መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ/Sola scriptura/ – ክፍል 2

የማይሳሳቱትን መጽሐፍት ማን ሰጣችሁ? እንዴትስ አወቃችሁ?

በጥንቷ ሆነ በአሁኗም ቤተክርስቲያን ውስጥ ምናልባትም ዋና አከራካሪው ርዕሰ ጉዳይ ሚባለው የቅዱሳት መጽሓፍት ቀኖና ነው። በታሪካዊው ፕሮቴስታንቱም ላይ በተደጋጋሚ ከሚነሱና ዋና ከሚባሉ ጥያቄዎች መካከል ትላልቆቹን ሁለቱን ከፍለን እናንሳ፦

1) ያለ ቤተክርስቲያን ምስክርነት በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉት መጽሐፍት ራሳቸው እንዴት ትክክለኛና ስህተት አልባ መሆናቸውን እናውቃለን?

2) በምንስ ስልጣን ነው የቅዱሳት መጽሐፍትን ቀኖና ምንወስነው? የማይሳሳቱትን መጽሐፍት የማይሳሳት አካል ነው የሰጧችሁ?

በመጀመሪያ ይሄን ጥያቄ ለመመለስ ከኦርቶዶክሶች እና ከካቶሊካዊያን ጋር ምን ላይ እንስማማለን?

1) እስትንፋሰ መለኮት እንዳለባቸው

2) ቤተክርስቲያን ለቅዱሳት መጽሓፍት ምስክር ነች፥ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን ተቀብላለች። ስለዚህ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስን የማስተማር፣ የመጠበቅና፣ የመለየት ሃላፊነትና ስልጣን አላት።

Post reformation reformed dogmatics vol 2

  • እኚህ ምንስማማባቸው አበይት ርእሶች ሆነው ነገር ግን ከecclesiasticals ጋር ምንለይበት ምክንያት አለን። ለእነርሱም፦ ቅዱሳት መጽሐፍትን መቀበልና ማስተላለፍ ቤተክርስቲያንን የማትሳሳት(infallible) ያደርጓታል ለቤተክርስቲያን የተሰጡ ናቸውና በሚል።
  • ለእነዚ መሠረት ለጣሉት በሥነ አመክንዮ እና ታሪካዊ ሙግት እናቅርብ
  1. ሥነ አመክንዮአዊ ሙግት

ለማይሳሳት(infalliable) ለሆነ ነገር ምስክር ለመሆን የማይሳሳት(infalliable) መሆን ይጠበቅበታል ማለት አይደለም። ወይም አንድ አካል የማይሳሳት ነው(infalliable ነው) ተብለን ለመቀበል የእርሱ ምስክር ግዴታ የማይሳሳት (infalliable) መሆን የለበትም። ለምሳሌ፦ ነቢያት የእግዚአብሔርን ድምጽ ይሰሙ ነበር ታዲያ ሊሳሳት ማይችለውን የእግዚአብሔርን ቃል ሊሳሳት በሚችል አእምሮአቸው ተቀብለውታል። ክላሲካል ፕሮቴስታንት ይሄንን ጨመር አድርገው ሲያስረዱ

  • ቤተክርስቲያን ሊመጣ ስላለውና ስለመጣው መሲህ ምስክር እንደሆነው እንደ መጥምቁ ዮሃንስ ናት። እርሱ ሊመጣ ስላለው ሊሳሳት የማይችል መሲህና ስጋ ስለሚሆነው መለኮት ምስክር መሆኑ እሱን መሲህም ሆነ፤ ለዚህም ነገር እግዚአብሔር መጥመቁን ስህተት አልባ አድርጎ አልሾመውም። ልክ እንደዚሁ ቤተክርስቲያን እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት ልትሳሳት የማትችል ነች ማለቱ አግባብ አይሆንም።
  • አንጥረኛው ወርቁን ወደ ወርቅነት እንዳላመጣው ይልቁኑ ወርቁን እንደሚያስውብ
  • ሻማም ብርሃንን መያዙ ብርሃን እንደማያደርገው ይልቁኑ ብርሃኑን እንደሚጠብቀው እንደሚያደርግ
  • አይዛክ ኒውተንም ስበትን እንዳልፈጠረ ነገር ግን ያንን ስበት እንድናውቅ እንዳደረገ

