Islam

ሑባል(هبل)

እስልምና እና የአረቡ ጣዖታት ክፍል 1 እንደሚታወቀው እስልምና ሲነሳ በአእምሯችን ፈጥኖ የሚሳለው የገሚሱ ጨረቃ እና ኮከብ አርማ ነው። በትላልቅ መስጂዶች አናት ላይ በሚናራዎች[¹] እንዲሁም እስላማዊ በሆኑ ኪነ ህንጻዎች ላይ የሚስተዋል ምልክት ነው። በሰባተኛው መቶ ክ/ዘ መጀመሪያዎቹ አካባቢ የእስላማዊ አገሮች መገበያያ የጨረቃ እና ኮከብ ምስል ያለው ሳንቲሞችን እንደሚጠቀሙ አርኪዎሎጂስቶች ያትታሉ።[²] በ11ኛው መቶ ክ/ዘ ግብጻውያን እና ሶርያውያን ይህንን ምልክት ለጌጣጌጣቸው ማስዋቢያነትም ይጠቀሙት ነበር።[³] በተጨማሪም አንዳንድ አገራት ማለትም እንደ አልጀሪያ፣ አዘርባጃን፣ ኮሞሮስ፣ ማሌዥያ፣ ሞሪታንያ፣ ፓኪስታን፣ ቱኒዚያ፣ ቱርክ፣ የቱርክ ሪፐብሊኳ ሰሜኒቷ ቆጵሮስ፣ ኡዝቤክስታ የምዕራብ ሰሐራ …ወዘተ  እስላማዊ አገራት ይህንኑ አርማ እንደ ሀገራዊ መለያ ሰንደቅ ማድረጋቸው ይታወቃል።[⁴] እስልምና ከጨረቃ እና ኮከብ ምልክት ጋር ምን ግንኙነት አለው? ይህንን ግንኙነት ለመረዳት ዲነል ኢስላም ከመጀመሩ በፊት ጥቂት አመታት እልፍ ብለን ስንመለከት በመካ ይመለኩ ከነበሩ ጣዖታት መካከል አንዱ ሑባል(هبل)  የጨረቃ እና የከዋክብት አምላክ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያትታሉ።[⁵] ሑባል(هبل) የአሏህ ቤት ተብሎ በሚጠራው በካዕባ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የነበረው እና ለነገደ አረቡ ጣዖት አምላኪያን ሐያል አምላክ እና ታላቁ ጣዖታቸውም ነበር።[⁶] የሑባል ሌላኛው ስሙ “ሏህ” በመባል ይታወቅ ነበር። እንደ ሮበርት ሞሪ ያሉ ስኮላሮች ጥናት መሠረት ከአርኪዎሎጂስቱ ተመራማሪ ሁጎ ዊንክለር ጥናት በመነሳት “አሏህ” የሚለው ስም ለቅድመ እስላማዊ የአረብ ማህበረሰብ አፈታሪክ ውስጥ ለጨረቃ አምላካቸው ስያሜ እንደዋለ ይነግረናል።[⁷] ጁሊየስ ዌልሃውሰንም ጨምሮ የእስልምና ሐይማኖት ከማንሰራራቱ በፊት የአሏህ ቤት ተብሎ የሚጠራው ካዕባ በጣዖቱ ሑባል ሐውልቶች ቁሳቁሶችና ስዕላት ተሞልቶ እንደነበርና ሑባል የአሏህ የመጀመሪያ ስሙም እንደነበር ይናገራል።[⁸] ነገር ግን በእስልምናውም ላሉ ሊቃውንቶች ሆነ ለለዘብተኛ የታሪክ አጥኝዎች ጥያቄ የሆነው ክስተት አሏህ ስለዚህ ታላቅ የአረቦች ጣዖት በሐዲሱ ላይ አንድ ሱፍያን ኢብን ሀርብ የተባለ የቁረይሽ የጦር መሪ ከባድር ጦርነት በኋላ ድልን እንዲሰጣቸው እንደተጣራና ሑባልን እንዳመሰገነ[⁹] ከመጥቀሱ ባለፈ በቁርአኑ ውስጥ በስሙ ተጠቅሶ አለመነሳቱ ነው። እንደ እነ አል ላት አል ኡዛ እና እንደ እነ አል መናት ያሉ ጣዖቶች በቁርአኑ ውስጥ ተጠቅሰው ሳሉ ጣዖቱ ሑባል አለመጠቀሱ አጠያያቂ ጉዳይ ነው። እንደ አንዳዶች አባባል ቁርአን በካዕባ ስለነበሩ ሶስት መቶ ስልሳ ጣዖቶች እያንዳንዱን ስም እየጠቀሰ ግድ መናገር የለበትም ይላሉ። ነገር ግን ቁርአን በቁረይሾች ነገድ እንደ ሑባል በገነነ መልኩ የማይመለኩትን በስም ጠቅሶ ከገለጠ ስለ ሑባል አለማውራቱ አግራሞትን የሚያጭር ጉዳይ ሁኖ እናገኘዋለን። ይህ የሆነበት እንደምክንያት የሚነሳው የእስልምናው ሐይማኖት ቆርቋሪ እና መስራች የሆነው መሐመድ ከጣዖቱ ሑባል ጋር የተቆራኘ ታሪክ ስላለው ነው። ነብይ ተብዬው ከመወለዱ በፊት አያቱ አብዱል ሙጠሊብ የጣዖቱ ሑባል አምላኪ እንደነበር የእስልምና ታሪክ መዛግብት ይናገራሉ።[¹⁰] አብዱል ሙጠሊብ ከልጆቹ መኻል እጣው የወደቀበትን ልጅ በአሁኑ ጊዜ ቅዱስ ስፍራ ተብሎ በሚጠራው በካዕባ ለጣዖት ሑባል መስዋዕት አድርጎ ለማቅረብ በደጋን እጣ በልጆቹ ላይ ይጥላል። የደጋኑም ጫፍ የመሐመድ አባት በሆነው በአብደላህ ላይ ያመልክታል። የመሐመድም አያት ልጁን ለመሰዋት ማረጃ እንዳነሳና ነገር ግን ቁረይሾች፣ ከመኸዙም ጎሳ የሆነው አጎቱ እና ወንድሙ ልጁን እንዳይሰዋ አሳምነው አብዱል ሙጠሊብ በመሐመድ አባት አብደሏህ ምትክ የሚሆን የግመል መስዋዕት ለሑባል እንዳቀረበ እንመለከታለን።[¹¹] እንደውም እንደ ጠበሪ ዘገባ አብዱል ሙጠሊብ መሐመድ ጨቅላ እንደነበር ወደ ጣዖቱ ሑባል ፊት ያመጣው እንደነበር ይተርካል።[¹²] ይህ ሁሉ የታሪክ ማስረጃዎች የሚያሳዩን የቁርአኑ ደራሲ መሐመድ ከሑባል ጣዖት ጋር ገና ከመወለዱ ጀምሮ ህጻንም እያለ ጥብቅ ቁርኝት እንደነበረው ያሳያል። ምንም እንኳን መሐመድ በካዕባ የሚገኙትን የሑባልን ጣዖት እና መገልገያዎችን ለማጥፋት ቢሞክርም የሑባል ጣዖት የአምልኮ ስርአቶችን ለምሳሌ በካዕባ ዙሪያ ጠዋፍ ማድረግን(የቅድመ አረባውያን የጣዖት አምላኪዎች ልምምድ ነበር ለጣዖት ሑባልም ይህንኑ የአምልኮ ስርአት አምላኪዎቹ ይከውኑ ነበር) የጣዖቱ ስም ከአምላኩ ስም ጋር ማመሳሰሉ(ቀደምት እስልምና የጣዖት አምላኪያውያን አምላካቸውን ላህ ወይም ሑባል በማለት ይጠሩት እንደነበር እና የእስልምናው አምላክ ስም ከጣዖታውያኑ ጋር ጥልቅ ቁርኝት ነበረው) በተጨማሪም የአሁኑ የሙስሊም  ማህበረሰብ የሚጠቀምበት የእምነት መለያ አርማቸው ያደረጉት በጥንቱ የአረብ ጣዖት አምላኪያን ዘንድ ለሑባል የተሰጠ የጣዖታቸው መለያ መሆኑ ይህ ሁሉ የሚያሳየን እስልም የቅድመ አያቶቹን የአረብ ጣዖታውያንን የሐይማኖት ስርአት፣ ስያሜ የማምለኪያ ቦታ(ካዕባ) እና የመለያ ምልክቱን መኮረጁ ወልደ ጣዖታውያን የእምነት መሠረት መሆኑን በግልጽ ሁኔታ መረዳት የምንችለው የሐይማኖት ቡድን እንደሆነ ነው። መጽሐፍ ቅዱሳችን ግን፦ “እኔ እግዚአብሔር አምላካችሁ ነኝና ለእናንተ ጣዖት አታድርጉ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ትሰግዱለትም ዘንድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።”  — ዘሌዋውያን 26፥1 በማለት እንዳናመልክና እውነተኛውን ጌታ እንድንከተል ያደርገናል። እግዚአብሔር በዚህ መንገድ ይመራቸው ዘንድ ፀለይን አሜን። ማጣቀሻዎች [¹] International Federation of Red Cross & Crescent Societies [²] S. Album & T. Goodwin – Syllogue Of Islamic Coins In The Ashmolean – The Pre-Reform Coinage Of The Early Islamic Period – 2002, Volume I, Ashmolean Museum: Oxford (UK), pp. 6-7 [³] “Pendant (Egypt) (30.95.37)”. In Heilbrunn Timeline of Art History. New York: The Metropolitan Museum of Art, 2000–. (October 2006) [⁴] Islamic flags – Flags Of The World, October 18, 2008 [⁵] Karen Armstrong (2000,2002). Islam: A Short History. pp. 11 [⁶] ዝኒ ከማሁ [⁷] Morey, Robert(1994)The Moon-god Allah in Archeology of the Middle East. Newport, Research & Education Foundation. [⁸] Wellhausen, Julius. Reste Arabischen Heidenthum, pp. 75/ Hawting, Gerald R.(1999). The Idea of idolatry & the emergece of Islam: from polemic to History. pp. 112 [⁹] Winckler, Hugo(1901) Arabisch, Semitisch, Orientalisch: Kulturgeschichlich-Mythologische Untersuchung.Berlin:W. Peiser pp. 83 [¹⁰] Ibn Hisham 1/151-155; Rahmat-ul-lil’ alammeen 2/89, 90 [¹¹] ዝኒ ከማሁ [¹²] Mohammed ibn Jarir al-Tabari, The History of the Prophet & Kings,1:157

