መሬትን ተሸካሚው ፍጡር  (“አል-ኑን/النون”)

በእስልምናው አስተምህሮት ውስጥ አፈታሪካዊ እና ተረታዊ ከሆኑት ታሪኮች መካከል አንደኛው ግዙፉ እስላማዊው አሳ ነባሪ ( الحوت الإسلامي ፣ አል-ሁት አል-ኢስላሚ) ይሄም ፍጡር ምድርን በጀርባው እንደሚሸከም የተገለጸለት  አፈታሪካዊው ፍጡር ነው፡፡ ታዳ  ይሄ እስላማዊው አውሬ/አሳነባሪ(አል-ሁት/ٱلْحُوتِ) በቁርአን ላይ “ምድር ተሸካሚ አሳ” ወይም “አል-ኑን/النون” ተብሎ ተጠርቷል። ቁርአኑ ስለዚህ ፍጡር ግልጽ በሆነ ሁኔታ አላስቀመጠልንም። በዚህም ምክንያት በአንዳንድ የሙስሊም ሊቃውንቶች መካከል እስካሁኑ ሰአት ድረስ ያልተፈታ ትልቅ ንትርክን የፈጠረ ለዘመናዊው ሳይንስ ጥናቶች እንግዳና አጠያያቂ የሆነ ጉዳይ ነው። እኔም ስለዚህ ፍጡር ጉዳይ በስፋት በመመልከት አንዳንድ እስላማዊ ጽሁፎችን ማለትም ሐዲሳትን እና የተለዩ ተፍሲራትን እያገላበጥን ለማሳየት ቀርቤያለሁ።

➙ ከላይ በጨረፍታ ለመመልከት እደሞከርነው “አል-ኑን/النون” በውሀ ውስጥ ከሚኖሩ የአሳ ዝርያዎች መካከል አንዱ ነው። በቁርአን በሱረቱል አል-ቀለመ በአንደኛው አያት ላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን። ይሄንን አያት በእስልምናው ማህበረሰብ ውስጥ እጅጉን እውቅና ካላቸው የቁርአን ተፍሲሮች (ኢብን-ከሲር፣ አል-ቁርጡቢ፣ ጃለለይን እና አት-ጠበሪ) እንደሚያስረዱን ከሆነ “ኑን” የሚባለው ግዙፍ አሳ ነባሪ እንደሆነና ምድርን የተሸከመ ፍጡር እንደሆነ ይነግሩናል።

አል-ቀለም 68:1
نٓۚ وَٱلْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَ
ነ.( #ኑን)፤ በብርእ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት፡፡

ኢብን ከሲር አል-ቀለም 68:1 ተፍሲር፦
ታላቁ ሙፈሲር ኢብን ከሲር በተፍሲሩ ላይ ስለ ኑን ሲናገር፦ አላህ ‹ ኑን› የተባለውን ከፈጠረ በኋላ ምድር በኑን ጀርባ ላይ እንደዘረጋ ይናገራል፡፡ ከዛም ተረቱ ይቀጥላል #ኑን የሚባለው ፍጡር ደነበረ ወይም ተረበሸ ይለናል። በዚህ መሀል ምድር ማረግረግ ወይም መንቀጥቀጥ ጀመረች። አላህ ለዚህ ችግር ሲል ተራሮችን ፈጠረ። እነዚህም ተራሮች ምድር እንዳትነቃነቅ እንደ ችካል ቸከላቸው ይለናል። እንደውም በቁርአን 78:7 ላይ “…ጋራዎችንም(ተራሮችን) ችካሎች አላደረግንምን(وَٱلۡجِبَالَ أَوۡتَادًا)?)…”  አላህ ተራሮችን የቸከላቸው የመሬትን መንቀጥቀጥ ለማስተካከል እንደሆነ ተፍሲራት ይነግሩናል(ጃላለይን, ኢብን ከሲር ተፍሲር)። ምን ይሄ ብቻ አሁም አፈታሪካዊ ተረቱ አላበቃም አል ባግሃዊ እና ሌሎች የሙስሊም ሙህራኖች እንደተናገሩት በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ ሰባቱ መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል ብለው ያስባሉ። እስቲ ይሄን ታሪክ ከኢማም ኢብን ከሲር ተፍሲር በተወሰነ መልኩ እንመልከት፦

