አለበት። መጽሐፍ ቅዱስ ሰው ለመዳን ማመን እንዳለበት መሐከለኛ አስተምህሮው አድርጎ የሚያስቀምጠው ነገር ነው። ነገር ግን አንድ የምናውቀው ነገር ህፃናት ወንጌልን ብንሰብክላቸው ሰምተው ከዛም አሰላስለው የተነገራቸውን ተረድተውት ፤ በተገለጠም መልኩ እምነታቸውን አያሳዩም ወይም አይናገሩም። ስለዚህም ብዙዎች ከዚህ ተነስተው ህፃናት ሊያምኑ አይችሉም ብለው በማመን እነሱን ማጥመቅ ይከለክላሉ። በአጭሩ የዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ስህተት የሚጀምረው ራሳቸው ጥያቄ አድርገው ከሚያቀርቡት ከእምነት ምንነት ነው። እምነትን በትክክል በመረዳት ብቻ ይህን አረዳድ ማስካከል ይቻላል። እንግዲህ እምነት ማለት ሰዎች ከእግዚአብሔር በነፃ የቀረበላቸውን የተጨረሰና የተጠናቀቀ ድህነት የሚቀበሉበት እጅ ነው።(ይህንን በሌላ ጽሑፍ የእምነት ብቻ አስተምህሮና የቅዱሳት ሚሥጢራት አስተምህሮ ንፅፅር በስፋት አብራርቼ አስቀምጣለሁ።) በታሪካዊው ፕሮቴስታንቱ አስተምህሮ መሠረት እውነተኛ አዳኝ እምነት በሶስት መሠረታዊ ነገሮች ላይ የሚመሠረት ወይም የሚተረጎም ነው። እነርሱም እውቀት ፣ ፍቅር እና መደገፍ (Trust) ናቸው። አንድ ሰው ለማመን የሚታመንበት ነገር ሊቀርብለት እርሱንም በሆነ መልኩ ሊያውቅ፣ ሊረዳ ወይም ሊያስተውል ይገባል። በመቀጠልም ይህ አዳኝ እምነት በፍቅር የሚሰራ ነው። ማለትም ከፍቅር ባህሪ ጋር የተጋመደና የፍቅር ድርጊቶችንም የሚያፈልቅ ነው። ሶስተኛውና ትልቅ ዋጋ ያለው ደግሞ(Definitional Aspect) ደግሞ መደገፍ(Trust) ነው። ይህም ማለት እምነት በአማኙ ደካማነት ፣ አለመቻልና ባዶነት ላይ ተመስርቶ የሚታመነው አካል ባለው ጥንካሬ፣ ችሎታ፣ አቅምና ብርታት ላይ ራስን መጣልና መደገፍ ነው። ከዚህ የመደገፍ(Trust) ትርጉሙ አንፃር እምነት ሙሉ ለሙሉ ተቀባይ ነው እንጂ ሰጪ አይደለም ማለት ነው። እምነት የሚያድነውም በዚህ በተቀባይ ባህሪው ብቻ ነው። ይህንን እውነተኛ እምነት/Fides Directa/ ብለን እንጠራዋለን። እምነትን በዚህ መልኩ ከተረጎምነው ሌላው መረዳት ያለብን አንድ ልዩነት/Distiniction/ አለ። እርሱም Councious Faith እና Uncouncious Faith ናቸው። እንተርጉማቸው። Conscious Faith/አስተውሎታዊ እምነት/፦ ይህም አማኙ በውል ተረድቶትና አውቆት የሚይዘው እምነት ነው። ይህም አንድ ሰው ሾለ እምነቱ ያለውን ጥልቅ የሆነ አመክንዮአዊ ምልከታና ምክንያታዊ ግንዛቤን ያካትታል። Unconscious Faith/ደመ-ነፍሳዊ እምነት/፦ ይህም በአንድ ሰው ውስጥ ያለ ነገር ግን ገና በንቃት ወይም በዕውቀት ያልተገለጠ የእምነት ዓይነት ነው። ይህም ሾለ እምነት ያለን አመክንዮአዊ ትንታኔ ወይም ምክንያታዊ መረዳትን አይዝም። እነዚህን ሁለት ልዩ ባህርያት/Distinictions/ ህፃናቱ ጋር ሳንሄድ ከትላልቅ ሰዎች በመነሳት መረዳት እንችላለን። ለመጀመሪያው የእምነት አይነት ምንም የራቀ ማስረጃም አያስፈልግም። ለምሳሌ ይህን ጽሑፍ የምታነቡት አንባቢያን ለአፍታ ወደራሳችሁ ዞር ብላችሁ ስለእምነታችሁ ካስተዋላችሁ ካደረጋችሁ እርሱ በቂ ማስረጃ ይሆናችኋል። ሁለተኛውን የእምነት አይነት ግን አቅርበንም፣ አርቀንም በተለያዩ መንገዶች ልንመለከተው እንችላለን። ከቅርቡ ለመነሳት ያህል ለምሳሌ በቀን ውሏችን ውስጥ ሙሉ ለሙሉ ትኩረታችንን በሚወስዱ ስራና የተለያዩ ድርጊቶች በተወጠርንበት ሰአት አስተንትኖታዊ እምነት/ Councious Faith/ አይኖረንም። በዚህ ውስጥ የትኛውም ከራሳችን ውጪ ሙሉ ትኩረታችንን የሚወስዱ ድርጊቶች ሙሉ ለሙሉ ሊካተቱ ይችላሉ። ይህ የዕለት ተዕለት ኑሮዋችን ውስጥ የሚከናወን ከመሆኑ አንፃር ቀላሉና ቅርቡ ምሳሌ ይሆናል። ምናልባት ሰፋ አድርገን ከሩቁ ካየነው ደግሞ እውነተኛ እምነት የነበራቸውና የዳኑ ነገር ግን በአደጋ ምክንያት ራሳቸውን የሳቱ ወይም ሲብስ ኮማ ውስጥ የገቡ ሰዎችን መጥቀስ እንችላለን። በእርግጥ እዛም ሳይደርስ ሁላችንንም የሚያካትት ሙሉ ለሙሉ የፍቃድም/Will/ ሆነ የነቃ የአእምሯዊ ህላዌን/Intellect Conciousness/ የምናጣበት እጅግ ቅርብ የሆነውን የሌሊት እንቅልፍ በምሳሌነት ማንሳት እንችላለን። በእነዚህ ሁሉ ውስጥ ግን ምንም እንኳ አስተንትኖታዊ እምነት/ Councious Faith/ ባይኖረንም ግን እምነታችንም አይጠፋም። በአጭሩ እነዚህ ከላይ ያሉት ሁሉ ሰው የፍቃዱም ሆነ የመረዳቱ ችሎታዎች ሙሉ ለሙሉ ተግባራቸውን በንቃት በማይሰሩበት በዛ ሁኔታ ውስጥ ቢሆንም ግን እውነተኛ እምነት መኖርና መቀጠል መቻሉን የሚያስረግጡ ናቸው። ወደ መጀመሪያው ጥያቄ ስንመለስ ቀድመን መረዳት ያለብን ነገር “ህፃናት ማመን አይችሉም!” የሚሉ ወንድሞች በዚህ አገላለፃቸው በጭራሽ ህፃናት የማመን አቅምና ችሎታ የላቸውም(Capacity to Believe) እያሉን አይደለም። ምክንያቱም እነዚህ ክሂሎች ግዴታዊ ባህሪያት በማንኛውም ሰው ውስጥ የሚቀመጡ ሰው ሰው ለመሆኑ በባህሪያዊ ግዴታ የሚይዛቸው(Intrinsic