ጥያቄ፦ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻን(Sola Scriptura) ተቀብሎ መቀጠል የቤተክርስቲያን ሥልጣናዊነትን እና የአበውን ጽሑፍ ባለስልጣንነትን እንዳንቀበል ያደርጋል። አይደል?
መልስ፦ ኧረ በፍፁም! ይህን እንድንል ትንሽ ክፍተት እንኳን አይሰጠንም። ምክንያቱም የመጽሐፍ ቅዱስ ብቻና አይሳሳቴው ባለስልጣን ነው የሚለው አስተምህሮ እነዚህን ጨምሮም ነው፦
➙ ቤተክርስቲያን ባለስልጣን ነች።
➙ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ስንልም የአበው ክታባት ባለስልጣን አድርገን ነው።
ይህን ስንል ግን ሊሳሳት የማይችልና የሁሉ መመዘኛ ባለስልጣን የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን አምነን ነው። ለዚህም ነው አውግስጢኖስ እንዲህ በማለት የተናገረው፦
If you discover in my writing anything false or blameworthy, you may know that it is bedewed by a human cloud, and you may attribute that to me as truly my own.[1]
ስለዚህ እነዚህ መጻሕፍት ማለትም የአበው ክታባት ሕጸጽ ከሌለባቸው (infallible & inerrant) ከሆኑ ከቅዱሳት መጻሕፍት ቀጥሎ ክብር የሚሰጣቸው መጽሐፍት ናቸው።
ጥያቄ፦ ለዚህ ንግግርህ የአዲስ ኪዳን ድጋፋት አለህ?
መልስ፦ አዎ። ጌታ ኢየሱስ ካደረገው እና ካስተማረው ማሳየትና መጥቀስ ችላለሁ።
ለምሳሌ፦
ማቴዎስ 23
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ በዚያን ጊዜ ኢየሱስ ለሕዝቡና ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ብሎ ነገራቸው፦
² ጻፎችና ፈሪሳውያን በሙሴ ወንበር ተቀምጠዋል።
ጌታችን በማቴዎስ 23:2-3 በሙሴ ወንበር ላይ ስላሉ ጻፎችና ፈሪሳውያን ለተናገሩት ቃል ለቃላቸው መታዘዝ እንደሚገባ ያስተምራል።(ይሄም ደሞ በዘመኑ ሥልጣናዊ መሆናቸውን ያሳያል። ለዛም ሥልጣን መታዘዝ እንዳለብን ይናገራል።)
ይህን አይተን ረሱ ጌታችን በማቴዎስ ምዕራፍ 15፥1-39 ላይ ጻፎች እና ፈሪሳውያን የደነገጓቸውን መመሪያዎች ከዋናው ከመጽሀፍ ቅዱስ ማዕከላዊ ትምህርት ጋር ስለተቃረኑ ይቃወማቸዋል።(ይህ ደሞ በመጀመሪያው ክፍለ ዘመናት ከመጽሐፍ ቅዱስ ሥልጣን በላይ የሆነ ግዛት እንዴሌለ ያሳየናል።
መልሴን በአጭሩ ሳስቀምጠው፦
መነሻ1፦ ጻሕፍት እና ፈሪሳውያን ሥልጣናዊ ናቸው።
መነሻ2፦ ይህ አንድ አካል ሥልጣን አለው ማለት ግን የግድ ሊሳሳት የማይችል ሥልጣን(ከመጽሐፍ ቅዱስ እኩል የሆነ) ነው ማለት ግን ፈጽሞ አይቻልም።
ስለዚህ
ድምዳሜ1፦ ስለዚህ ይህ ሥልጣናዊው አካል ራሱ በመጽሐፍ ቅዱስ ይመዘናል። ልክ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳደረገው።
ድምዳሜ2፦ እነዚህ መዛኞቹ ጌታችንን ራሱ የጠየቁት እና የመዘኑት በመጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ የሚያሳየው በዘመኑ በእነርሱ አስተሳሰብ መጽሐፍ ቅዱስ የበላይ ባለስልጣን መሆኑን ጥቂት የሚያሳይ ፍንጭ ነው። በዚህ ክፍል ግን ጌታችን የበላይ ባለስልጣን ያደረገው ራሱ በነብያቱ በኩል የተናገረውን የራሱን ቃል በሕዝቡ ዘንድ ነው።
በመጨረሻም ድምዳሜ1 እና ድምዳሜ2፦ መጽሐፍ ቅዱስ የማይመዘን መመዘኛ ነው። ይህ ማለት ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ማለት ነው። አንተም ስትጠይቅ እኛ የምንለውን መጽሐፍ ቅዱስ ባለሥልጣን ነው ስንል ሌሎች ባለስልጣናንነታቸውን መካድ ማለት አይደለም። ይልቅ የማይመዘነው ብቸኛ የማይሳሳት መመዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ ነው ማለት ነው።
መልስ፦ እሺ። አሁን የእኛን እሳብ ተረዳህ?
ጥያቄ፦ ይቀጥላል…
ማጣቀሻ
Augustine, Letter 19 (To Gaius):