“…ከዚያም አላህ ‹ኑን› የተባለውን ከፈጠረ በኋላ ሰማይ የተፈጠረበት ጭስ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ከዚያም ምድር በኑን ጀርባ ላይ ተዘረጋች፡፡ ከዚያም ኑን ስለደነበረ ምድር ማረግረግ ጀመረች፤ ነገር ግን (አላህ) ምድርን እንዳትንቀሳቀስ አድርጎ በተራሮች ቸከላት…

“ኢብን አቡ ኑጃኢህ እንደተናገረው ኢብን አቡ በኪር በሙጃሂድ እንዲህ ተብሎ ተነግሮት ነበር፣ “ኑን ከሰባቱ መሬቶች በታች የሚገኝ ታላቁ አሣ እንደሆነ ይነገራል፡፡” በተጨማሪም አል ባግሃዊ (አላህ ነፍሱን ያሳርፋትና) እንዲሁም ሌሎች ሐታቾች እንደተናገሩት በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ ሰባቱ መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል፡፡…”[1]

ኑን ለሚለው ቃል ትርጓሜ ሲያስቀምጥ ደግሞ “…ኑን የሚባለው ትልቅ አሳነባሪ ነው(Nun is a big whale/نۤ حوت عظيم)…” በማለት ኢብን ከሲር ትንታኔውን አስቀምጧል።[2]

አል-ቁርጡቢ ተፍሲር 68:1 
نۤ> الحوت الذي تحت الأرض السابعة>
"…<ኑን>ከሰባተኛው(السابعة) መሬት(الأرض) በታች(تحت) የሚገኘው አሳ ነባሪ(الحوت) ነው…."[3]

በአል-ቁርጡቢ ተፍሲር መሰረት ” ኑን” የሚባለው ከሰባተኛው  መሬት በታች የሚገኝ አሳ ነባሪ እንደሆነ ይነግረናል። ልብ በሉ “…ከሰባተኛው(السابعة)…” ሰባት ምድር እንዳለም ከላይ በኢብን ከሲር ተፍሲር ላይ ተመልክተናል። እነርሱም ተደራራቢ እንደሆኑ “ታሐት(تحت)” ወይም “ከታች/ከስር” የሚለው ቃል ያስረዳናል።

ተፍሲር አት-ጠበሪ 68:1
አት-ጠበሪ በሱረቱል አል-ቀለም 68:1 ላይ ማብራሪያ ሲያስቀምጥ እንዲህ ብሏል፦
“…هو الحوت الذي عليه الأرَضُون…”
“…ሰባቱ ምድሮች የተቀመጡበት ፍጡር አሳ ነባሪ(الحوت) ነው…”[4]

በእስልምናው ኮስሞሎጂ መሰረት አላህ ሰባት ሰማያትን እንደፈጠረ ሁሉ ሰባት ምድሮችንም ፈጥሯል(Quran 65:12)።

እነዚህም ጠፍጣፋ ምድሮች በአሳ ነባሪው ላይ ተደራርበው ተቀምጠው እንደሚገኙ ጥንታዊ የሙስሊም ሊቃውቶች ይነግሩናል።

ተፍሲር አል-ከቢር(አር-ረዚ)/tefsir Al kabir(by Ar-Razi)፦

"…بالحوت الذي على ظهره الأرض وهو في بحر تحت الأرض السفلى…"

በዚህም ተፍሲር ላይ በጀርባው ምድር የሚሸከመው ዓሳ ነባሪ እንደሆነና አል-ከቢር እዚህ ዓሳ ነባሪ ጀርባ ላይ ሚዛናዊ የሆኑ ጠፍጣፋ መሬቶች እንዳሉ  ይነግረናል፡፡[5]

ተፍሲር አል-ቃዲር/Tafsir Al-Qadir (by Shawkani)

ተፍሲር አል-ቃዲር/Tafsir Al-Qadir (by Shawkani)

ይህ ተፍሲር ከ 18 ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ዓለም ዓሳ ነባሪ ጀርባ ላይ ተሸክሟል የሚል ሀሳብን በመደገፍ ያረጋግጣል።

"….ምድርን የተሸከመው ፍጡር አሳ ነባሪ/الحوت ነው….."/Fath Al-Qadir on 68:1__[6]

ሐዲስ ከኢብን አባስ (ቱርጁማን ኡል-ቁርአን/ترجمان القرآن)
(ሐዲስ ከአት-ጠበሪ)

