ተሐድሶ በአጭሩ

ጊዜው ኦክቶበር 31፣ 1517 ነበር። በዚህ ወቅት ነው አንድ መነኩሴ የተነሳው። ይህ ወቅት በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ውስጥ ትልቅ መንፈሳዊ ቀውስ የነበረበት፤ ሥልጣናዊነት በቤተክርስቲያን ላይ ትልቁን ለጳጳጻቱ አድርጎ፣ መጽሐፍትን የመተርጎም ስራ የእነርሱ መብት ብቻ የሆነበትና ትምህርተ ድነት መጽሃፍ ቅዱሳዊ ማንነቱን ያጣበት 16ኛው ክፍለ ዘመን ነበር።

በዚህም በአንዲት ትንሽ የጀርመን ትምህርት ቤት ውስጥ ለመጽሐፍ ቅዱስ ሕልውና ሲል የቤተ ክርስትያን በሮች ላይ የተወሰኑ አንቀጾችን ለመለጠፍ በሕይወት ዘመኑም ለመጽሐፍ ቅዱስ ሕልውና ዘብ ለመቆም ሩቅ መንገድ የሄደበት ጊዜ የጀመረው። እነዚያ አናቅጾች የለጠፈበት ምክንያት በዚህ ዘመን እኛ ለሥራ መግለጫ ሥፍራ አሳደን ለማንበብ እንደምንታትረው የቤተክርስትያኒቱ በር ብዙዎች ቀልባቸውን ስበው የሚያነቡበት ሥፍራ ተደርጎ ስለሚወሰድ ነበር በዚያ የለጠፈው።

ባስቀመጠው 95 አናቅጽ ውስጥ የኢንደልጀንስን “በጥምቀቱ ጊዜ እንደነበረው አይነት ንጽህና” ከመስጠቱም በላይ ሰዎች ለሞቱ ወገኖቻቸው ሳይቀር ይህንን ክፍያ ከፍለው ከስቃይ ሊያድኗቸው እንደሚችሉ ተሰበከ። በካቶሊኮቹም ዘንድ ፑርጋቶሪ ማለትም ነፍሳችን ወደ ገነትም ሆነ ሲዖል ከመጣሏ በፊት የምትሆንበት ስፍራ ውስጥና በሕይወት እንቅስቃሴዎቻችን እያለን ስላጠፋው ስለኃጢአቷ የሚቆይበትን ጊዜ (ወደ መንግስተ ሰማይ ከመግባቱ በፊት) በሚገዛው ኢንደልጀንስ ማቀናነስ ይችላል የሚል የኑፋቄ ትምህርት ነበር።

እንግዲህ ይህ ክስተት ምን ያህል ትክክለኛውን የድህነት መንገድ እንዳጣመመ ለመረዳት የአዲሲ ኪዳናችንን መጽሐፍ ገለጥ አድርገን ብንመለከት ቅዱስ ዮሃንስ በወንጌሉ እንዲህ አለ፦

ዮሐንስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹¹ የእርሱ ወደ ሆነው መጣ፥ የገዛ ወገኖቹም አልተቀበሉትም።
¹² ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ሥልጣንን ሰጣቸው፤

በማለት የመሰከረለት ድነት ለሕንጻ ማስጨረሻ በጳጳሳቱ በተዘየደው መላ ሕያው የመዳኑ መንገድ ተሻረ፤ ይህም ጳጳሳቱ ያልተገደበ ስልጣንና ህጸጽ የለሽ ማንነትን ለራሳቸው እንደወሰዱ በግልጽ ያሳየና ቃሉን ለፈለጉት አላማ ለማዋል እንደሚደፍሩ ያመለከተ ነበር።

