ሥነ አመክንዮአዊ ተቃርኖ በመጽሐፍ ቅዱስ አይሳሳቴነት – ክፍል 2

ለዘብተኛ ምሑራን ሆኑ ከክርስትና ውጪ ባሉ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ህጸጽ አልቦነትን በዚህ መልኩ ሲቃወሙ እናያለን፦
መንደርደሪያ አንድ፦ በእጆቻችን ላይ ህጸጽ አልቦ የሆኑ እደ ክታባት የሉንም
መንደርደሪያ ሁለት፦ እደ ክታባት ቅዱሳት መጻሕፍት ናቸው[¹]
ስለዚህ: መጽሐፍ ቅዱስ ህጸጽ አልባ አፊዎተ ቃለ እግዚአብሔር አይደለም።
(ማሳሰቢያ የሁለተኛው አዋጅ አጽዕኖት ከክርስቲያናዊ እደ ክታባት ያፈነገጠ ተደርጎ እንዳይታሰብ)

በመጀመሪያ ይሄን ሙግት ርዕቱ ነው ወይስ አይደለም? ከማለታችን በፊት ህጸጽ አልቦነትን(inerrancy) ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት። ህጸጽ አልቦነትን ማለት ከስህተት የጸዳ እውነት አዘል አልያም ዝንፈተ እውነት የሌለበት ማለት ነው። አንዳንዶች የመጽሐፍ ቅዱስን ህጸጽ አልቦ አፊዎተ ቃለ እግዚአብሔርነቱ ላይ ሒስ ለማቅረብ ሲሉ ሁለት መሰረታዊ ነባቤ ቃላትን እርስ በእርሳቸው ያጠረማምሳሉ(ለምሳሌ የኤቲስቱ ባርት ኧርማን ሙግት)፤ ይኸውም የቃል በቃል አጠባበቅ እና ህጸጽ አልቦነትን ነው። ሁለቱ መሠረታዊ ልዩነቶች ያሏቸው ሲሆኑ የአንድ ነገር ንግግር ወይም ጽሑፍ የቃል በቃል አጠባበቅ ላይ ችግር ማግኘታችን ህጸጽ አልቦነቱን ላያሳጣው ይችላል። ባጭሩ የዚህ ሙግት ችግር የመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ግልጠት ማለታችን በእደ ክታቦቹ የቃል በቃል መስማማት አለባቸው ከሚለው ቅድመ ግንዛቤ ላይ የተመረኮዘ አለመሆኑን ካለመረዳት አንጻር ሊታይ ይችላል። ለምሳሌ ያክል የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ በሁለት የግሪክ ቃላት ብቻ ልዩነት የተፈጠረ አንድ የሚስተዋል ልዩ ምንባባት አሉ፦

እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤
ሮሜ 5፥1

አንዳንድ እደ ክታባት ሰላምን እንያዝ የሚለውን ሐረግ ሲያካትቱ አንዳዶቹ ደግሞ ሰላም አለን የሚልን ነባቤ ሐረግ ይጠቀማሉ(አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚሁ መልክ ሲጠቀም ይታያል)። የግሪኩ ቃል አንዱ ኤኾሜን በኦሜጋ ፊደል(ἔχωμεν) ሲጠቀም ሌላኛው ደግሞ ኤኾሜን በኦሚክሮን ፊደል (ἔχὸμεν) ይጠቀማል። ምንም እንኳን እንደዚህ አይነት የቃላት ልዩነት ቢኖርም የአረፍተ ነገሩ ዋና ሐተታዊ እውነታው የሚደበዝዝ ወይም ሊናድ አይችልም። የአረፍተ ነገሩ ትክክለኛው አቀማመጥ፦ “peace is the possession of those who have been justified” እስከሆነ ድረስ የክታቡን ህጸጽ አልቦነት በቃላት ቦታ መለዋወጥ ሆነ አለመመሳሰል ልናጣው በፍጹም አንችልም። ምክንያቱም ህጸጽ አልቦነት የሚገናኘው ከትክክለኛ ዓርፍተ ሐሳቦ ጋር ነው። ነገር ግን አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር አንዳንድ የእደ ክታባቱ ልዩ መሆን(texual variant) ችግር ሆነው የሚመጡበት ጊዜ ሆነው የሚመጡበት ሰዓት ሊኖር ይችላል። ይሄን መሠል ችግሮች አገኘን ማለት ግን እንደነዚህ አይነቱን ለመለየት አስቸጋሪ አይደለም እንደውም በቀላሉ የሚለዩ ናቸው። ሙስሊሞችም ሆኑ ለዘብተኛ ምሑራን የሚጠቅሷቸው ነጠሮች በአጥባቄው ምሑራኑ ዓለም ውስጥ መልስ ተሰጥቷቸው ያለፉ ናቸው። በምሳሌም እውቁ የምንባባዌ(ጽሑፋዊ) ሕያሴ ስኮላር ዋላስ 99 በመቶ በላይ የሚሆኑት በእነርሱ መካከል ልዩ ምንባባት እንደሌሉ ይናገራሉ። Matthew Barrett በመጽሐፉ እንዲህ ሲል ያስቀምጠዋል፦

"….textual variations in the copies do not imply that the original manuscripts contained errors. These variations are seen as part of the natural process of transmission over time, but they do not undermine the truthfulness of Scripture as it was originally given. the existence of textual variants should not shake one's confidence in the inerrancy of the Bible, as the original text remains reliable and intact, even if minor discrepancies exist in the copies.."

በዚህ መሠረት ደግሞ በመጀመሪያው ጽሑፍ መካከል ልዩነት አለና በኋላ ላይ ባሉት ኮፒዎች ልዩነት አለ በሚሉ ሰዎች ሙግት ልዩነቶቹ በራሷቸው የእግዚአብሔር ቃል ህጸጽ አልቦ መሆኑን ሊሸፍኑ አንዳች አይቻላቸውም በማለት ክታባቱን ያጠኑ ምሑራን በዚህ መልክ ያስቀምጡታል ማለት ነው።

ማጣቀሻ

Barrett, Matthew. God’s Word Alone: The Authority of Scripture. Zondervan, 2016

ለሌሎች ያጋሩ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top