ሑባል(هبل) Read More »

ማርያም የሐሩን እህት?

“የእንበረም(አምራም/עַמְרָם) ሚስት ስም ዮካብድ(ዮኬቬድ/יוֹכֶבֶד) ነበረ። እርስዋ በግብፅ ከሌዊ የተወለደች የሌዊ ልጅ ነበረች፤ ለእንበረምም አሮንንና(አኻሮን/אַהֲרוֹן) ሙሴን(ሞሼኽ/מֹשֶׁה) እኅታቸውንም ማርያምን(ሚርያም/מִרְיָם) ወለደችለት።”— ዘኍልቁ 26፥59 በመጽሐፍ ቅዱሳችን መሰረት የአሮን (አኻሮን/אַהֲרוֹן)፣ የሙሴና(ሞሼኽ/מֹשֶׁה) የነብይቷ ማርያም(ሚርያም/מִרְיָם) አባታቸው እንበረም(አምራም/עַמְרָם) ነው።እንበረም በእብራይስጡ አምራም/עַמְרָם በ ፊደል ሜም “ם” ሲያበቃ በአረበኛው መጽሐፍ ቅዱስ ላይ አምራም(عمرام) በፊደል ሚም(م) የሚጨርስ ቃል ነው፦ أبْناءُ عَمْرامَ هُمْ هارُونُ وَمُوسَى وَمَرْيَمُ የእንበረምም ልጆች አሮን፥ ሙሴ፥ ማርያም።”— 1 ዜና 6፥3በቁርአኑ ላይ ደግሞ ኢምራን(عمران) በፊደል ኑን(ن) በሚያበቃ ስም ተጠቅሶ እናገኘዋለን[¹]። ذكر نسب موسى بن عمران (የአት-አጠበሪ ታሪክ ቅጽ3) ቀዓት(ቀኻት/קְהָת) ልጅ የሆነው  እንበረም(1 ዜና 6፥2) የመጀመሪያ ልጁ ነብይቷ ማርያም ስትሆን ሙሴ እና ወንድሙ አሮን የተወለዱት 1400-1500 ዓ.ዓ እንደሆነ ይታሰባል[²]። ከዚህ ሁሉ ዘመናት በኋላ በዘመነ አዲስ ኪዳን ጊዜ የጌታችንና የመድኃኒታችን እናት የሆነችው ቅድስት ድንግል ማርያም ኢየሱስን እንደወለደች ቅዱሱ መጽሐፋችን ይነግረናል። መጽሐፍ ቅዱስ የቅድስት ድንግል ማርያምን አባትና እናት ባይጠቅስልንም ብዙ ድርሳናትና ታሪካዊ መጽሐፍት ኢዮአቄም(Joachim) እና አና(Anne) እንደሆኑ ይነግሩናል[³]።ባጭሩ የሙሴ እህት ነብይቷ ማርያም ጺን ምድረ በዳ እንደሞተች በኦሪት ዘኍልቁ ም.20 ቁ.1 ላይ እንመለከታለን። ቅድስት ድንግል ማርያም ከሙሴ እህት ማርያም ጋር በማንነት ሆነ በነበሩበት ጊዜ ይለያያሉ። እንደዚህ ያክል የመጽሐፍ ቅዱሱን በንጽጽራዊ ትንተና ከተመለከትን ወደ ቁርአኑ እንለፍና የመሐመድን በታሪክ ላይ የፈጸመውን ወንጀል እንመልከት፦መሐመድ በቁርአኑ ላይ የኢሳ እናት ማርያምን እና የነብዩ ሙሴ እና የአሮን እህት ማርያምን እንደ አንድ ሴት አድርጎ ማስተማሩ ነው!!!የብዙ ዘመናት ልዩነት ያላቸው በሁለት ታሪኮች መካከል ያለ መመሳሰልን ማለትም፦ ➙ የሙሳ ወንድም ሃሩን እና የኢሳ እናት ወንድም ሃሩን ➙የሙሳ አባት ኢምራን እና የኢሳ እናት አባት ኢምራን ➙ ራሷ ባለ ታሪኳ የኢሳ እናት መርየመ እና የሙሳ እህት መርየም ያለውን መመሳሰል ስንመለከት በይበልጥ ታሪኩን እንድንመረምር አድርጎናል። በዚህም ጉዳይ በርከት ያሉ ዳዒዎችና ለእስልምናና ለመሐመድ ዘብ(ጥበቃ) እቆማለሁ የሚሉት ዳዕዋጋንዲስቶች የሙግት ነጥብ ይሆኑናል ብለው የሚሰነዝሯቸውን ነጥቦች እንመልከት፦ የስም መመሳሰል፦ በዚህ የሙግት ነጥባቸው ላይ የኢሳ እናት የሆነችው የመረየም ወንድም ሃሩንና የሙሳ ወንድም ሃሩን ሁለት የተለያየ ማንነትና በተለያየ ጊዜ የነበሩ ሰዎች ናቸው ይላሉ። ይሄን የሙግት ነጥባቸውን ይደግፍልናል ብለው የሚጠቅሱት ሐዲስ አል-ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባ የሚባል ሰው ወደ ነጅራን በሄደ ጊዜ በዛ አካባቢ ያሉ ክርስቲያኖች በሱረቱል መርየምን (19:28) ላይ የተጠቀሰውን «…የሃሩን እኅት ሆይ!…» የሚልን ጽሑፍ እንዳነበቡና ሙሳ ደግሞ ከዒሣ ብዙ ጊዜ በፊት እንደነበር በነገሩት ጊዜ ጥያቄውን ይዞ ለመሀመድ አቀረበላቸው። መሀመድም በመልሳቸው “የድሮ ሰዎች ከራሳቸው በፊት ከነበሩት የነቢያቶች ስሞች ከነቢያቱ ህልፈት በኋላ ይጠቀሙ ነበር” ብሎ ነገረው(ኢማም ሙስሊም መጽሐፍ 38 ሐዲስ 13)። አስተውሉ፦ በሐዲሱ መሠረት የመጽሐፉ ባለቤቶች የሚባሉት ክርስቲያኖች ስለ ኢየሱስ እናት የማርያም ወንድም ስለሆነው አሮን የሚባል ወንድም እንዳላት በጭራሽ የማያውቁ እንደሆኑና አል-ሙጊራህ ኢብኑ ሹዕባ የሚባለው ሙስሊም ሙእሚን ግራ ተጋብቶ ጉዳዩ ጥያቄ እንደፈጠረበት እንመለከታለን። በተጨማሪም የምእመናን እናት የሆነችው አዒሻ (ኡም አል-ሙእሚኒን/أمّ المؤمنين‎) እንኳን እንደማታውቅ ከከዓብ (ረዐ) ጋር ባደረገችው ንግግር እንረዳለን[⁴] “…’የሃሩን(የአሮን) እህት!’ (የሱራ 19 28) የሙሴን ወንድም አሮንን አያመለክትም። ዓኢሻ(ረዐ) ለከዓብ(ረዐ) “ #ዋሽተሃል” በማለት መለሰችለት።….”(ተፍሲር ኢብን ከሲር 19:28) በእነዚህ ሁሉ ሰዎች ማለትም ለአንዳንድ ሙስሊሞች እንግዳ የሆነና በመሐመድ ዘመን የነበሩት የተማሩ ዐረብ ክርስቲያኖች(የመጽሐፉ ባለቤቶች) የማየታወቅን ታሪክ መሐመድ ከየት አምጥቶ ነው አሮን(ሃሩን) የሚባል የማርያም(መርየም ) ወንድም አለ ያለን? በተጨማሪም የኢሳ እናት የሆነችው የመረየም ወንድም ሃሩንና የሙሳ ወንድም ሃሩን የተለያዩ ሰዎች ናቸው ካሉን አንድ ወሳኝና አነጋጋሪ ጥያቄ መጠየቃችን አይቀሬ ነው በታሪክ ስለማይታወቀው ሰውዬ(የኢሳ እናት የመረየም ወንድም ሃሩን ተብዬው) እንደዚህ ያክል አስፈላጊና የኢሳ እናት መረየም በእርሱ እስከምትጠራ ስላስደረገው ሰው እንዴት ቁርአን ችላ ብሎ አለፈው እናም ስለሱ የሚናገሩ የታሪክ መዛግብት እንዴት ልናጣ ቻልን? ወይም ደግሞ የሙሴ (ሙሳ) ወንድም የሆነውን አሮንን(ሃሩን) የኢሳ እናት ለሆነችው ማርያም(መርየም) ወንድም መስሎት እንደነበር ይሄም ደግሞ የመሐመድ አላዋቂነት ማለትም በታሪክ ላይ የሰራው ወንጀል መሆኑን ማወቅ ይጠበቅብናል። ኢኽዋህ(إِخْوَة) የሙሳ ወንድም እና የመርየም ወንድም አንድ ማንነት ናቸው ስንል አማኞች ወንድም እና እህት ናቸው በሚል ቀመርና ስሌት ነው ይሉናል። ይሄም የሙግት ነጥባቸው መፍለክለኪያ(ማምለጫ) ያጣ ሰው ለማምለጫ ከሚፈጥረው ቀዳዳ ተለይቶ አልታየኝ። በሃገሬው አባባል “…ከቀዳዳ ይሻላል ጨምዳዳ…” እንደሚባለው ነጥቦቻቸው የመሐመድን ስህተት መደበቅ ሳይችልላቸው ሲቀር ከአንዱ ወደ አንዱ በይሻላል መንፈስ ይራወጣሉ። ለማንኛውም በአማኞች መካከል ኢኽዋህ(إِخْوَة) ማለትም ወንድማማችነትና እህትማማችነት ቢኖርም አሁንም የሱረቱል መርየም(19:28) ከጥያቄ አያመልጥም። ቁርአኑ ስለ ሙሳ ከወንድሙ ሃሩን ይልቅ በስፋት ነግሮን ሳለ ሙሳ ሳይጠቀስ ሃሩን የተጠቀሰበት አግባብ ግልጽ አይደለም።