ሆሣዕና <አሁን አድን….!>
ደጉ ጌታ መጣ ተገለጠ ሰዎችም ተቀበሉት። ከተቀበሉት መካከል ሰው ብቻ ሳይሆን ከምድር ፍጥረታት መካከል ያለች አንዲት ውርጭላ ከአህያይቱም ጋር ነበረች። አህያይቱም ተነሳች ክብሯን አየች፣ ንጉስም ተቀመጠባት፤ አምላክ ሥጋን ለብሶ መጣ ወደ ምድር አቤቱ ዛሬ አድን ሆ…ሆ ብለን ሆሣዕና[፩] እንድል። የቀደመው ተተንብዮ የነበረው ትንቢቱ ተፈፀመ ሆ…! እያልን ከተገኘው የዘንባባ ዝንጣፊ ከእግሩ ሥር እያቀረብን። ንጉሡም ተራመደ[፪] አለፈ የትንቢቶቹ ምጻሜ ሊቃረብ ሆነ…! ይኼን ለመረዳት ጥሞና መውሰዱ ሳያሻን አይቀርም ከበፊቱ ይልቅ ሆሣዕና እንድልን…[፫] መልካም የጥሞና ቀን እና ምሽት…! [፩] ሆሣዕና|Hosanna፦ ዋሴ ና፣ አዳኜ ና፣ ጠባቂዬ ድረስ ማለት ነው። ‘ዋስ’ እና ‘ና’ ከሚሉ ቃላት የተመሠረተ ቃል ነው።[…አድነን፡ እባክኽ አድነን…መድኅኒትነት፤ መሆን ወይም መባል።] [፪] ጌታ ወደ ኢየሩሳሌም በገባ ጊዜ ህጻናት ካዜሙት ቃል፥ ሆሣዕና ፥ “…ሆሣዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባከ ነው፤ ሆሣዕና በአርያም እያሉ ይጮኹ ነበር።” (ማቴ 21፡9) [፫] ሆሣዕና በአርያም ሆሳዕና በምድርይሁን ለዳዊት ልጅ ለመጣው በክብርይዘርጋ ዘንባባ ይነጠፍ ምንጣፉከዳዊት አምላክ ጋር በክብር እንዲያልፉይቻለዋል አምላክ ታሪክ ይለውጣልመራራውን ሕይወት እርሱ ያጣፍጣልጌታ አንዴ ከፈታን ከቶ ማን ያስረናልሆሳሣና እንበል ነጻነት ወጥተናል