“ጣዕመ ዜማ የሌለው እንቢተኛ ልብ…!”

መናፍቃን እና እንቢተኛ ልብ አንድ ናቸው። ሁለቱም ስተው ሳሉ ጭብጨባ ይሻሉ፤ መናፍቅ ሁሌ የሳተ ስለሆነ ከቅዱሳት መጽሐፍት መውጣቱ በቀላሉ ያሳብቅበታል። እንቢተኞቹ ግን ተበጥረው ከመናፍቃኑ መለየቱ የሰሚው ድርሻ ነው። በዚህች አጭር ጽሑፍ ግን የምታደምጥ እና የምትሰማ አንባቢ ሆይ ዕቡይ[፩] ልብ ያላቸውን ሰዎች በዚህ ለያቸው፦ “የቅዱሳት መጻሕፍት ትርጓሜ ቃናው ጠፍቶባቸው፤ አቃቢነ ክርስትና ዕቡይ ሰው ልሁን ልደመጥ ማለታቸው መሠረታዊ መለያቸው ነው። በመጨረሻም አንባቢ ሆይ..! ያው ዕቡይ ዕቡየ ልብ ነው። ዕቡየ መንፈስም።[፪] እኒህን ዕቡያን ከመናፍቃኑ ለመቆንጠር ቢያዳግትም…. ሥነ-ምግባራቸውን በሚያስተምሩት አስተምህሮ ከቅዱሳት መጽሓፍት እና ከቤተክርስቲያን ትምህርት አፈንግጦ ወጥ መሆናቸውን በጩኸቱ፣ በሥነ-ምግባሩ እና በሚያደርገው ክዋኔ ለክተህ ታውቅ እንደሆነ እወቅ።[፫]

[፩] በቁሙ ትቢተኛ፣ ኵሩ፣ ልቡ ያበጠ፣ የተነፋ፡፡ ምንጭ፤ መጽሐፈ ሰዋሰው ወግስ ወመዝገበ ቃላት ሐዲስ (ኪዳነ ወልድ ክፍሌ)

[፪] ኦ ዘያነብብ!! በእለ ምግባሮሙ ወበስብከቶሙ እም ቅዳሳት መጻሕፍት ወ ትምህርተ ቤተክርስቲያን አእምር ከመ ለሊሆሙ ውጉዛን ውእቶሙ!

[፫] Tertullian,De praescriptione haereticorum (On the prescription of heretics), Chap. 43፡ You can judge the quality of their faith from the way they behave. Discipline is an index to doctrine.

[፬] Erasmus, Paraphrase On Matthew, Chap. 7፡ “If you observe their lives and character more attentively, you will find them to be self-pleasing, everywhere serving their own advantage, arrogant, vindictive, envious, disparaging, thirsting for glory, often both devoted to their bellies and acting completely in their own interests, rather than in the interest of the flock or of the gospel.”

ለሌሎች ያጋሩ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top