እንዲሁ ቤተክርስቲያን በቀኖና ጊዜ ለመጽሐፍቱን የስልጣን ምንጭ እየሆነች ወይም ሊሳሳት የማይችል ነገር እያደረገች አይደለም። ይልቁንም የእውነትን አስተምህሮ እያስተማረችና እየጠበቀች እንጂ። ይህ የእኛ የክላሲካል/ታሪካዊው/ ፕሮቴስታንት መሠረቶቻችን ናቸው።

  1. ታሪካዊ ሙግት

ታሪካዊ ሙግታችን ደግሞ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ የመጽሐፍትን አይሳሳቴነት እንዴት እንደምንረዳ እንይ በተለይ ከቀኖና አንፃር፦

2.1 አዲስ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና

በአዲስ ኪዳን መጽሐፍት ቀኖና ጊዜ ቤተክርስቲያን እንደ መስፈርት አድርጋ ከተጠቀመቻቸው ነጥቦች ውስጥ፦

  • ሐዋርያት የክርስቶስ ደቀመዝሙር እና የእነሱ የቅርብ ወዳጅ
  • በሁሉም አብያተክርስቲያናት ዘንድ ተቀባይነታቸው ምን ነበር የሚለውና
  • ትክክለኛ ዶክትሪን ዋናዎቹ ናቸው።

በዚህ ሁሉ ግን ለመጽሐፍቱ ቀኖና የቤተክርስቲያን አይሳሳቴነት በየትኛውም ጉባኤያት ላይ ለቀኖና መስፈርት ሆኖ አያውቅም። የሚገርመውም ደሞ ጉባኤያቱ ራሳቸው Local እንጂ አለም አቀፍ አይደሉም። ታሪካዊ ነን በሚሉ ቤተክርስቲያን በመካከላቸው የቆየ አለመግባባት ስለነበር ለብዙ አመታት የተዋቀረና ስሙንሙነት ያለው ቀኖና አልነበራቸውም።

2.2 የብሉይ ኪዳን ቀኖና

ብሉይ ኪዳን መጻሕፍትን የተቀበሉት አይሁዳዊያን  ቢያንስ በ1ኛው ክፍለዘመን ጊዜ የተዘጋና የቆመ የመጻሕፍት ቀኖና ነበራቸው። ኢየሱስ ክርስቶስም በ ዮሐ5፥39 እና በሉቃ24፥44 ላይ ካለው ንግግሩ የታውቁ የህግና የነቢያት እንደነበሩ መናገር ይቻላል። ይሁንና እነዚህ አይሁዳዊያን መጽሐፍቱን እንደ የማይሳሳቱ አድርጎ ለመቀበል(infallible accept) ለማድረግ ምንም አይነት የማይሳሳት(infalliable) ሥልጣን ያለው አካል ሲጠቀሙ አናይም።

እንደሙግቱ ከሆነ እነዚህ አይሁዳዊያን infallible የሆኑ የብሉይ መጽሐፍትን ስለተቀበሉ እነሱም የማይሳሳቱ(infallible) መሆን አለባቸው? ይሄ እንኳን ቀርቶ ሻገር ብለን ስናይ እኛ ሁላችን ጌታን ለማመን የማይሳሳት እውቀት(infalliable knowledge) እንኳን የለንም። ሊኖረንም አይገባም።

ይሄ አጠቃላይ ሙግታችን ሥነ አመክንዮን እና ታሪካዊውን ክርስትና የሚጠብቅ ሙግት ነው። ስለዚህ የማይሳሳቱ መጻሕፍት ለመቀበል ሌላ የማይሳሳት ነገር(infallible) መሆን የለበትም። ይልቅ(Falliable list of infallible books) ማለታችን ታሪካዊ ሃቅ ነው። እኛም ይህንን ለመቀበላችን ምክንያት ብዙ ማለት ይቻላል። በአጭሩ ከክላሲካል ፕሮቴስታንት መሠረቶች መጽሐፍ ቅዱስን ብቻ ከመቀበል ውጪ ሌላ አማራጭ የለም። እግዚአብሔር ይርዳን!

ለሌሎች ያጋሩ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top