ደግሞስ መርየም አባቷ ኢምራን እያለ በሙሳ ወንድም በሃሩን ስም መጠራቷ ምንን ያመለክታል? ደግሞም በሌላ ክፍል በሱራ 33 እና 66:12 ላይ “የኢምራን ሴት ልጅ” በመባሏ ወደ ሱራ 19:28 ስንመጣ ከሩቅ ዘመን ባለ ሰው ስም መጠራቷ ጉዳዩን የበለጠ ብዥታንና እና ችግርን አስከትሏል። ለዚህ ሁሉ ጥያቄ መልስ የሚሆነው የመሐመድን ስህተት መቀበል ነው። በተጨማሪም መሐመድን ለዚህ ትልቅ ስህተት ያበቃው አንዳንድ ምንጫቸው በቅጡ ከማይታወቁ በክርስትናው ላይና በአይሁዳውያን መጽሐፍት ላይ ከሚጨመሩ አፈታሪኮች የሰማውን በራሱ አገላለጽ ስለሚዘግብ ነው። ሱረቱ መርየም የተወሰኑ ክፍሎች የአፖክሪፋን ታሪኮች እንደ የያዕቆብ ፕሮቶቫንጄሊየም (Protoevangelium of James) እና የሐሰተኛው-ማቴዎስ ወንጌል(gospel of Pseudo-Matthew) ካሉ አፈ ታሪኮች የአዋልድ ታሪኮች ተመሳሳይነት ያለው ታሪክ እናገኝበታለን። ለምሳሌ የቴምር ዛፉ ስር የተፈጠረው ታሪክ[⁵] ስለ መርየም ወላጆች ታሪክ[⁶] ለአብነት ተጠቃሽ ናቸው። በተጨማሪም በአረባዊቷ ምድር በፍልስጤም ውስጥ በቅድስት ድንግል ማርያም የተሰየመ የባይዛንታይን ቤተክርስቲያን አለ። ይህ ቤተክርስቲያን ከእስልምና ወግ ጋር ጥልቅ እና የተወሳሰበ ግንኙነት አለው እንዳለው ታሪክ ይነግረናል። በመሐመድ ዘመን አካባቢ ይህች ቤተክርስቲያን የክርስትና አምልኮ ማዕከል ነበረች። በቅዳሴ ወቅት ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጭ ከሚነበበው ከካቶሊክ እና ከኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በተቃራኒ በዚህ ጊዜ ለንባብ ከአፖክሪፋ እና ከሌሎች ቀኖናዊ ያልሆኑ መጽሐፍት መነበቡ የተለመደ ነው። በተጨማሪም የተለያዩ የክብረ በዓላት የምታከብር ቤተ ክርስቲያን ነበረች። ለምሳሌ ላይ በነሐሴ ወር አጋማሽ ላይ ቀን 14 ከነብዩ ኤርምያስ ሕይወትም ከአዋልድ መጽሐፍት ይነበብ ነበር። በምንባቡ ላይ መሐመድ በሱረቱል በመርየም ላይ እንዳሰፈረው አይነት ማለትም ሃሩን(አሮን) የማርያም (መርየም) ወንድም በማለት የተጠቀሰን ጽሑፍ እናገኛለን[⁷]፦ “ነቢዩ [ኤርምያስም] እንዲህ አለ – መምጣቱ ለእርስዎ እና ለሌሎች ልጆች በዓለም ምልክት መጨረሻ ይሆናል ።57 እንዲሁም የተደበቀውን ታቦት ከዓለት ላይ የሚያወጣ የለም ከማርያም ወንድም አሮን በስተቀር ።(The Lection of Jeremiah) በተመሳሳይ ሁኔታ ቁርአኑ ስለ ማርያም (መርየም) ሲናገር ሃሩን(አሮን) የማርያም (መርየም) ወንድም እንደሆነ ዘግቦልን አግኝተናል፦ 19፥28 « የሃሩን እኅት ሆይ! አባትሽ መጥፎ ሰው አልነበረም፡፡ እናትሽም አመንዝራ አልነበረችም» አሏት፡፡ يَا أُخْتَ هَارُونَ مَا كَانَ أَبُوكِ امْرَأَ سَوْءٍ وَمَا كَانَتْ أُمُّكِ بَغِيًّا በመጨረሻም ለመሐመድ ዘብ እንቆማለን ባዮቹ አብዱሎች ታሪክን በመደበቅ የመሐመድን ስህተቶችና አላዋቂነቱን ለመደበቅ መፍጨርጨራቸው የሚያዋጣ አይደለም። መሐመድ ከታሪክ አንጻር ሲሳሳት ይሄ የመጀመሪያው እንዳልሆነ ከታሪክ መዛግብት ዘንድ ብዙ መረጃዎችን ስንበረብር የሚጋለጥ ሐቅ ነው። እስከምንገናኝ በክርስቶስ ፍቅር ቸር ሰንብቱ! ማጣቀሻዎች እና ማስፈንጠሪያዎች [¹] https://al-maktaba.org/book/9783/383 [²] የተለያዩ የታሪክ ተመራማሪዎች እና ጸሐፊዎች ስለ ሙሴ የውልደት ዘመን ላይ የተለያየ አስተያየቶችን ሰንዝረዋል። በአማካይ ከወሰድነው ሙሴ እና ወንድሙ አሮን የተወለዱት 1400-1500  ዓ.ዓ ገደማ እንደሆነ አብዛኞቹ ምሁራን ይስማሙበታል(Seder Olam Rabbah,Jerome’s Chronicon (4th century) gives 1592 for the birth of Moses,The 17th-century Ussher chronologycalculates 1571 BC (Annals of the World, 1658 paragraph 164) [³] The gospel of the birth of Mary, 1:1-2, Gambero, Luigi (1999). Mary and the Fathers of the Church: The Blessed Virgin Mary in Patristic Thought. Ignatius Press.ISBN 978-0-89870-686-4. [⁴] https://quran.al-islam.com/Page.aspx?pageid=221&BookID=11&Page=1 [⁵] The Gospel of Pseudo-Matthew Chapter 20 [⁶] Protoevangelium of James Gospel

ማርያም የሐሩን እህት? Read More »

የመስዋዕቱ ልጅ ኢስሐቅ ወይስ ኢስማኢል?