Property) ናቸውና። ስለዚህ በብቸኝነት ለእውነተኛ እምነት እና ግዴታዊ ውሳኝ ቅድመ ሁኔታ አድርገው የሚያስገቡት ከላይ የተቀመጠውን አስተውሎታዊ እምነትን(Conscious Faith) ነው። እርሱም በቀጣይነት ያለንበትን ሁኔታ በመመርመር እና ምክንያታዊ በሆነ መንገድ ማስጨበጥ ነው። ነገር ግን ከላይ ከተቀመጡት ሁለቱ ልየነቶች የምንረዳው ለእውነተኛ እምነት (Fides Directa) አስተውሎታዊ እምነትን(Conscious Faith) በጭራሽ ውሳኝ ቅድመ-ሁኔታ(necessary condition) ሊሆን እንደማይችል ነው። ይህ ካልሆነ ግን በUnconscious Faith/ደመ-ነፍሳዊ እምነት/ ሾር በተዘረዘሩት ምሳሌዎች ውስጥ ያሉ አማኝ ሰዎችን በጠቅላላ ወደ ኢ-አማኒነት እየገለበጥን ልናስቀምጣቸው እንገደዳለን። ምክንያቱም ይህን አመለካከት እንደ ቅድመ-ሁኔታ ካደረግው ከእርሱ የወጣውን እምነትም ሙሉ ለሙሉ ስለሚጠፋ። ከዚህ ቀጥሎ መጨመር የሚያስፈልገን ነጥብ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለውን አንድ መፅሀፍ ቅዱሳዊ እውነት ነው። እርሱም እምነት ልሹ የእግዚአብሄር ስጦታ መሆኑ ነው። መፅሐፍ ቅዱስ መንፈስቅዱስ በሚሰጠው የቃሉ ብርሀን እና እርሱም ይዞት በሚመጣው ፀጋ እምነትን በነፍሳችን ውስጥ እንደሚፈጥር መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምረናል። እዚህ ላይ መሳሳት የሌለብን ይህ ማለት እግዜር ነው የሚያምንልን ማለት አይደለም። አማኞቹ እኛ ነን። ነገር ግን የምናምንበትን ልብ እንዲያምን የሚቀርፀውም ሆነ የምናምንበትን ያንን የእምነት ይዘት(content) የሚያቀርብልን መንፈስቅዱስ ነው ማለት ነው። መንፈስ ቅዱስ ይህንን ሾል እንዳይሰራ በብቸኝነት የሚከለክለው ነገር ደግሞ ተቃውሞና እምቢታ(Will full Rejection) ብቻ ነው። ህፃናት ግን መንግስተ ሰማይ የተወከለባቸው ፤ እኛንም እንኳን መንግስቱን ለመምሰል ወደ ኋላ ተመልሰን እነርሱን እንድንመስላቸው የተነገረላቸው ናቸው። መቼም ምሰሉ የተባልነው ቁመታቸውን አይደለም። ይህም ራሳቸውን አዋርደው የተሰጣቸውን ሁሉ ያለተቃውሞ የሚቀበሉ መሆናቸውን እርሱም እምነታቸውን(Fides Directa) እንጂ! ስለዚህ መንፈስቅዱስ ልክ በእኛ ውስጥ እምነትን እንደሚሰራ በእነርሱም ውስጥ ሊሰራ የማይችልበት ምንም ምክንያት የለም ማለት ነው። የእግዚአብሔር ጸጋና ሰላም ይብዛላችሁ።

የህፃናት ጥምቀት | Infant Baptism Read More »

ማቴዎስ 28፥19 እና ሰዋሰዋዊ ሙግት

በማቴዎስ 28:19 በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም የሚለው ሐረግ የአካል ሦስትነትን አያሳይም የሚሉ መናፍቃን ሙግት የሚንድ ሆኖ የሚቀጥ ነው። ምክንያቱም ከስም ባሻገር የአካላዊ ሶስትነትን ያሳያል። በአንደኛው መቶ ክፍለ ዘመን ውስጥ እንደተጻፈ የሚታመነው ዲዳኬ (ትምህርተ ሐዋርያት) ጽሑፍ ላይ ሾለ ጥምቀት ስርአት በማቴዎስ ወንጌል ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተላለፈውን ትእዛዝና ሐዋርያት በዛ ዘመን እንዴት እንደሚያጠምቁ ሲያብራራ እንመለከታለን፦ “…ስለ ጥምቀትም ረገድ እንዲህ አጥምቁ፤ ይህን ሁሉ በመጀመሪያ ከተናገርክ በኋላ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም በሕያው ውኃ አጠምቁ (“…βαπτίσατε εἰς τὸ ὄνομα τοῦ πατρὸς κι὜ τοῦ υἱοῦ κι὜ τοῦ ἁγίου πνεύματος…”)…….በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም ልሾ ላይ ሦስት ጊዜ ውኃ አፍስሱ…” [ትምህርተ ሐዋርያት ሾለ ጥምቀት ህግጋት][1] አንዳንድ ጸረ ስላሴያውያን የማቴዎስ ወንጌል 28:19 የስላሴን አስተምህሮ አያሳይም በማለት ክፉኛ ሲሞግቱ እንመለከታለን። ነገር ግን ይሄ አካሄዳቸው የበኩረ ጽሑፋቱን ቋንቋ ያማከለ ሙግት ፈጽሞ አይደለም። ይሄም የሚያሳየው የሰዋሰው ሙግት ላይ ምን ያህል ደካማ መሆናቸውን ነው። ይባሱን ብሎ ጽሑፉ በጥንታውያን ክታባት ላይ አይገኙም የሚሉም መጥተዋል። ለዛሬ እኛ በማቴዎስ ወንጌል 28:19 ያለው ጽሑፍ ላይ እናተኩር። ጥንታዊ ሰነድ የሆነው ዲዳኬ (ትምህርተ ሐዋርያት) የጥምቀት ስርዓትን በተመለከተ የአብ የወልድና የመንፈስ ቅዱስ ስም ከመጠቀሱም ባሻገር አካላዊ ልዩነቶች (Personal Distinction) እንዳላቸው በግልጽ ያሳያል። ይህም ማለት አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ እያንዳንዱ አካል እኔነት እንዳለው የሚያሳይ ክፍል ነው። የክፍሉን የሰዋሰው መዋቅር ከመመልከታችን በፊት አንድ ወሳኝ ህግ እንመልከት፦ በ1735-1813 ይኖር የነበረው የግሪክ ቋንቋ ሊቅ እንዲሁም ባለ ብዙ ዘርፈ ሙያ ባለቤት የሆነው ግራንቪል ሻርፕ ሾለ ውስን መስተኣምር አገባብ እና የአረፍተ ነገሩን አተረጓጎም ሒደት ላይ ባስቀመጠው ስድስት