ኢብን አባስ እንደተናገረው፦አላህ የፈጠረው የመጀመሪያ ነገር ብእርን  ስለነበረ “ጻፍ!” አለው፡፡ እናም እስከ ሰዓቱ (የፍርድ ቀን) ድረስ ምን እንደሚሆን ጽፏል፤ ከዚያም ኑንን ከውሃ በላይ ፈጠረ ከዚያም ምድርን በእርሱም ላይ ተጫነች፡፡(ታሪኽ አት-ታባሪ) [7]

ይህም ሀዲስ(ትረካ) በሀዲሳት ሰንሰለት  ትክክለኛ(ሰሒህ/صحيح) ትረካ ተደርጎ ተቆጥሯል፡፡[7] መሐመድ ለኢብን አባስ ዱዓ (ጸሎት) ስላደረገ አላህም የቁርአንን ትክክለኛ አተረጓጎም ያስተምረው ነበር፡፡እንዲሁም ኢብን አባስ (ቱርጁማን ኡል-ቁርአን/ترجمان القرآن) “የቁርአን ተርጓሚ” ተብሎ ተጠርቷል ፣ ምክንያቱም ስለ ራእዮች ትርጓሜ (ቃል በቃል መተርጎም) የሚሰጥና ጥልቅ ዕውቀት ያለው ሰው ነበር።

ኢብኑ ዐባስ (ራአ) እንደተናገሩት፦
ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) አቅፈውኝ “አሏህ ሆይ! የመጽሐፉን (ቁርአን) እውቀት አስተምሩት ፡፡ ”(ሳሂህ ቡኻሪ 9:92:375)

ታድያ ይህ በቁርአን ጥልቅ እውቀት ያለው አሊም ተራራዎቹ በቁርአን ውስጥ እንደ ችካል እንዴት እንደተደረጉ የእርሱ ትረካ ያስረዳል፡፡ ምክንያቱም በባህላዊው እስላማዊ የኮስሞሎጂ መሠረት ምድር ከዓሣ ነባሪው ጀርባ ላይ ትነቃነቅ (ትንቀጠቀጥ) ስለነበረ አላህ ምድርን ዓሣ ነባሪው ላይ ተረጋግታ እንድትቀመጥ ተራሮችን እንደ ችካል እንዳደረጋቸው በግልጽ ሁኔታ ተርኮልናል፡፡

በመጨረሻም ከዚህ ሁሉ መረጃዎችና ማስረጃዎች የምንረዳው ነገር ቢኖር አላህ ሰባት መሬቶችን ፈጥሮ በአሳ ነባሪው(“አል-ኑን/النون” ) ጀርባ ላይ ደራረቦ በማስቀመጥ ከዛም አሳ ነባሪው(“አል-ኑን/النون” ) ሲደነብር መሬት እዳትነቃነቅ በተራሮች በመቸከል እንድትረጋጋ አድርጓል። ይባስ ብሎም በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ ሰባቱ መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል ብለው በማሰብ ይህ ለሳይንስና ለእውነታ ሆድና ጀርባ የሆነን ነገር ከአንዳንድ የመሰለኝን ልናደርግ ከሚሉ ፈላስፋዎች ቀጥታም ሆነ ተጨማምሮበት የተቀዳ አፈታሪክን የአምላክ መገለጥ ነው ብሎ መቀበል በጣም ሞኝነት ነው። አንዳንድ የዘመኔ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ስኮላሮችና ዳኢዎች ይሄ ነገር አልዋጥ ሲላቸው የውሸት የትረካ ሰነድ ወይም አምላካዊ ንግግር የሆነ ሀሳብ አይደለም ይሉናል።[8] ነገር ግን አይኑ የፈጠጠ በድሮ ዘመን በነበሩት የእስልምና ሊቃውንቶች መካከል ተቀባይነትን ያተረፈ ታሪክ እንደሆነ ከተፍሲራትና ከሐዲስ ለመመልከት ችለናል። ይሄን የመሰለ ተረትና አፈታሪክ ታቅፈው ነው እነ ዶክተር ዛኪር ናይክና ቢጤዎቹ ቁርአን ከሳይንስ ጋር አይጣረስም የሚሉን። በመሰናበቻዬም አንድ ነገር ተናግሬ ልደምድም፦ እውነት ቁርአን የፈጣሪ ንግግር ነውን? ከሆነስ ለምን ከሐቅና ከሳይንስ ጋር ላይስማማ ሊጣረስ ቻለ? እውነትን ፈልጉ እውነትም አርነት ያወጣችኋል።

ማጣቀሻዎችና ማስፈንጠሪያዎች
ለሌሎች ያጋሩ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top