ኢድ አል አድሃ(عيد الأضحى) ኢድ(عيد) ማለት በአል፣ ድግስ ወይም ለመታሰቢያነት የሚከበር ነገር ማለት ሲሆን አድሃ (أضحى) ወይም ቁርበን (قربان) ወይም ደግሞ የእብራይስጡ አቻ ቃል ቆርባን(קׇרְבָּן) ማለት “መስዋዕት/መባ” ማለት ነው። ኢድ አል አድሃ ሁለተኛው የሙስሊም ወገኖቻችን ክብረ በአል ነው። በዚህም ክብረ በአል ሙስሊም ወገኖቻችን ለመስዋዕትነት የሚሆነውን የበግ፣ የግመል፣ የፍየል ወየም የጠቦትን…ወዘተ የመሳሰሉትን የእንስሳትን ደምን ያፈሳሉ። የበአሉ እርሾ ወይም ጅማሮ በቁርአን ውስጥ የኢብራሂም(ዐሰ) ልጁን ለአምላኩ ለመሰዋት የታዘዘበትን ቀን ለማሰብ ሲባል የሚከበር በአል ነው። በቁርአን ላይ አላህ በሱረቱ አልሷፍፋት (የተሰላፊዎቹ ምዕራፍ) ላይ ስለ ተሰላፊዎች እምነት በሚናገርበት ክፍል በቁጥር 83 ላይ ከአማኞች መካከል የሆነው ኢብራሂም (ዐሰ) አንደኛው እንደሆነ ይናገራል። በዛው ክፍል በቁጥር 100 ላይ ደግሞ ኢብራሂም (ዐሰ) አንድን ጸሎትን ሲጸልይ እንመለከታለን፦ As-Saffat 37:100ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ፡፡(رَبِّ هَبْ لِى مِنَ ٱلصَّلِحِينَ) የኢብራሂምም አምላክም ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም ባሪያውን አበሰረው። ኢብራሂም (ዐሰ) ከባዱ ፈተና የሚጀምረው በቁጥር 102 ላይ ነው። አምላኩ የሰጠው ልጅ ለስራ በደረሰ ጊዜ ኢብራሂም (ዐሰ) በራዕይ አንድ ልጁን እንደሚያርድ ሁኖ ያልማል። እርሱም ለልጁ ስለ ራዕዩ ምን እንደሚያስብ በጠየቀው ጊዜ “የታዘዝከውን ሥራ” ብሎ ሲፈቅድለት እንመለከታለን። አሁን ዋናው ጉዳይና ጥያቄ ያ ለኢብራሂም (ዐሰ) የተበሰረው የመስዋዕቱ ልጅ ማነው? የሚለው ንግርት ነው! የዘመናችን የሙስሊም ኡስታዞች ሽንጣቸውን ገትረው በመከራከር በቁርአኑ ላይ የመስዋዕቱ ልጅ ኢስማኢል  ለማስመሰል የቁርአኑን አያህ የማይቀባቡት ነገር የለም። ከሁሉም በላይ ደግሞ አጃኢብ የሚያስብለው ጥርት እና ጥንፍፍ ብሎ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተነገረለትን የቃል ኪዳን ልጅ ይስሐቅን በእስማኤል ተክተውና አንሻፈው የመስዋዕቱ ልጅ እስማኤል እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል ማለታቸው ነው። “..የያዙት ነገር..” እንደሚሉት አበው በእኛ ዘንድ የሙስሊም ኡስታዞች መካከል ይሄንን ዜማ መስማቱ የተለመደ ነው። ሲጀመር ኡስታዞቹ የማይሆን የማይሆን የሙግት ነጥቦቻቸውን እየሰካኩ ለሙስሊሙ ተደራሲያን እየፈተፈቱ ሲያጎርሷቸው እኛንም (የክርስቲያኑን ማህበረሰብ) ለማታለል መጣጣራቸው ሳስብ ይገርመኛል። ለማንኛውም የኡስታዞቻቸውን ድርሳነ ባልቴት ወይም የአሮጊቶች ተረት የሆነውን የሙግት ሐሳባትን በሁለት ጎራዎች ከፍለን ስለ መስዋዕቱ ልጅ ማንነት እንመለከታለን፦ የቁርአናዊ ሙግት በመጀመሪያ ኢስማኢል ነብይ መሆኑ ለመስዋዕትነት የተዘጋጀው ልጅ እርሱ ነው የሚያስብለን አንድምታ የለም። ምክንያቱም እንዲሁ ኢስሐቅም ነብይ መሆኑን ቁርአናቸው ይነግረናል(Al-‘Ankabut 29:27)።[1] ስለዚህ ስለ ኢስማኢል ነብይነት መጥቀስና ማጠቃቀስ ጉንጭ ማልፋት ካልሆነ በስተቀር ለሙግቱ እንብዛም ውጤት የለውም። ለማንኛውም ኡስታዞቹ ያነሷቸውን ዋና ዋና ነጥቦችን እንመለከታቸዋለን። ቀጠሮ አክባሪው የዘመናችን የሙስሊም አቃብያነ እምነት ነን የሚሉት በሱረቱ መርየም 54 ላይ የተጠቀሰውን ክፍል ከሱረቱ አልሷፍፋት 102 ጋር በማጣመር የተሳሳተ ምስስሎሽን (wrong analogy) በመፍጠር ለመስዋዕትነት የቀረበው ኢስማኢል መሆኑን ለማሳየት ሞክረዋል። ነገር ግን በክፍሉ ላይ አውዳዊ ምልከታ ስናደርግ ሙግታቸው የሚያስኬድ ሁኖ አናገኘውም፦ Maryam 19:54በመጽሐፉ ኢስማዒልንም አውሳ፡፡ እርሱ ቀጠሮን አክባሪ ነበረና፡፡ መልክተኛ ነቢይም ነበር፡፡(وَٱذْكُرْ فِى ٱلْكِتَٰبِ إِسْمَٰعِيلَۚ إِنَّهُۥ كَانَ صَادِقَ ٱلْوَعْدِ وَكَانَ رَسُولًا نَّبِيًّا ) በዚህ ክፍል ላይ አላህ የኢብራሂምን ልጅ ኢስማኢልን ሲያመሰግነው እንመለከታለን። ኢስማኢል የአረቦች ሁሉ አባት ነበር። በተጨማሪም እርሱ ለቃለ ማሐላው እውነተኛና ታማኝ እንደነበር የሙስሊም ሊቃውንት ይናገራሉ።[2] የክፍሉን አውደ ሕታቴ ለመረዳት ቁጥር 55ን መመልከቱ አስፈላጊ ነው፦ Maryam 19:55ቤተሰቦቹንም በሶላትና በዘካ ያዝ ነበር፡፡ እጌታውም ዘንድ ተወዳጅ ነበር፡፡(وَكَانَ يَأْمُرُ أَهْلَهُۥ بِٱلصَّلَوٰةِ وَٱلزَّكَوٰةِ وَكَانَ عِندَ رَبِّهِۦ مَرْضِيًّا ) ኢስማኢል በጌታው ዘንድ ተወዳጅ የሆነበትና ከላይ ደግሞ አላህ ኢስማኢልን እንዲያስቡ ለምእመናን ሲናገር በኢስማኢል የግብር ጉዳይ ረገድ መሆኑ ግልጽ ነው። ኢስማኢል ለአላህ ለሆኑ ስራዎች ላይ ታማኝና አክባሪ ነብይ መሆኑን ከክፍሉ አውድ መረዳት እንችላለን። እንደውም የእንግሊዘኛው ትርጉም ቁጥር 54ን የሚገልጸው “he was true to his promise” ለቃለ መሐላው እውነተኛ ወይም ታማኝ እንደሆነ በሚያሳይ መልኩ ነው። And mention in the Book, Ishmael. Indeed, he was true to his promise, and