ህጎች መካከል በስድስተኛው ነጥብ ላይ እንዲህ የሚል መርህ እናገኛለን፦ “ሁለት ወይም ከዛ በላይ ተመሳሳይ ሙያ(case) ያላቸው ስሞች(የማዕረግ )፤ በ ‘እና/ካይ (κι὜)’ ተያይዘው፤ በስሞቹ መጀመሪያ ላይ ውስን መስተኣምር ካለ አረፍተ ነገሩ ሾለ ተለያየ አካል(person) የሚናገር ነው”[2] “πορευθέντες οὖν μαθητεύσατε πάντα τὰ ἔθνη, βαπτίζοντες αὐτοὺς εἰς τὸ ὄνομα τοῦ πατρὸς κι὜ τοῦ υἱοῦ κι὜ τοῦ ἁγίου πνεύματος”[Κατα Μαθθαιον 28:19] በዚህ ህግ መሰረት የማቴዎስ ወንጌል 28፥19 ያለው ክፍል ይሄንኑ ህግ አሟልቶ እንመለከታለን። አብ፣ ወልድ፣ መንፈስ ቅዱስ የሚሉት የማዕረግ ስሞች ተመሳሳይ ሙያ ያላቸው ነጠላ ስሞች(የቃል ክፍሉ Noun, የሙያ መደቡ Genitive case, የብዜት ቁጥሩ Singular) ስለሆኑ አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ የተለያዩ ማንነቶች እንደሆኑና ያልተጨፈለቁ አካላቶች መጠቀሳቸው በግልጽ ህጉ ይደግፍልናል። ይህ ደግሞ ስም ብቻ መጠቀሱን አይተን በቀላሉ እንድናልፍ የሰዋሰው ውቅረ ህጉ አይፈቅድልንም። በዚህም መስፈርት ከሄድን ከማቴዎስ ወንጌል በተጨማሪ በ2ኛ ቆሮንቶስ ም.13 ቁ.14 የሰዋሰው አወቃቀሩ ተመሳሳይ ነው የህጉን መስፈርት ያሟላል። ጸጋ ሰላም ይብዛላችሁ! ዋቢ ምንጮች

ማቴዎስ 28፥19 እና ሰዋሰዋዊ ሙግት Read More »

ቅድመ ኒቂያ አበው ትምህርተ ሥላሴ እና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ

ሰላም እንደምን ቆያችሁን በባለፈው ልጥፍ ማለትም በመጽሐፍ ዳሰሳችን የትምህርተ ሥላሴ ቀዳማይ አመንጪ ጉባኤ ኒቂያ አለመሆኑን በአጭሩም ቢሆንም አይተናል። ይህ አይነት አስተሳሰብ ላላቸው(ቅድመ ኒቂያ ጉባኤ ያሉት የቤተ ክርስቲያን አበው ሥላሴን  የሚገልጽ ነገር ፈጽሞ አላስተማሩም) ለሚሉት ትችት ታሪክን ካለማንበብ የመነጨ እንደሆነ እናስተውላለን። ይህንን ማሳያ ከሌሎች አበው አንጻር በማቅረብ እንዘልቃለን። የቤተ ክርስቲያን አበው ሾለ ሥላሴ የነበራቸውን መረዳት እዚህ ጋር አምጥቶ መጻፍ እጅጉን ብዙ ነው። ከእነዚህም መካከል ጥቂቱን እናጋራችሁ፦ 1)Clement of the Rome(30-95) ቅዱስ ቀለሜንጦስ የሐዋርያውን ቅዱስ ጳውሎስን ኤፌሶን ላሉት ምእመናን በጻፈው መልእክት ላይ በምዕራፍ 4 ከቁጥር 4 እስከ 6 ባለው ሐሳብ ተሞርክዞ የስላሴን አንድነትና ሶስትነት ሲገልጽ እንመለከተዋለን፦ “….አንድ አምላክ፤ አንድ ክርስቶስ፣ በእኛ ላይ የፈሰሰው አንድስ የጸጋው መንፈስ ያለን አይደለንምን? [1] ኤፌሶን 4፥4-6″…⁴ በመጠራታችሁ በአንድ ተስፋ እንደ ተጠራችሁ አንድ አካልና አንድ መንፈስ አለ፤ ⁾ አንድ ጌታ አንድ ሃይማኖት አንዲት ጥምቀት፤ ⁜ ከሁሉ በላይ የሚሆን በሁሉም የሚሠራ በሁሉም የሚኖር አንድ አምላክ የሁሉም አባት አለ።(——ኤፌሶን 4፥4-6) 2)Hippolytus of Rome(3rd ce. earlier)፦ በ3ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ የሮሙ ሂፖሊተስ ኖተስ(Noetus) ለተባለ የሰምርኔስ ክርስቲያን(Christian from Smyrna) ሂፖሊተስ ምንፍቅና ነው ብሎ ያመነበትን የፓትሪፓሻውያንን አመለካከት ሲያራምድ ለነበረው መናፍቅ ምላሽ በኖተስ ላይ የጻፈው ጽሑፍ ሾለ አስተምህሮተ ስላሴ እንዲህ ብሎ ሲሞግት እንመለከታለን፦ “…እንግዲህ የአብን መስተጋብራዊ ግንኙነትን፤ ፈቃዱንና አብም ከዚህ መንገድ ውጭ ሊመለክ እንደማይፈልግ አውቆ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለደቀመዛሙርቱ ይሄንን ትእዛዝ ሰጣቸው፦’እንግዲህ ሂዱና አሕዛብን ሁሉ በአብ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ስም እያጠመቃችኋቸው፥ ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው…'(— ማቴዎስ 28፥19-20) ከእነዚህም አንዱን ያጎደለ ሰው እግዚአብሔርን ፍጹም በሆነ መንገድ እንዳላከበረ ጭምር አሳይቶናል። ምክንያቱም እግዚአብሔር የሚከብረው በስላሴ በኩል ነው። አብ ፈቅዷልና ወልድ አደረገ መንፈስ ቅዱስም ተገለጠ ይቺም የአብ ቃል ናትና…”[2] 3) ጠርጡሊያኖስ ወይም ተርቱሊያኖስ (Tertullian 160-215) ፦ የጥንቷ የቤተ ክርስቲያን አባት የሆነው ጠርጡሊያኖስ በስላሴያዊ አስተምህሮት ላይ ለሚነሱ ኑፋቄዎች መልስ በመስጠትና ቤተክርስቲያን እምነት ላይ ከሚሰሩ አቃብያነ አባቶች መካከል አንዱ ነው። ለምሳሌ በመናፍቃን ሙግት ላይ ባነሳው በፕራክሲየስ (against praxeas) ለሞዳሊስት አራማጅ የሆነው የፓትሪፓሺያን(Patripassian) ሐሳብ አንስቶ እንዲህ ሲል በሙግቱ ላይ ጽፏል፡- “…ሶስቱ አብ፣ ወልድና መንፈሱ ናቸው። ሶስት ናቸው ነገር ግን በሁናቴ አይደለም በግብር እንጂ፤ በኑባሬም አይደለም በአካል እንጂ፤ በስልጣን