ነገር ግን ይህ አይነቱ ኢ መጽሃፍ ቅዱሳዊ አካሄድ በሁሉም ዘንድ ይሁንታን አላገኘም፤ እንደ ሉተር አይነቶቹን በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የነበሩ ምሁራን አስነስቷል። በርግጥ ወደ ቤተክርስቲያኒቱ የተወረወረው የመጀመሪያው የተሃድሶ ፍላጻ ከሉተርም ቀደም ይል ነበር። ውስጥ የተነሳው ጆን ዊክሊፍ የጳጳሱን ያልተገደበ ስልጣን በመቃወሙና መጽሃፍ ቅዱስን ማንኛውም ሰው እንዲያነበው ወደ እንግሊዘኛ በመተርጎሙ ምክንያት በኑፋቄ ተወግዟል፤ ተከታዮቹም ከስደት በቃጠሎ እስከመሞት ድረስ መከራ ተቀብለዋል። ታሪኩ ሰፊ ነው በዚህ ማያበቃ ቢሆንም እኛ ግን በዚህ እናብቃ፦ በዚህ ዘመን ያለነው ከቅዱሳት መጽሐፍትና ከአበው ትምህርት ላልተቀዱ ትምህርቶች ጎን ሳንቆም ቅዱሳት መጽሐፍትን የሁሉ የበላይ አድርገን እንድንቀጥልና የቫሌንቲነስ ኑፋቄ የሐዋርያትን ትምህርት ከአፍላጦን ፍልስፍና ጋር ያገናኘ፣ የመርቅያን ኑፋቄ የሐዋርያትን ትምህርት ከስቶይሲዝም ጋር በመቀየጥ የተገኘ ነው እንደሚለው  ዛሬም እንደ ሉተርና ተሐድሶ አበው የምንቃወማቸውን ነገሮች ከራሳችን ሳይሆን ከመጽሐፍ ቅዱስና ከአበው ክታባት እንዲሆን መሆን አለበት። ከቶ ጥለን መቀጠል የለብንም።

“ከሕገ ቤተ ክርስቲያን ቅጽርና ክልል ወጥታችሁ፣ የሕግ ክልል የሥርዓት ወሰን በሌለው ሜዳዊ ሕግ አውታሯን እንደበጠሰች በቅሎ ፈቃደ ሥጋችሁ እንዳዘዛችሁ ስትፏልሉ ትታያላችሁ። የሚወስናችሁ የሥርዓት አጥር ቅጥር፣ የሚገታችሁ የሕግ ልጓም ከማጣታችሁ የተነሣ የማኅበራችሁና የባህላችሁ ቁጥር በየቀኑ እየበዛ ሲሔድ ይታያል።”[1]

ለማስተማር የሚነሳ ሁሉ ግለሰብ ከሁሉም አስቀድሞ ሐዋርያት ያስተማራትን የሃይማኖት ትምህርት ጠንቅቆ ማወቅ ይገባዋል።[2]

ልክ ማርቲን ሉተር An Assertion of All the Articles (1520) እንደጻፈው፦

I do not want to throw out all those more learned [than I], but Scripture alone to reign, and not to interpret it by my own spirit or the spirit of any man, but I want to understand it by itself and its spirit.
Martin Luther King Jr.

“[ከእኔ በላይ] የተማሩትን እነዚያን አውጥቼ ልጥላቸው አልወድም፣ ነገር ግን መጽሃፍ ቅዱስ ብቻ እንዲነግስ፤ በራሴም ይሁን በሌላ በማንም መንፈስ እንዳልተረጉመው፤ በእርሱ በራሱ መንፈስም እንደረዳው እፈልጋለሁ”[3]

ከቶ አባቶችን ጥለን የምንቀጥለው ተሐድሶ የለምና ከዚህ ትምህርት ጋር የተቆራኘውን ክላሲካል ፕሮቴስታንት መኾን ያሻልና አንዘንጋ!

ማጣቀሻ

[1] አድማሱ ጀንበሬ፣ ኰኲሐ ሃይማኖት፣ ገጽ 160

[2] ሔኖክ ኢሳያስ፣ በእንተ ኑፋቄ፣ ገጽ 24

[3] Martin Luther, Assertio omnium articulorum M. Lutheri per bullam Leonis X. novissimam damnatorum (1520), WA 7:98.40–99.2.

ለሌሎች ያጋሩ

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top