he was a messenger and a prophet./English – Sahih International (Maryam 19:54)/ በተጨማሪም ኢብን ጁረይጅ ስለ ኢስማኢል ሲናገሩ፦ “He did not make any promise to his Lord, except that he fulfilled it./የሚፈጽመውን ካልሆነ በቀር ኢስማኢል ምንም አይነት ቃለ መሐላ ለጌታው አይገባም “Ibn Jurayj ስለዚህ ኢስማኢል ለቃለ መሐላው እውነተኛ፣ ታማኝና አክባሪ መሆኑን የሱረቱ መርየም ቁጥር 54 አውዳዊ አንድምታው ፍንትው አድርጎ ያሳያል። ቀጠሮ ከሚለው ፍታቴ ይልቅ ቃለ መሐላ ወይም ቃልኪዳን(promise) እንደሆነ የክፍሉ ዙሪያ ገባ ይነግረናል። “ቀጠሮውን አክባሪ” የሚለው ኃይለቃል በተጨማሪም የማያስኬደው በመጀመሪያ አላህ በሱረቱ አልሷፍፋት 102 ላይ ራዕይን ያሳየው ለኢብራሂም (ዐሰ) እንጂ ለልጆቹ ለኢስሐቅ ወይም ለኢስማኢል ፈጽሞ አይደለም። فَلَمَّا بَلَغَ مَعَهُ ٱلسَّعْىَ قَالَ يَٰبُنَىَّ إِنِّىٓ أَرَىٰ فِى ٱلْمَنَامِ أَنِّىٓ أَذْبَحُكَ فَٱنظُرْ مَاذَا تَرَىٰۚ قَالَ يَٰأَبَتِ ٱفْعَلْ مَا تُؤْمَرُۖ سَتَجِدُنِىٓ إِن شَآءَ ٱللَّهُ مِنَ ٱلصَّبِرِينَ ከእርሱ ጋርም ለሥራ በደረሰ ጊዜ «ልጄ ሆይ! እኔ በሕልሜ እኔ የማርድህ ሆኜ አያለሁ፡፡ ተመልከትም፤ ምን ታያለህ?» አለው፡፡ «አባቴ ሆይ! የታዘዝከውን ሥራ፡፡ አላህ ቢሻ ከታጋሾቹ ሆኜ ታገኘኛለህ» አለ፡፡ በተጨማሪም አላህ የመስዋዕቱን ቀጠሮ የሰጠው ለአባቱ ለኢብራሒም(ዐሰ) እንጂ ለልጁ አልነበረም። ምክንያቱም የራዕዩና የትእዛዙ አክባሪ አባቱ እንጂ ልጁ አይደለም። በተጨማሪም በቀጠሮው ቀን ለመሰዋት ልጁን የወሰደው አባትየው እንጂ ልጁ አይደለም። ስለዚህ ለመስዋዕትነት የተቀጠረው ኢስማኢል የቀጠሮው አክባሪ ነበር የሚለው አንድምታ ኪስ ወለድ እንጂ አውዳዊ አለመሆኑን ለመረዳት አያዳግትም። የኢብራሒም ጸሎት ሌላው የሙግት ነጥብ ብለው የሚያቀርቡት ደግሞ “ኢስማኢል/إِسْمَٰعِيْل”  ማለት “አምላክ ይሰማል” ማለት ስለሆነ ኢብራሒም ደግሞ በቁጥር 100 ላይ ወደ አላህ በጸለየው መሰረት ልጅን ሰጠው የሚል ነበር። ነገር ግን ከአውዱ ተነስተን ስንመለከት አላህ ለኢብራሒም በጸሎቱ መሰረት የተሰጠው ልጅ ኢስሐቅ እንጂ ኢስማኢል እንዳልሆነ እንረዳለን። ሲጀመር ኢስሐቅ(إسحاق) ወይም በእብራይስጥ ይሽሐቅ(יִשְׂחָק) ደስታ፣ ሳቅ ወይም ብስራት ማለት ነው። በቁጥር 100 ላይ ነብዩ ኢብራሂም(ዐሰ) ጌታዬ ሆይ! ከመልካሞቹ የሆነን (ልጅ) ስጠኝ(رَبِّ هَبْ لِى مِنَ ٱلصَّلِحِينَ) ብሎ ከጸለየ በኋላ፤ በቁጥር 101 ላይ ጌታውም ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው (فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍ) ብሎ ሲናገር እንመለከታለን። አስተውሉ! የጌታው መልስ ላይ “አበሰርነው” የሚለውን ቃል ከኢስሐቅ ጋር እንጂ ከኢስማኢል የስም ትርጉም ጋር ፈጽሞ የሚገናኝ አይደለም። እንደውም ስለ ልጁ ማንነት በዛው ሱራ በቁጥር 112 ላይ ግልጽ አድርጎ የብስራቱ ልጅ ኢስሐቅ እንደሆነ ይነግረናል በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን(وَبَشَّرْنَٰهُ بِإِسْحَٰقَ نَبِيًّا مِّنَ ٱلصَّلِحِينَ)በተጨማሪ በሱረቱ ሁድ 11፡69-71 ያለውን ክፍል ስንመለከት በቁጥር 101 ላይ ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው የሚለው ንግግር ለኢስሐቅ መሆኑን ግልጽ የሚያደርግ ክፍል ነው። 11:69 – መልክተኞቻችንም ኢብራሂምን በ(ልጅ) ብስራት በእርግጥ መጡት፡፡ ሰላም አሉት፡፡ ሰላም አላቸው፡፡ ጥቂትም ሳይቆይ ወዲያውኑ የተጠበሰን የወይፈን ስጋ አመጣ፡፡11:70 – እጆቻቸውም ወደ እርሱ የማይደርሱ መኾነቸውን ባየ ጊዜ ሸሻቸው፡፡ ከነሱም ፍርሃት ተሰማው፡፡ «አትፍራ እኛ ወደ ሉጥ ሕዝቦች ተልከናልና» አሉት፡፡11:71 – ሚስቱም የቆመች ስትኾን (አትፍራ አሉት) ሳቀችም፡፡ በኢስሐቅም አበሰርናት፡፡ ከኢስሐቅም በኋላ (በልጁ) በያዕቁብ (አበሰርናት)፡፡ ከኢስሐቅ ሌላ አካል በዚህኛው የሙግት ሐሳብ ላይ ደግሞበቁጥር 112 በኢስሐቅም አበሰርነው፡፡ ከመልካሞቹ የሆነ ነቢይ ሲሆን በሚለው ክፍል ላይ በኢስሐቅም ስለሚል “-ም” የምትለው ጥገኛ ምእላድ ከኢስሐቅ ተጨማሪ ሌላ አካል እንዳለ ያመለክታል የሚል ሙግት ነው። ነገር ግን ይሄ ሐሳብ ፈጽሞ የሚያስኬድ አይደለም። አብዱሉ በክፍሉ ላይ ሁለት ልጅ የተባሉ አካላት እንዳሉ ይናገራል። የመጀመሪያው ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም ሲሆን ሁለተኛው በኢሥሐቅ ብሎ ከፋፍሎ እንመለከታለን። እንደዛ ከሆነ የሙግቱ ሃሳብ አጠያያቂ ይሆናል። ምክንያቱም በእርሱ ሎጂክ ከሄድን በቁጥር 101 ላይ አላህ ለኢብራሒም ታጋሽ በሆነ ወጣት ልጅም አበሰርነው (فَبَشَّرْنَٰهُ بِغُلَٰمٍ حَلِيمٍ ) በሚለው አንቀጽ ላይ ወጣት ልጅም በሚለው ኃይለ ቃል ይሰመርበት “-ም” የምትለው ምእላድ አሁንም በእነርሱ ሎጂክ ኢስማኢል ነው ብለው ከሚያምኑት አካል ሌላ ከእርሱ