ወይም በሐይል አይደለም በአይነት እንጂ ሆኖም ግን እግዚአብሔር አምላክ አንድ ኑባሬ፣ ስልጣን፣ ሐይል አለው ምክንያቱም በአካል፣ በግብርና በአይነት በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ የተገለጠ አንድ አምላክ ነውና…”[3] 4)አርጌንስ (Origen 185-254) ፦ አርጌንስ የተባለው አባት ከጠርጡሊያኖስ ትምህርት በመነሳት ከእርሱ ጋር በተመሳሰለ ሁኔታ ሾለ አስተምህሮተ ስላሴን ሲደግፍ እንመለከታለን። ነገር ግን አርጌንስ በስላሴ አካላት መካከል እንደ ጠርጡልያኖስ በደረጃ (ወይም በsubordination) ረገድ ልዩነት መኖሩን እንደሚያምን ከጽሑፋቱ እንመለከታለን። ሆኖም ግን ኦሪገን የጻፈው የመጀመሪያው መርህ (De Principiis or Peri Archon) እጅግ ጥንታዊ የሆነ የስነ መለኮት ትምህርት ግኝት እንደሆነ ሊቃውንት ያትታሉ። በጽሑፉም ላይ በስላሴ ማመን እንዴት አስፈላጊ እንደሆነ አትቶልን እናገኛለን፦ “…ስላሴ ዘላለማዊ ነው……….በእርግጥ ከስላሴ ውጭ ያሉ ነገሮች ሁሉ በጊዜና በእድሜ ሊለኩ ይችላሉ። ደግሞም ማንም ሰው ለመዳን ወይም “እንደገና ከእግዚአብሔር ለመወለድ” አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ እንደሚያስፈልገውና ከሥላሴ እምነት ውጪ ደህነትን የማያገኝበትን እንዲሁም ያለ መንፈስ ቅዱስ የአብ ወይም የወልድ ተካፋይ መሆንን የማይችልበትን ምክንያት ለምን እንደሆነ መጠየቁ ተገቢ ይመስለኛል። በእነዚህ ነጥቦች ላይ በመወያየት ለመንፈስ ቅዱስ፣ ለአብ እና ለወልድ ልዩ የሆነውን ተግባር(አስተምህሮ) መግለጽ እንደሚያስፈልግ አያጠራጥርም።”[4] 5)Gregory Thaumaturgus-Wonder worker/ጎርጎርዮስ ገባሬ ተአምራት ወመንክራት/(205–270)፦ “ሁሉም(አካላቶች) አንድ ምንነት፤ አንድ ባህሪዎት እና አንድ ፈቃድ አላቸው። ይህ ደግሞ “ቅድስት ስላሴ” ተብሎ ይጠራል። እንዲሁም እግዚአብሔር በንዑሳን ስሞች፣ በአንድ ምንነት ሶስት አካላት እና በአንድ አይነት ዘር (አካላቶቹ በባህሪ ደረጃ) የተገለጠ አምላክ ነው።”[5] ይሄን ካየን ከሁሉ በፊት የሌለ በኒቂያ ነው የሥላሴ ትምህርት የተጀመረው የሚልን ነገር በፍፁም እንደሙግት አንድም ሰው በክርስቲያኖች ላይ ሊያቀርብ በፍፁም አይችልም ማለት ነው። ሌሎች ተጨማሪ የቤተክርስቲያን አበው ላይ የሚነሳውን ተቃውሞ በባለፈው ልጥፋችን ጠርጡሊያኖስ በመቀጠል እንደምናስቀምጥ ነግረናችሁ ነበር። የሌሎቹንም አባቶች በክፍል በክፍል አደራጅተን የምናቀርብ ይሆናል። ጸጋ ሰላም ከሁላችን ጋር ይሁን ማጣቀሻ 1] /1Clement 46:6/ 2] /—Against Noetus Ch. 14./ 3] /Against Paraxeas 2/ 4] /De Principiis, book 1, chapter 3The Trinity according to Origen/ 5] Gregory Thaumaturgus, On the Trinity. ANF, VI:48

ቅድመ ኒቂያ አበው ትምህርተ ሥላሴ እና የቤተ ክርስቲያን ታሪክ Read More »

ትምህርተ ሥላሴ እና የቤተክርስቲያን ታሪክ

የመጽሐፍ ዳሰሳ [1] በመጀመሪያ ይህን ክፍል ለማጥናት ምሥጢረ ስላሴ ምን ማለት ነው!? የትምህርተ ሥላሴ ቀዳማይ አመንጪ መጽሐፍ ቅዱስ ነው። አንዳንድ ሥላሴን ስሩን ሳይዙት አውቀን ጨርሰናል በማለት ሲናገሩ አስተውያለሁ በዕውነቱ ያሳዝናል ለዚህም ነው በተለይ በአባቶች መምህራን የምሥጢረ ሥላሴ   በስፋቱና በትልቅነቱ ሲነገርም እንዲህ ይባላል፦ “..ምሥጢረ ሥላሴን ጠልቆ ለማወቅ መሞከር ባሕረ ውቅያኖስን በዕንቁላል  እየቀዱ ለመጨረስ እየጨለፉም ለመጨለጥ እንደ ማሰብ ነው ይላሉ…” እውነት ነው፤ ለሰው ከተሰጡ ስራዎች ምሥጥረ ሥላሴን ከመመርመር የሰፋና እና የከበደ የለም። ➝ ሆኖም ሾለ ሥላሴ በትክክል ማሰብ ለክርስቲያናዊ ኑሮ ዋንኛ ነገር መሆኑን አንባቢ ልብ ይበል። አይሁድ፣ ክርስቲያኖችና ሙስሊሞች አንድን አምላክ ሲያመልኩ፥ የሥላሴን ትምህርት በአንድ አምላክ ከሚያምኑ ሌሎች ሁሉ ክርስቲያኖች ይለዩዋቸዋል። ስለዚህ ክርስቲያን ለልሹ ብቻ ሳይሆን የራሱን እምነት ለሌሎች ለመግለጥም የሥላሴን ትምህርት ማወቅ ይገባዋል። ➝ሥላሴ የሚለው ቃል በመጽሐፍ ቅዱስአይገኝም። በግእዝ ቋንቋ ቃሉ ሦስትነት ማለት ነውና በትምህርተ መለኮት ጥቅም ላይ ሲውል..በአንዱ እግዚአብሔር ሦስት አካላት እንዳሉ ያሳስባል። በ2ኛው መቶ ዓመት የአንጾኪያ ጳጳስ የነበረው ቴዎፍሎስ በግሪክ ቋንቋ ትሪአስ እና ጠርጡሊያን በላቲን ቋንቋ ትርንታስ በእንግሊዘኛው ደግሞ TRINITY የሚለው ሲሆን፣ ቃሉ “Tri” ወይም “ሦስት” እና “Unity” ወይም “ኅብረት/አንድነት” ከሚሉት ሁለት የላቲን ቃላቶች የመጣና አንድ ቃል ሆኖ በተገናኝ የሚነበብ (“tri” + “unity” ) ነው። ሥላሴ የሚለው ቃልና ትምህርቱ እንደ መነጥር ሆነው በመፅሐፍ ቅዱስ ያለውን ትምህርት ጉልሕ ሆኖ እንዲታየን ያደርጋሉ እንጂ በእግዚአብሔር ቃል ላይ አዲስን ትምህርት አይጨምሩም። ትምህርተ ሥላሴ ለክርስቲያን ረቂቅ ፍልስፍናም አይደለም። ወደፊት እግዚአብሔር ቢፈቅድ ሥላሴን በደንብ እንመረምራለን። ወደ ዋናው ርዕሳችን ወደ ሚያንደረድር ሀሳብ ስንመለስ፦ ትምህርተ ሥላሴ እንደ አርዮስ ያሉ የመናፍቃን ጥቃት በቤተክርስቲያን ላይ ሲያደርሱ የመጠበቁ ሂደት ውስጥ ትልቅ ድርሻ ከነበራቸው አትናቴዎስ(Athanasius) አንዱ ቢሆንም ርእሰ ጉዳዩን በዳበረ መልኩ የተነተኑት ቀጰዶቃውያን አበው ናቸው። በመጀመሪያ ከዛ በፊት ቀጰዶቃውያን አበው እነማን ናቸው የሚለውን በጥቂቱ እንመልከት… ቀጰዶቃውያን አበው(Cappadocian Fathers) የሚባሉት ውስጥ፦ ትምህርተ ሥላሴ በቤተክርስቲያን ታሪክ ቅድመ ጉባኤ ኒቂያ አበው ግንዛቤአቸው ምን ነበር? ከላይ እንዳየነው ሥላሴ የሚለው ቃል በአዲስ ኪዳን ባይገኝም ትምህርተ ሥላሴ የነገረ መለኮት ዐብይ ርዕስ መሆኑን አይተናል። የአዲስ ኪዳን ጸሐፊዎች ምን ያህል ትምህርተ ሥላሴን እንደተረዱት ባናውቅም ግን፥ እግዚአብሔር ሦስት አካላት እንዳሉ አምነው የመለኮትን አንድነትንና የአካል ሦስትነትን ለትምህርታቸው መሠረት አደረጓቸው። የትምሕርተ ሥላሴ ቀዳሚ አመንጪ መጽሐፍ ቅዱስ ቢሆንም፣ በሐዋሪያት እግር ሾር የተማሩ ቀደምት የሆኑ የቤተክርስቲያን አበው ምን አሉ የሚለውን ጉዳይ መቃኘት፣ የተዛባ የታሪክ መረጃ ያላቸው ሰዎችን ለማቅናት ጠቃሚነት ስላለው ይህ ጽሑፍ ዳሰሳዊ ጥናት ስለሆነ የሁሉንም አበው እማኝነትና ትምህርት በክፍል አንድ በስፋት ማቅረብ ስለማይቻል በተወሰነው እንመለከታለን። 1) ጶሊቃርጶስ (Polycarp) :- በ70ዓ.ም ተወልዶ በ155 ዓ.ም ወይም በ160 ዓ.ም የሞተ፣ የሐዋሪያው ዮሐንስ ደቀ መዝሙር የነበረ እንዲሁም የሰምርኔስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት የነበረ ሰው ነው።..ይህ ሰው ትምህርተ ሥላሴን በተመለከተ እንዲህ ብሏል፦ “ሁሉን ቻይ እግዚአብሔር ሆይ…ዘላለማዊና ሰማያዊ በሆነ ሊቀ ካህናት በምትወደውና ባከበርኸው ልጅህ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ለአንተና ለእርሱም እንዲሁም ለመንፈስ ቅዱስ አሁንም ሆነ ለዘላለም ክብር ይሁን”[2] 2) ዮስጦስ ሰማዕት (Justin Martyr) ፦ የቤተክርስቲያን አቃቤ እምነት የነበረና የሰማዕትነትን ክብር የተቀናጀው ይህ አባት አባት በ100 ዓ.ም ተወልዶ በ165 ዓ.ም እንደ ሞተ ይገመታል። ይህ አባት ትምህርተ ሥላሴን በተመለከተ እንዲህ ብሏል፦ “የዓለማት ጌታ በሆነው በእግዚአብሔር በስመ አብ፣ በመድሐኒታችንም ኢየሱስ ክርስቶስ እንዲሁም በመንፈስ ቅዱስ በውሃ መታጠብን ያገኛሉ”[3] 3)አግናጢዮስ ዘአንጾኪያ (Ignatius of Antioch) ፦ የአንጾኪያ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት የነበረና በ98 ዓ.ም ወይም በ117 ዓ.ም እንደሞተ የሚገመት ክርስትናን ከመናፍቃን በመከላከሉ ዙሪያ ብዙ የጻፈ ዐቃቤ ክርስትና ነው። እንዲህም አለ፦ “በእምነትና በፍቅር፤ በወልድ፣ በአብና በመንፈስ ቅዱስ፤ በመጀመሪያው እና በመጨረሻው፤ ከሚያስደንቅ ጳጳስችሁ ጋር እናም እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ካሉ ዲያቆናት ጋር በሚገባ በጠበቀ መንፈሳዊ አክሊል የምታደርጉትን ሁሉ በስጋና በመንፈስ እንዲከናወን በጌታችንና በሐዋርያት ትምህረት እድትጸኑ አጥኑ። ክርስቶስ ኢየሱስ ለአብ በስጋው እንደተገዛለት እናም ሐዋርያት ለክርስቶስ፣ ለአብና ለመንፈስ ቅዱስ እደሚታዘዙ እናንተም ለጳጳሳችሁ እና እርስ በእርሳችሁ ተገዙ(ታዘዙ) በዚያን ጊዜ በስጋችሁም በመንፈሳችሁም አንድነት ይኖራችኋል።”[4] 4) ጠርጡሊያኖስ ወይም ተርቱሊያኖስ (Tertullian 160-215) ፦ አፍሪካዊ ዕቃቤ ክርስትና እንዲሁም የነገረ መለኮት ሊቅ ነው። ክርስትናን ከመናፍቃንና ከሌሎች ሐያስያን ለመከላከል ብዙ ጽፎአል፦ “አብና ወልድ ሁለት ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ደግሞ ሦስት መሆናቸውን እንገልጻለን። የቁጥሩንም ቅድመ ተከተል ከድነት አንጻር ነው….ይህም አንድነትና ሦስትነትን መሠረት አድርጎ ሦስቱንም ማዕከል ያደረገ ነው፤ እነርሱም አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ። [አብ፣ ወልድና መንፈስ ቅዱስ] ሦስት ናቸው….