የመስዋዕቱ ልጅ ኢስሐቅ ወይስ ኢስማኢል? Read More »

መሬትን ተሸካሚው ፍጡር  (“አል-ኑን/النون”)

በእስልምናው አስተምህሮት ውስጥ አፈታሪካዊ እና ተረታዊ ከሆኑት ታሪኮች መካከል አንደኛው ግዙፉ እስላማዊው አሳ ነባሪ ( الحوت الإسلامي ፣ አል-ሁት አል-ኢስላሚ) ይሄም ፍጡር ምድርን በጀርባው እንደሚሸከም የተገለጸለት  አፈታሪካዊው ፍጡር ነው፡፡ ታዳ  ይሄ እስላማዊው አውሬ/አሳነባሪ(አል-ሁት/ٱلْحُوتِ) በቁርአን ላይ “ምድር ተሸካሚ አሳ” ወይም “አል-ኑን/النون” ተብሎ ተጠርቷል። ቁርአኑ ስለዚህ ፍጡር ግልጽ በሆነ ሁኔታ አላስቀመጠልንም። በዚህም ምክንያት በአንዳንድ የሙስሊም ሊቃውንቶች መካከል እስካሁኑ ሰአት ድረስ ያልተፈታ ትልቅ ንትርክን የፈጠረ ለዘመናዊው ሳይንስ ጥናቶች እንግዳና አጠያያቂ የሆነ ጉዳይ ነው። እኔም ስለዚህ ፍጡር ጉዳይ በስፋት በመመልከት አንዳንድ እስላማዊ ጽሁፎችን ማለትም ሐዲሳትን እና የተለዩ ተፍሲራትን እያገላበጥን ለማሳየት ቀርቤያለሁ። ➙ ከላይ በጨረፍታ ለመመልከት እደሞከርነው “አል-ኑን/النون” በውሀ ውስጥ ከሚኖሩ የአሳ ዝርያዎች መካከል አንዱ ነው። በቁርአን በሱረቱል አል-ቀለመ በአንደኛው አያት ላይ ተጠቅሶ እናገኘዋለን። ይሄንን አያት በእስልምናው ማህበረሰብ ውስጥ እጅጉን እውቅና ካላቸው የቁርአን ተፍሲሮች (ኢብን-ከሲር፣ አል-ቁርጡቢ፣ ጃለለይን እና አት-ጠበሪ) እንደሚያስረዱን ከሆነ “ኑን” የሚባለው ግዙፍ አሳ ነባሪ እንደሆነና ምድርን የተሸከመ ፍጡር እንደሆነ ይነግሩናል። አል-ቀለም 68:1نٓۚ وَٱلْقَلَمِ وَمَا يَسْطُرُونَነ.( #ኑን)፤ በብርእ እምላለሁ በዚያም (መልአኮች) በሚጽፉት፡፡ ኢብን ከሲር አል-ቀለም 68:1 ተፍሲር፦ታላቁ ሙፈሲር ኢብን ከሲር በተፍሲሩ ላይ ስለ ኑን ሲናገር፦ አላህ ‹ ኑን› የተባለውን ከፈጠረ በኋላ ምድር በኑን ጀርባ ላይ እንደዘረጋ ይናገራል፡፡ ከዛም ተረቱ ይቀጥላል #ኑን የሚባለው ፍጡር ደነበረ ወይም ተረበሸ ይለናል። በዚህ መሀል ምድር ማረግረግ ወይም መንቀጥቀጥ ጀመረች። አላህ ለዚህ ችግር ሲል ተራሮችን ፈጠረ። እነዚህም ተራሮች ምድር እንዳትነቃነቅ እንደ ችካል ቸከላቸው ይለናል። እንደውም በቁርአን 78:7 ላይ “…ጋራዎችንም(ተራሮችን) ችካሎች አላደረግንምን(وَٱلۡجِبَالَ أَوۡتَادًا)?)…”  አላህ ተራሮችን የቸከላቸው የመሬትን መንቀጥቀጥ ለማስተካከል እንደሆነ ተፍሲራት ይነግሩናል(ጃላለይን, ኢብን ከሲር ተፍሲር)። ምን ይሄ ብቻ አሁም አፈታሪካዊ ተረቱ አላበቃም አል ባግሃዊ እና ሌሎች የሙስሊም ሙህራኖች እንደተናገሩት በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ ሰባቱ መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል ብለው ያስባሉ። እስቲ ይሄን ታሪክ ከኢማም ኢብን ከሲር ተፍሲር በተወሰነ መልኩ እንመልከት፦ “…ከዚያም አላህ ‹ኑን› የተባለውን ከፈጠረ በኋላ ሰማይ የተፈጠረበት ጭስ እንዲወጣ አደረገ፡፡ ከዚያም ምድር በኑን ጀርባ ላይ ተዘረጋች፡፡ ከዚያም ኑን ስለደነበረ ምድር ማረግረግ ጀመረች፤ ነገር ግን (አላህ) ምድርን እንዳትንቀሳቀስ አድርጎ በተራሮች ቸከላት… “ኢብን አቡ ኑጃኢህ እንደተናገረው ኢብን አቡ በኪር በሙጃሂድ እንዲህ ተብሎ ተነግሮት ነበር፣ “ኑን ከሰባቱ መሬቶች በታች የሚገኝ ታላቁ አሣ እንደሆነ ይነገራል፡፡” በተጨማሪም አል ባግሃዊ (አላህ ነፍሱን ያሳርፋትና) እንዲሁም ሌሎች ሐታቾች እንደተናገሩት በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ ሰባቱ መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል፡፡…”[1] ኑን ለሚለው ቃል ትርጓሜ ሲያስቀምጥ ደግሞ “…ኑን የሚባለው ትልቅ አሳነባሪ ነው(Nun is a big whale/نۤ حوت عظيم)…” በማለት ኢብን ከሲር ትንታኔውን አስቀምጧል።[2] አል-ቁርጡቢ ተፍሲር 68:1 نۤ> الحوت الذي تحت الأرض السابعة>”…<ኑን>ከሰባተኛው(السابعة) መሬት(الأرض) በታች(تحت) የሚገኘው አሳ ነባሪ(الحوت) ነው….”[3] በአል-ቁርጡቢ ተፍሲር መሰረት ” ኑን” የሚባለው ከሰባተኛው  መሬት በታች የሚገኝ አሳ ነባሪ እንደሆነ ይነግረናል። ልብ በሉ “…ከሰባተኛው(السابعة)…” ሰባት ምድር እንዳለም ከላይ በኢብን ከሲር ተፍሲር ላይ ተመልክተናል። እነርሱም ተደራራቢ እንደሆኑ “ታሐት(تحت)” ወይም “ከታች/ከስር” የሚለው ቃል ያስረዳናል። ተፍሲር አት-ጠበሪ 68:1አት-ጠበሪ በሱረቱል አል-ቀለም 68:1 ላይ ማብራሪያ ሲያስቀምጥ እንዲህ ብሏል፦“…هو الحوت الذي عليه الأرَضُون…”“…ሰባቱ ምድሮች የተቀመጡበት ፍጡር አሳ ነባሪ(الحوت) ነው…”[4] በእስልምናው ኮስሞሎጂ መሰረት አላህ ሰባት ሰማያትን እንደፈጠረ ሁሉ ሰባት ምድሮችንም ፈጥሯል(Quran 65:12)። እነዚህም ጠፍጣፋ ምድሮች በአሳ ነባሪው ላይ ተደራርበው ተቀምጠው እንደሚገኙ ጥንታዊ የሙስሊም ሊቃውቶች ይነግሩናል። ተፍሲር አል-ከቢር(አር-ረዚ)/tefsir Al kabir(by Ar-Razi)፦ “…بالحوت الذي على ظهره الأرض وهو في بحر تحت الأرض السفلى…” በዚህም ተፍሲር ላይ በጀርባው ምድር የሚሸከመው ዓሳ ነባሪ እንደሆነና አል-ከቢር እዚህ ዓሳ ነባሪ ጀርባ ላይ ሚዛናዊ የሆኑ ጠፍጣፋ መሬቶች እንዳሉ  ይነግረናል፡፡[5] ተፍሲር አል-ቃዲር/Tafsir Al-Qadir (by Shawkani) ተፍሲር አል-ቃዲር/Tafsir Al-Qadir (by Shawkani) ይህ ተፍሲር ከ 18 ኛው ክፍለዘመን ጀምሮ ዓለም ዓሳ ነባሪ ጀርባ ላይ ተሸክሟል የሚል ሀሳብን በመደገፍ ያረጋግጣል። “….ምድርን የተሸከመው ፍጡር አሳ ነባሪ/الحوت ነው…..”/Fath Al-Qadir on 68:1__[6] ሐዲስ ከኢብን አባስ (ቱርጁማን ኡል-ቁርአን/ترجمان القرآن)(ሐዲስ ከአት-ጠበሪ) ኢብን አባስ እንደተናገረው፦አላህ የፈጠረው የመጀመሪያ ነገር ብእርን  ስለነበረ “ጻፍ!” አለው፡፡ እናም እስከ ሰዓቱ (የፍርድ ቀን) ድረስ ምን እንደሚሆን ጽፏል፤ ከዚያም ኑንን ከውሃ በላይ ፈጠረ ከዚያም ምድርን በእርሱም ላይ ተጫነች፡፡(ታሪኽ አት-ታባሪ) [7] ይህም ሀዲስ(ትረካ) በሀዲሳት ሰንሰለት  ትክክለኛ(ሰሒህ/صحيح) ትረካ ተደርጎ ተቆጥሯል፡፡[7] መሐመድ ለኢብን አባስ ዱዓ (ጸሎት) ስላደረገ አላህም የቁርአንን ትክክለኛ አተረጓጎም ያስተምረው ነበር፡፡እንዲሁም ኢብን አባስ (ቱርጁማን ኡል-ቁርአን/ترجمان القرآن) “የቁርአን ተርጓሚ” ተብሎ ተጠርቷል ፣ ምክንያቱም ስለ ራእዮች ትርጓሜ (ቃል በቃል መተርጎም) የሚሰጥና ጥልቅ ዕውቀት ያለው ሰው ነበር። ኢብኑ ዐባስ (ራአ) እንደተናገሩት፦ነቢዩ (ሶ.ዐ.ወ) አቅፈውኝ “አሏህ ሆይ! የመጽሐፉን (ቁርአን) እውቀት አስተምሩት ፡፡ ”(ሳሂህ ቡኻሪ 9:92:375) ታድያ ይህ በቁርአን ጥልቅ እውቀት ያለው አሊም ተራራዎቹ በቁርአን ውስጥ እንደ ችካል እንዴት እንደተደረጉ የእርሱ ትረካ ያስረዳል፡፡ ምክንያቱም በባህላዊው እስላማዊ የኮስሞሎጂ መሠረት ምድር ከዓሣ ነባሪው ጀርባ ላይ ትነቃነቅ (ትንቀጠቀጥ) ስለነበረ አላህ ምድርን ዓሣ ነባሪው ላይ ተረጋግታ እንድትቀመጥ ተራሮችን እንደ ችካል እንዳደረጋቸው በግልጽ ሁኔታ ተርኮልናል፡፡ በመጨረሻም ከዚህ ሁሉ መረጃዎችና ማስረጃዎች የምንረዳው ነገር ቢኖር አላህ ሰባት መሬቶችን ፈጥሮ በአሳ ነባሪው(“አል-ኑን/النون” ) ጀርባ ላይ ደራረቦ በማስቀመጥ ከዛም አሳ ነባሪው(“አል-ኑን/النون” ) ሲደነብር መሬት እዳትነቃነቅ በተራሮች በመቸከል እንድትረጋጋ አድርጓል። ይባስ ብሎም በዚህ ዓሣ ጀርባ ላይ ውፍረቱ ከሰማይና ከምድር የሚበልጥ ትልቅ ዓለት አለ፡፡ ከዚህ ዓለት በላይ ደግሞ አርባ ሺህ ቀንዶች ያሉት ኮርማ ቆሟል፡፡ በዚህ ኮርማ ላይ ሰባቱ መሬቶችና በውስጣቸው የሚገኙት ሁሉ ተቀምጠዋል ብለው በማሰብ ይህ ለሳይንስና ለእውነታ ሆድና ጀርባ የሆነን ነገር ከአንዳንድ የመሰለኝን ልናደርግ ከሚሉ ፈላስፋዎች ቀጥታም ሆነ ተጨማምሮበት የተቀዳ አፈታሪክን የአምላክ መገለጥ ነው ብሎ መቀበል በጣም ሞኝነት ነው። አንዳንድ የዘመኔ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ስኮላሮችና ዳኢዎች ይሄ ነገር አልዋጥ ሲላቸው የውሸት የትረካ ሰነድ ወይም አምላካዊ ንግግር የሆነ ሀሳብ አይደለም ይሉናል።[8] ነገር ግን አይኑ የፈጠጠ በድሮ ዘመን በነበሩት የእስልምና ሊቃውንቶች መካከል ተቀባይነትን ያተረፈ ታሪክ እንደሆነ ከተፍሲራትና ከሐዲስ ለመመልከት ችለናል። ይሄን የመሰለ ተረትና አፈታሪክ ታቅፈው ነው እነ ዶክተር ዛኪር ናይክና ቢጤዎቹ ቁርአን ከሳይንስ ጋር አይጣረስም የሚሉን። በመሰናበቻዬም አንድ ነገር ተናግሬ ልደምድም፦ እውነት ቁርአን የፈጣሪ ንግግር ነውን? ከሆነስ ለምን ከሐቅና ከሳይንስ ጋር ላይስማማ ሊጣረስ ቻለ? እውነትን ፈልጉ እውነትም አርነት ያወጣችኋል። ማጣቀሻዎችና ማስፈንጠሪያዎች [1] Tafseer Ibn Katheer;Online Edition: http://quran.al-islam.com/Tafseer/DispTafsser.asp?l=arb&taf=KATHEER&nType=1&nSora=68&nAya=1 [2] https://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=0&tTafsirNo=7&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1 [3] https://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=1&tTafsirNo=5&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1 [4]  https://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=1&tTafsirNo=1&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1 [5]  https://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=1&tTafsirNo=4&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1 [6] https://altafsir.com/Tafasir.asp?tMadhNo=1&tTafsirNo=9&tSoraNo=68&tAyahNo=1&tDisplay=yes&UserProfile=0&LanguageId=1 [7]  https://hdith.com/?s=%D8%AB%D9%85+%D8%AE%D9%84%D9%82+%D8%A7%D9%84%D9%86%D9%88%D9%86+%D9%81%D9%88%D9%82+%D8%A7%D9%84%D9%85%D8%A7%D8%A1%D8%8C+%D8%AB%D9%85+%D9%83%D8%A8%D8%B3+%D8%A7%D9%84%D8%A3%D8%B1%D8%B6+%D8%B9%D9%84%D9%8A%D9%87 [8]  https://islamqa.info/en/114861

መሬትን ተሸካሚው ፍጡር  (“አል-ኑን/النون”) Read More »

የቀድሞ ነብያት ክርስቲያን አልነበሩምን?

ለሙስሊም ሰባኪያን ሙግት ምላሽ የእግዚአብሔር ቅዱስ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሥጋ የተገለጠ አምላክ መሆኑንና ከእርሱም በፊት የነበሩት ነብያት እና የእምነት አባቶች ከዛም በመቀጠል በሐዲስ ኪዳን የነበሩት ሐዋርያቶች እርሱን እንደተከተሉ የክርስትና መሠረት እምነት የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ያስተምራል። በተጻራሪው ግን ቅዱሳት መጻሕፍት ተጽፈው ከተጠናቀቁ ከብዙ መቶ ዓመታት በኋላ የመጣው እስልምና ደግሞ በቀድሞ ነቢያት ተወርቶ እና ተሰብኮ የማይታወቅ አምላክ አስተዋወቀን፤ ከዛም አልፎ ተርፎ ተከታዮቹ ሙስሊም እንጂ ክርስቲያን አይደሉም ብሎ ብቻውን ቆሞ ያስተምራል። ኢስላም ናቸው እንጂ ክርስቲያን አይደሉም የሚለው ንግግር በብዙ ሙስሊሞች ዘንድ እንደ ትልቅ ርዕስ አድርገው ክርስቲያኖችን ጋርም በጥያቄ መልክ ሲቀርብ ይስተዋላል። እኛም ይህን አስተምሮታቸው ከሆነው ከቁርኣን የመነጨ እና ጥያቄያቸው በራሱ ማስረጃ የሌለው ኪስ ወለድ ሙግት ሀሳብ መሆኑን እንመለከታለን። በመጀመሪያ ግን ክርስቲያን እና ደቀመዛሙርት ማለት ምን ማለት ነው? ክርስቲያን(Χριστιανούς/ክሪስትያኑስ)፦ ማለትም የክርስቶስ ተከታይ ወይም በክርስቶስ ህግ እና ትምህርት የሚመራ ማለት ነው። የእርሱ አቻ ቃል የክርስቶስ ደቀመዝሙር/μαθητής  ሲሆን ጥቅልል ትርጉሙ “ የክርስቶስ ተማሪ ”ወይም” የክርስቶስ ተከታይ” ማለት ነው። የሐዋርያቶች ደቀመዝሙር የነበሩት ከማን እግር ስር እንደተማሩ ለመግለፅ ይህንን ቃል ይጠቀሙትም ነበር። ለቅምሻ ታህል ደቀመዝሙር በሚለው ቃል ላይ አንድ ምሳሌ ላሳይ፦ ጶሊቃርጶስ በ70ዓ.ም ተወልዶ በ155 ዓ.ም ወይም በ160 ዓ.ም የሞተ የሐዋሪያው ዮሐንስ ደቀመዝሙር(ማቴቴስ/μαθητής) እንደነበር የቤተክርስቲያን የታሪክ መጻሕፍት ያወሱናል። በተጨማሪ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ዘአቴንስ ደግሞ ስሙም በሐዋ17:34 ላይ የተጠቀሰ ሲሆን ይህ የቤተክርስቲያን አባት ደግሞ የሐዋርያው ጳውሎስ ደቀመዝሙር (ማቴቴስ/μαθητής) እንደነበር ይነገራል። ይህ ማለት ጶሊቃርጶስ የሐዋርያው ዩሐንስ ተከታይ ሲሆን፤ ቅዱስ ዲዮናስዮስ ዘአቴንስ የቅዱስ ጳውሎስ  ደቀመዝሙር እንደሆነና የአስተማሪያቸው ማቴቴስ ተብለው መጠራታቸውም ከታሪክ ክታባት እንረዳለን። በአንዳንድ የሙስሊም ተሟጋቾች የኢየሱስ ክርስቶስ ደቀመዛሙርት እንዲሆኑ እንጂ ክርስቲያን እንዲሆኑ ኢየሱስ ሐዋርያትን አላዘዘም ይላሉ። ነገር ግን የክርስቶስ ደቀመዝሙር ማለት እና ክርስቲያን ከሚለው ቃል ጋር ተመሳሳይ ነው። ስለዚህ ደቀመዛሙርቴ ካለ( ዮሐ 15:8፣ 13:35፣ ማር 14:14፣ ሉቃ 22:11፣ ማቴ 26:18…) የእርሱ ተከታይ(ክርስቲያን) መሆናቸውን ምንም ሳናቅማማ እንቀበላለን ማለት ነው። ስለ ክርስትና እና ደቀመዝሙር ይህን ያህል ካየን ነብያቱ ክርስቲያን ነበሩ ወይ? ክርስቲያን ከነበሩስ ምንድነው ማስረጃቹ? የሚለውን በመመለስ እንዝለቅ። የክርስቶስ ምስክርነት በማቴዎስ ወንጌል 5፡3-13 ላይ በተለምዶ ይህ ክፍል የተራራው ስብከት በመባል የሚታወቅ ሲሆን ሙሉ ዐውደ ምልከታ እያነበባቹ ስትወርዱ ቁጥር 11-12 ላይ አንድ አስደናቂ ንግግር እንመለከታለን እንዲህ ይላል፦ “ሲነቅፉአችሁና ሲያሳድዱአችሁ በእኔም ምክንያት ክፉውን ሁሉ በውሸት ሲናገሩባችሁ ብፁዓን ናችሁ።”  ማቴዎስ 5፥11 እዚህ ክፍል ላይ ኢየሱስ እርሱን በመከተላቸው ስለሚደርስባቸው ነቀፌታ፣ ስደትና ችግር ሁሉ መፍራት እንደሌለባቸው፤ ጨምሮም ብፁዓን እንደሆኑ ይነግራቸዋል። ስደቱም በክርስቶስ ያለ መሆኑን በቁጥር 11 ላይ በእኔ ምክንያት የሚል ንግግር ያስቀምጣል። በዚህም አላበቃም ይቀጥልና በቁጥር 12 ላይ እንዲህ ይለናል፦ “ዋጋችሁ በሰማያት ታላቅ ነውና ደስ ይበላችሁ፥ ሐሴትም አድርጉ፤ ከእናንተ በፊት የነበሩትን ነቢያትን እንዲሁ አሳድደዋቸዋልና።”  ማቴዎስ 5፥12 ክርስቶስን የሚከተሉ ሰዎች ዋጋቸው ታላቅ እንደሆነ! እርሱንም መከተል የዚህ ስደት እና እንግልት ከንቱ እንዳልሆነ፤ ይልቁንም “ከእናተ በፊት የነበሩትን ነብያቶች እንዲሁ አሳድዷቸዋልና በማለት በረከቱን ይነግራቸዋል። ምክንያቱም በክፍሉ ዐውድ ሲብራራ እነርሱ ተነቅፈዋል፣ ያላቸው ነገር አጥተዋል፣ ስለ እርሱ ሲሉ መረባቸውን ጥለው ተከትለውታል መሠደዱ እና ማጣቱ “በእኔ ምክንያት ነው ይላቸዋል” ነገር ግን እኔን መከተላችሁ ከንቱ አይደለም፤ ብሎ ይቀጥልና፦ ከእናተ በፊት የነበሩትን ነብያት እንዲሁ አሳድዷቸዋልና በማለት ከቀድሞ ነብያት ጋር አገናኝቶት የቀድሞዎቹም መሠደዳቸው በእርሱ መሆኑን ይነግራቸዋል። በተጨማሪም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ 23፥34-37 ላይ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የኦሪት ህግ መምህራንን እና ፈሪሳውያንን ሲነቅፍ እንዲህ ብሎ ሲናገር እንመለከታለን፦ ማቴዎስ 23 ³⁴ ስለዚህ፥ እነሆ፥ ነቢያትንና ጥበበኞችን ጻፎችንም ወደ እናንተ እልካለሁ፤ ከእነርሱም ትገድላላችሁ ትሰቅሉማላችሁ፥ ከእነርሱም በምኵራባችሁ ትገርፋላችሁ ከከተማም ወደ ከተማ ታሳድዳላችሁ፤³⁵ ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።