ነገር ግን በባሕርይ ሳይሆን በገጽ፣ በኀይል ሳይሆን ነገር ግን በዐይነት። በባሕርይና (Substance) በኀይል አንድ ናቸው፤ ምክንያቱም አንድ አምላክ ብቻ ስላለና ይህም ባሕርይ፣ ገጽና ዐይነት በአብ፣ በወልድና በመንፈስ ቅዱስ ዙሪያ ያለ በመሆኑ”[5] 5) አርጌንስ (Origen 185-254) ፦ የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን የነገረ መለኮት ምሁር ነው። አርጌንስ ክርስትናን በተመለከተ ብዙ የጻፈ ነው፦ “የእግዚአብሔር ቃል ወይም የእግዚአብሔር ጥበብ ጅማሬ አለው የሚል ማንኛውም ሰው፣ ቢያንስ እግዚአብሔርን መናቁ እንደሆነ ልብ ሊለው ይገባል…ምክንያቱም እግዚአብሔር ባለፉት ዓመታት ሆነ ዘመናት ከዚህ ውጪ ሊገመት በሚችልበት ጊዜ ሁሉ፣ እግዚአብሔር የጥበብ ባለቤት ነውና ይህ እውነት ለእግዚአብሔር አብ እንደሆነው ሁሉ ለወልድም ነው”[6] “እውነታው ይህ ከሆነ [መንፈስ ቅዱስ አሁን እንደ ሆነው ሁሉ ዘላለማዊ ካልሆነ፣ በዘመናት ውስጥ ዕውቀትን ገብይቶ መንፈስ ቅዱስን መሆን ከቻለ] መንፈስ ቅዱስ ለዘላለም ዓለም መንፈስ ቅዱስ መሆን ካልቻለ፣ እንደማይለወጠው አብና እንደ ልጁ ሁሉ መንፈስ ቅዱስ የሥላሴ አንዱ አካል ነው ማለት አይቻልም”[7] “የመለኮት ምንጭ ብቻ ሁሉን ነገር በቃሉና በምክንዩው የሚይዝ ከሆነ፣ በሥላሴ አካላት ውስጥ መበላለጥ ወይም መተናነስ የለም”[8] ሔሬኔዎስ(Irenaeus)፦ በ115 ዓ.ም ተወልዶ 190 ዓ.ም ሞተ፣ በልጅነቱ የሐዋርያው ዩሐንስ ደቀ መዝሙር ከነበረው ከጶሊቃርጶስ እግር ሼር የተማረ እንዲሁም የልዮን ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሳት የነበረ ሰው ነው፦ “ቤተ ክርስቲያን በዓለም ሁሉ እንዲሁም እስከ ዓለም ዳርቻ ድረስ ብትበተንም፣ ቤተ ክርስቲያን ከሐዋርያትና ከእነርሱ ደቀ መዛሙርት የተቀበለችውን የሚከተለውን መሠረተ እምነት ነው፦…..ሁሉን ቻይ የሆነ እና ሰማይንና ምድርን እንዲሁም ባሕርን በእነዚህም ውስጥ የሚኖሩትን ሁሉ የፈጠረ አንድ እግዚአብሔር፤ በእግዚአብሔር ልጅ በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ፣ ለድነታችን ሲል ትስብእት የሆነ፣ በመንፈስ ቅዱስ፣ የእግዚአብሔርን ዘመን በነብያቱ ያበሠረ እንዲሁም የተወዳጁ ጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ምጽአት፣ ከድንግል መወለድ፣ ሕማም፣ ከሙታን መነሣት፣ በአካለ ሥጋ ወደ ሰማይ ማረግ፣ “ሁሉን አንድ አድርጎ ለመሰብሰብ በአብ ክብር ከሰማይ መገለጥ፣ የሰው ልጆችን ሁሉ በአዲስ አካል ከሙታን ማስነሳት፣ ይኸውም ክርስቶስ ኢየሱስ ጌታችንና አምላካችን እንዲሁም አዳኛችንና ንጉሣችን መሆኑን፣ በማይታየው አብ ፈቃድ “በሰማይና በምድር ከምድርም በታች” ያለ ጉልበት ሁሉ እንዲበረከክለት፣ ምላስም ሁሉ ኀጢአት ብሎ እንደ ተሰዋ እንዲመሰክርለት ነው…”[9] ከጉባኤ ኒቂያ በፊት እንዲህ አይነት እምነት ያላቸው ከሆነ፣ የአስተምሮው ቀዳማይ አመንጪ ጉባኤ ኒቂያ ነው የሚባል ነገር ፈፅሞ የለም። ከሁሉ በፊት የሌለ በኒቂያ ነው የሥላሴ ትምህርት የተጀመረው ቢባል እንኳን ክርስቲያኑ ማህበረሰብ ከቀድሞው አስተምሮው ጋር የማይጣጣም ነው በሚል ተቃውሞ ለምን አላቀረበም? ለምንስ አላወገዘም? ኖሮስ ካለ ለምን በታሪክ ተዘግቦ አልተገኘም!? እነዚህን ከዚህ መጽሐፍ ዳሰሳ ካየን በተጨማሪ ጥናት ደግሞ በክፍል ሁለት ተመሳሳይ ሙግት አንስተን በጠርጡልያኖስ ላይ የሚነሱትን ሙግቶች የምንዳስስ ይሆናል። ማጣቀሻ 1] ትምህርተ ሥላሴ መሠረታውያን በዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ 2] Martyrdom of Polycarp, 14. ANF, I:42. 3] Justin, First Apology, LXI. ANF, I:183. 4] Epistle to the Magnesians, Chapter 13 5] Tertullian, Against Praxeas, 2. PL 2.156–57.፣ በቅንፍ ያለውን አይጨምርም። 6] De Princ. 1.2.; PG 11.132). 7] Alexander Roberts and James Donaldson, eds., The Ante-Nicene Fathers, Grand

ትምህርተ ሥላሴ እና የቤተክርስቲያን ታሪክ Read More »

የዮሐንስ ወንጌል አጭር ሐተታ

መግቢያ ➥የዮሐንስ ወንጌል በዘመናት መሐል በቤተክርስቲያን ተወዳጅነቱን ጠብቆ የቆየ መጽሃፍ ሲሆን በሌሎች ለዘብተኛ ምሁራን ደግሞ “አራተኛው ወንጌል” በመባል ይጠራል። ከጥንታዊት ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል አንዱ የሆነው ቀለሜንጦስ ዘእስክንድሪያ ደግሞ መንፈሳዊ ወንጌል በማለት አቆላምጦታል [1]፤ ይህንን ያለበትም ምክኒያት ዮሃንስ ወንጌሉን የጻፈው በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት ነው ብሎ ስላመነ እንደነበር የአውሳብዮስ ዘቂሳርያ ዘገባ ያሳያል። ወንጌሉ ምንም ያህል አከራካሪ ጉዳዮች ቢኖሩበት፤ ከዘመናውያኑ ሥነ መለኮት ምሁራን አንዱ የሆነው ኮሊን ክሩዝ ደግሞ “ኁልቆ መሳፍርት ለሌላቸው የክርስትና ትውልዶች መነሳሳት የፈጠረና በስርዓት ላጠኑት ሁሉ ታላላቅ ሽልማቶችን ያስታቀፈ” [2] በማለት መስክሮለታል። የጸሃፊው ማንነት ➥የወንጌሉን ትክክለኛ ጸሃፊ በተመለከተ የተለያዩ አመለካከቶች ቢኖሩም በሐዋርያው ዮሃንስ ስለመጻፉ የሚቀርቡ ሃሳቦች ከሌሎች ይልቅ ተጨባጭነት አላቸው። በቅድሚያ የመጽሃፉን ውስጣዊ ማስረጃዎች (internal evidences) እንመልከት። ጸሃፊው የአረማይክ ቋንቋ ችሎታ ያለው አይሁዳዊ ስለመሆኑ ለሚጠቅሳቸው አንዳንድ የእብራይስጥና አራማይክ ቃላት ትርጉም ማስቀመጡ ምስክር ነው፤ የአይሁድን ወግና ስርአት ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው መሆኑን የገዛ ጽሁፉ ያሳያል (ዮሃ 4፡ 9፣ 20)፤ ስለ መጀመሪያው ክፍለ ዘመን የእስራኤል መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ በትክክል እንደሚያውቅም ከወንጌሉ ላይ መረዳት ይቻላል (ዮሃ 1፡44፣ 2፡1፣ 4፡5፣ 4፡21፣ 9፡7፣ 11፡18፣ 18፡1)፤ እንደዚሁም የአይን ምስክርና የኢየሱስ የቅርብና ተወዳጅ ሰው እንደነበርም ይናገራል (ዮሃ 1፡14፣ 19፡35) [3]።