³⁶ እውነት እላችኋለሁ፥ ይህ ሁሉ በዚህ ትውልድ ላይ ይደርሳል።³⁷ ኢየሩሳሌም ኢየሩሳሌም ሆይ፥ ነቢያትን የምትገድል ወደ እርስዋ የተላኩትንም የምትወግር፥ ዶሮ ጫጩቶችዋን ከክንፎችዋ በታች እንደምትሰበስብ ልጆችሽን እሰበስብ ዘንድ ስንት ጊዜ ወደድሁ! አልወደዳችሁምም። ትኩረት ሰጥታቹ ተመልከቱ፤ ቅዱሱም ማቴዎስ የክርስቶስን ንግግር አጽንዖት ሰጥቶ ነው እየጻፈልን ያለው። የጌታችን የኢየሱስ ንግግርም ዝም ብሎ ሀይለ ቃል አይደለም ይልቁን የርዕሳችን ዋና ማገር እንጂ። እንዲህ ነው ነገሩ፦ ጌታችን እሱን ባለመቀበላቸው የኢየሩሳሌም ነዋሪዎች በራሳቸው ላይ ሊደርስባቸው ያለውን መከራ ተናግሯል ነገር ግን ከዛ መከራ ያርፉ ዘንድ ዶሮ በክንፎቿ ስር እንደ ምትሰበስብ ሲጠራቸው እንመለከታለን። በዛው ክፍል ላይ፦ “እኔ ወደ እናንተ ነቢያትን እልካለሁ” ስለዚህ ያለ ጥርጥር እዚህ ነብያትንን፣ ሐዋርያትን እና ሌሎች የእሱን ተከታዮች መሆኑን እየገለፀ ነው። ይህ ማለት ምን ማለት ነው? በድጋሚ ወደ ማቴዎስ ተመልሳቹ ጌታችን የተናገረውን እና ያለውን አስተውሉ፦ “ከአቤል…እስከ ዘካሪያስ” ስለ አቤል ሞት ተጽፎ የሚገኘው በዘፍ 4፥8 ላይ ሲሆን፣ ስለ ዮዳሄ ልጅ ስለ ዘካሪያስ ሞት ደግሞ በ2ዜና 24፥20-22 ተጽፏል። ጌታችን ኢየሱስ በዚህ ላይ ምን እያለ ነው ከተባለ በአይሁድ የቅዱሳት መጻሕፍት ቅደም ተከተል መሠረት፣ መጽሐፈ ዜና መዋዕል የብሉይ የመጨረሻ መጽሐፍ ነው። “ከአቤል እስከ ዘካሪያስ” የሚለው አባባል እኛ “ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ” ከምንለው ጋር ተመሳሳይ ነው። ታዲያ ጌታችን ይህን ሀይለ ቃል መጠቀሙ የብሉይ አጠቃላይ ሰማዕታን የሆኑ መልዕክተኞች እርሱ እንደላካቸው ማስገንዘቡን እንመለከታለን። አስተውሉ እኔ ልኬ ነበር ገደላችሁ እያላቸው ነው። የትኛው ነብይ እንዲህ ሊናገር ይችላል? ለዚህም ነው ከጌታችን ንግግር ተነስተን ኢየሱስ ያህዌ ነው፣ የቀድሞም ነብያት እርሱን ሲከተሉ ነበር የምንለው። የእነዚህ ክፍል ማብራሪያ ከሌሎች ቅዱሳት መጽሐፍት ጋር በማመሳከር ከእነርሱ(ከሐዋርያቶቹ) በፊት የነበሩት ነቢያትና የእምነት አባቶች ጨምሮ ክርስቶስን እንደተከተሉ ስለ እርሱም ሲሉ መከራን እንደተቀበሉ እናም እንደተነቀፉ ከዚህ በመቀጠል በቅድመ ተከተል እንመለከታለን። የሌሎች ሰዎች ምስክርነት ቅዱሳት መጻሕፍት ከዚህ ርዕስ አንፃር ምን ያስተምራሉ? የሚለውን ለመመለስ በዕብራውያን መልዕክት ምዕራፍ 11:1-40 ያለውን መመልከት ለዚህ ጥያቄ ጥሩ ምላሽ የምናገኝ ይሆናል። በዚህ የታሪክ ምዕራፍ ስለ እምነት አባቶች ከሚያወሳ ክፍል ከሆነው ዕብራውያን ምዕራፍ 11:25-26 የሙሴ ያሳለፈው የህይወት ውጣውረድ እንዲህ እንዲህ በማለት ያስቀምጣል፦ “ከግብፅም ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መነቀፍ እጅግ የሚበልጥ ባለ ጠግነት እንዲሆን አስቦአልና ለጊዜው በኃጢአት ከሚገኝ ደስታ ይልቅ ከእግዚአብሔር ሕዝብ ጋር መከራ መቀበልን መረጠ፤ ብድራቱን ትኵር ብሎ ተመልክቶአልና።”  — ዕብራውያን 11፥25-26 በደንብ አስተውሉ የዚህን ክፍል ጥቅስ ከማቴዎስ ወንጌል 5:11-12 ጋር ስናነፃፅረው ጥልቅ መልዕክት ይነግረናል። ከላይ በተራራው ስብከት ላይ እርሱን በመከተል ስለሚደርስ መከራ ከነገራቸው በኋላ በዚህም ሳያበቃ እነርሱ ብቻ ሳይሆኑ በእርሱ ምክንያት መከራው የበዛባቸው የቀድሞም ነቢያቶችም ጭምር በመከራ ውስጥ ማለፋቸውንና የቀኝ እጃቸውን አሻራ አሳርፈው እንዳለፉ ይነግረናል። ታዲያ ከቀድሞ ነብያት ውስጥ ታላቁ ነቢይ የነበረው ሙሴ <<ከግብፅ ጮማ እና ብዙ ገንዘብ ይልቅ ስለ ክርስቶስ መከራን መቀበል>> እንደመረጠ የዕብራውያን መጽሐፍ ይነግረናል። ስለዚህ ክርስቲያን በሚለው የቃሉ ትርጓሜ መሠረት በመነሳት ከቀድሞ ነብያት ውስጥ ሙሴ ክርስቲያን ማለትም የክርስቶስ ደቀመዝሙር (μαθητής/ማቴቴስ) እንደነበረ እንመለከታለን ማለት ነው። ታዲያ ታላቁ የብሉይ ኪዳን ነቢይ ሙሴ እንዴት ሆኖ ነው ክርስቶስን ተከትሎ ሙስሊም የሚሆነው? ሙስሊም ማለትስ ክርስቶስን መከተል ነውን? መልሱን ለአንባቢ ልተወው። የዕብራውያን መልዕክት ጸሐፊ በዚህ አላበቃም ተጨማሪ ጥልቅ ጠቢብ ሚስጥር እንዲህ በማለት ለተደራሲያኑ ይገልፅላቸዋል፦ “እነዚህም ሁሉ በእምነታቸው ተመስክሮላቸው ሳሉ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አላገኙም፥ ያለ እኛ ፍጹማን እንዳይሆኑ እግዚአብሔር ስለ እኛ አንዳች የሚበልጥ ነገርን አስቀድሞ አይቶ ነበርና።”  ዕብራውያን 11፥39-40 እነዚህ ሁሉ የተባሉት በቁጥር 38 ላይ በጠቅላላ ለመተረክ ጊዜ ያጥረኛል ያላቸውን መሆኑን በክፍሉ ዐውደ ምንባቤ ላይ መረዳት ይቻላል። ከላይ ባለው ጥቅስ በመጨረሻ ቁጥር ስር

የቀድሞ ነብያት ክርስቲያን አልነበሩምን? Read More »

Scroll to Top