ከኢየሱስ የቅርብ ደቀ መዛሙርት መሃል ያዕቆብ ብዙም ሳይቆይ ስለሞተ፤ እንዲሁም ጴጥሮስ ቶማስና ፊሊጶስ በሶስተኛ መደብ እየተጠሩ ስለተዘገቡ የጸሃፊው ማንነት ዮሃንስ የመሆኑ እውነታ የበለጠ ተአማኒነት አግኝቶአል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ያሉ ማስረጃዎችን (External Evidences) በአጭሩ ስንዳስስ ደግሞ የጥንት የቤተክርስቲያን አባቶችን ምስክርነት እናገኛለን።ከላይ እንደተመለከትነው አውሳብዮስ ዘቂሳርያ በዘገበው መሠረት የእስክንድርያው ቀለሜንጦስ ይህንን ወንጌል መንፈሳዊ ወንጌል ብሎ ጠርቶታል። ቀለሜንጦስ ወንጌሉን በዚህ ስም የጠራውም ዮሐንስ ወንጌሉን የጻፈው በደቀ መዛሙርት ተገፋፍቶና በመንፈስ ቅዱስ ተነሳስቶ እንደሆነ በማመኑ እንደነበረ አውሳብዮስ ጨምሮ ዘግቧል [4]። በመሆኑም ቀለሜንጦስ አራተኛው ወንጌል የተጻፈው በሐዋርያው ዮሐንስ እንደሆነ ያምን ነበር። 200 ዓ.ም አካባቢ እንደጻፈ የሚገመተው ኢራኒየስ ወንጌሉን የጻፈው የተወደደው ደቀ መዝሙር ዮሐንስ መሆኑንና የጻፈውም በኤፌሶን ሳለ እንደነበረ ተናግሯል [5]። በተጨማሪም የተወሰኑትን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ዝርዝር ይዞ የተገኘውና ከ 180-200 ዓ.ም ድረስ እንደተጻፈ የሚገመተው የሙራቶሪያን ጽሁፍ አራተኛውን ወንጌል በዮሐንስ እንደተጻፈ ይመሰክራል። ዮሐንስ ወንጌሉን እንዴት ጻፈው? ለሚለው ጥያቄ ይህ ጽሁፍ ተአማኒ ዝርዝር ባይኖረውም ወንጌሉ በተጻፈባቸው አመታት ውስጥ ጸሃፊው ዮሐንስ መሆኑ ይታመንበት እንደነበር ያሳያል [6]። በመሆኑም ከውስጣዊ ማስረጃዎች ጸሃፊው ፍልስጤም ምድር ውስጥ የሚኖር አይሁዳዊ መሆኑን፣ የኢየሱስ የአይን ምስክር መሆኑን፣ከአስራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት አንዱ መሆኑንና ከጽሁፉ ዝርዝሮች በመነሳት ጸሃፊው ዮሐንስ እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ስንረዳ ከውጫዊ ማስረጃዎች ደግሞ ወንጌሉ ለተጻፈበት ዘመን የሚቀርቡ አባቶችና ተጨማሪ ጽሁፎች የዮሐንስን ጸሐፊነት እንደሚደግፉ መገንዘብ ይቻላል። የዮሐንስ ወንጌል በራሱ በዮሐንስ መጻፉን የሚጠራጠሩ ምሁራን ቢኖሩም ከላይ ባነሳናቸው ማስረጃዎች መሠረት ጸሃፊው ሐዋርያው ዮሐንስ መሆኑን ተቃውሞ በብቃት የሚቆምና ተለዋጭ ጸሃፊ በርግጠኝነት የሚያቀርብ መከራከሪያ ግን ሊገኝ አልቻለም። የተጻፈበት ዘመንና ስፍራ ➥ልክ እንደ ጸሃፊው ማንነት ሁሉ በዘመናችን ምሁራን ዘንድ ወንጌሉ መቼ እንደተጻፈ የማያባራ ክርክር ይደረጋል። አንዳንዶች የተጻፈው በ2ኛው ክፍለ ዘመን መካከለኛ አመታት፤ ማለትም 150 ዓ.ም አካባቢ እንደሆነ በማንሳት ይከራከራሉ። ይሁን እንጂ የሥነ ቁፋሮ (Archaeology) ጥናቶች የሚያሳዩት የዮሐንስ ወንጌል የተጻፈው በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ መሆኑን ነው። የዮሐንስ ወንጌል የመጀመሪያው እደ-ክታብ Papyrus 52 የሚባል ሲሆን የምዕራፍ 18ን የተወሰኑ ክፍሎች የያዘና በ130 ዓ.ም አካባቢ እንደተጻፈ የሚገመት ቁራጭ ብራና ነው። ቀጥሎም ከምዕራፍ 1-14 ድረስ ያለውን አብዛኛውን ክፍልና የቀሩትን ምዕራፎች በከፊል የያዘው Papyrus 66፤ እንዲሁም ከምእራፍ 1-11 እና ከ12-15 ድረስ የያዘው Papyrus 75 ከጥንታዊ እደ ክታባት ይመደባሉ። እነዚህ እደ ክታባት ከሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ይመዘዛሉ [7]። እንግዲህ እስካሁን የሚታወቀው የመጀመሪያው የወንጌሉ ቅጂ (P 52) የተጻፈው እንደተገመተው በ 130 አካባቢ ከነበረ የመጀመሪያው ጽሁፍ የተጻፈው በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን መሆኑ ግድ ነው። ወንጌሉ የት ተጻፈ? ለሚለው ጥያቄ ደግሞ በቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያንና በኢራንየስ ትውፊቶች ላይ መደገፍ ግድ ይለናል። ቀለሜንጦስ እንደጻፈው ዮሐንስ ከፍጥሞ ደሴቱ ስደት ወደ ኤፌሶን የተመለሰው ንጉሡ ዶሚሽያን ከሞተ በኋላ (ከ 81-96) ሲሆን ኢራኒየስ ደግሞ ሐዋርያው እስከ ትራጃን ንግስና ዘመን ድረስ (ከ98-117) እዚያው ኤፌሶን እንደነበረ ይናገራል [8]። ይህም ወንጌሉን በዚያ ጊዜ (በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን መጨረሻ) በኤፌሶን ሳለ ጽፎታል የሚል ግምትን አሳድሯል። ስለዚህም የዮሐንስ ወንጌል ከ80-90 ዓ.ም ሐዋርያው ዮሐንስ በኤፌሶን ሳለ የጻፈው ወንጌል መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት አለው። የዮሐንስ ወንጌል ዋና ዋና ይዘቶች ➥በመጀመሪያው ምእራፉ ስለዋና ገጸ ባህርዩ ማንነት በዝርዝር ይናገራል። ይህም ገጸ ባህርይ በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋርየነበረው በፍጥረት ስራ ላይ ተሳታፊ የነበረውና በኋላም ሰው ሆኖ የመጣው ኢየሱስ መሆኑን ይናገራል። ➥እስከ ምእራፍ 12 ድረስ ሰፋ ባሉ ንግግሮችና በተአምራት የተገለጠውንና በልጁ ለሚያምኑ ሁሉ የዘለአለም ህይወት የሚሰጥአባቱን የተረከውን ኢየሱስን በተዋበ የመክፈቻ ንግግር መልክ እናገኛለን። ➥ከምእራፍ 13 – 20 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለቀጣይ ዘመናት ሲያዘጋጅ፣ ሲመክራቸውና ሲጸልይላቸው፣ እንዲሁም ስቃዩን፣ ስቅለቱንና ሞቱን እንዲሁም ትንሳኤውን ያስቃኘናል። ➥ምእራፍ 21 ተጨማሪ የትንሳኤውን ምስክርነቶች፣ ለጴጥሮስ የተሰጠውን ተልአኮ ከሞቱ ትንበያ ጋር፣ እንዲሁም የተወደደውን ደቀ መዝሙር ምስክርነት ያስቃኘናል [9]። የዮሃንስ ወንጌል ልዩ ባህርያት ➥በሶስቱ ተመሳሳይ ወንጌላት ዘገባ የኢየሱስ አገልግሎት ትኩረት ያደረገው በገሊላ ሲሆን የዮሃንስ ወንጌል ግን በብዛት የኢየሱስን የይሁዳና የኢየሩሳሌም አገልግሎት ያስቃኘናል። ተመሳሳዮቹ ወንጌላት የኢየሱስን ምሳሌያዊ ንግግሮች፣ የእግዚአብሔርን መንግስት የተመለከቱ ስብከቶቹን፣ እንዲሁም በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያደረጋቸውን ንግግሮች (ለምሳሌ ስለ ምጽዋት፣ ስለጋብቻና ፍቺ፣ ስለግብር ስለጭንቀት፣ ስለሃብት፣ ወዘተ…) ሲያስነብቡን የዮሃንስ ወንጌል ግን “እኔ… ነኝ” በሚሉ ሃረጋት በሚጀምሩ ኢየሱስ ስለራሱ በተናገራቸው ንግግሮች ይታወቃል። የዮሃንስ ወንጌሉ የኢየሱስ ንግግር ከሶስቱ ተመሳሳይ ወንጌላት በተለየ ከላይና ከታች፣ ብርሃንና ጨለማ… ወዘተ በሚል ሁለት ነገሮችን በተነጻጻሪነት በሚመለከት አጻጻፉ ይታወቃል። በዮሃንስ ወንጌል በተዘገበው የኢየሱስ አገልግሎት የሚገኙት ክስተቶች በሌሎቹ ወንጌላት ውስጥ አይገኙም። ማለትም የወይኑ ተአምር (2: 1-11)፣ ከኒቆዲሞስ ጋር ያደረገው ጭውውት (3:1-13)፣ የሳምራዊቷ ሴት ታሪክ (4:1-42)፣ የቤተዛታው ኩሬ ፈውስ (5:1-18)፣ የሰሊሆም መጠመቂያው ፈውስ (ምእራፍ 9)፣ የአላዛር ከሞት መነሳት (ምእራፍ 11)፣ ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ (13: 1-11)፣ እንዲሁም ኢየሱስና ጲላጦስ ያደረጉት ዘለግ ያለ ንግግር (18:28-19:22) የሚገኙት በዮሃንስ ወንጌል ብቻ ነው [10] የዮሐንስ ወንጌል ስነ መለኮት ➥የዮሐንስ ወንጌል በውስጡ ብርሃንና ጨለማ፣ ሞትና ህይወት የሚሉ ሐሳቦች በተነጻጻሪነት ተደጋግመው ተነስተዋል፤ ይህም የኖስቲክ እሳቤን የያዘ ወንጌል እንደሆነ እንዲታሰብ ምክንያት ሆኗል። ነገር ግን የኖስቲክ መምህራን ስጋን ሁሉ እንደ እርኩስ ነገር ስለሚቆጥሩ አምላክ በስጋ እንደመጣ የሚናገረው የዮሐንስ ወንጌል ከእነርሱ አስተምህሮ በተቃራኒ እንደሚቆም ለመረዳት አይከብድም[11]። ይህ ወንጌል ልዩ የሆነ ነገረ ክርስቶስን ይዟል፤ ይህንንም ኢየሱስ አባቱን ለመተረክ ከሰማይ የመጣ፤ ተግባሩንም ተወጥቶ ወደመጣበት የተመለሰ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በአግባቡ በማሳየት ገልጦታል። (ዮሐ 1:18፣ 3:13፣ 6፡33፣ 38)። በስጋ የተገለጠ አምላክ የሚልን ነገረ ክርስቶስ በዋናነት የምናገኘውም እዚሁ ወንጌል ውስጥ ነው። መንፈስ ቅዱስ በታሪካዊው ክርስቶስ (Historical Jesus) የተገለጠውን እውነት ወደ አማኞች በማምጣት ተግባሩ ተገልጧል። የዩሐንስ ወንጌል በቃልና በስራ ለእግዚአብሔር የመታዘዝን ስነ ምግባር በኢየሱስ በኩል ያስተምራል። ዋናውን የኢየሱስን ትእዛዝ ፍቅርንና ትህትናን በአማኞች መሃል ያስተዋውቃል (ዮሐ 13:14)። ይህንንም ኢየሱስ ራሱ በተግባር በማድረግ አስተምሯል (ዮሐ 15:12-14) [12] ወንጌሉ የተጻፈበት አላማ ➥ለዚህ ጥያቄ እንደ መልስ የሚቀርበው የመጀመሪያው መላ ምት ዮሐንስ ወንጌሉን የጻፈው ለሶስቱ ወንጌላት ተጨማሪ ድጋፍ ይሆን ዘንድ ነው ይላል። በዚህ መላ ምት መሠረት ሐዋርያው ከእርሱ በፊት የተጻፉትን ሶስቱን ወንጌላት በተመለከተ ጊዜ ይዘታቸው አላረካውም፤ ስለዚህም ወንጌሉን በዚህ መልኩ ጻፈው። ነገር ግን ወንጌሉ በሶስቱ ወንጌላት ላይ ጥገኝነት ባለማሳየቱ ይህ

የዮሐንስ ወንጌል አጭር ሐተታ Read More »

Scroll to Top