bible

የዮሐንስ ወንጌል አጭር ሐተታ

መግቢያ ➥የዮሐንስ ወንጌል በዘመናት መሐል በቤተክርስቲያን ተወዳጅነቱን ጠብቆ የቆየ መጽሃፍ ሲሆን በሌሎች ለዘብተኛ ምሁራን ደግሞ “አራተኛው ወንጌል” በመባል ይጠራል። ከጥንታዊት ቤተክርስቲያን አባቶች መካከል አንዱ የሆነው ቀለሜንጦስ ዘእስክንድሪያ ደግሞ መንፈሳዊ ወንጌል በማለት አቆላምጦታል [1]፤ ይህንን ያለበትም ምክኒያት ዮሃንስ ወንጌሉን የጻፈው በመንፈስ ቅዱስ አነሳሽነት ነው ብሎ ስላመነ እንደነበር የአውሳብዮስ ዘቂሳርያ ዘገባ ያሳያል። ወንጌሉ ምንም ያህል አከራካሪ ጉዳዮች ቢኖሩበት፤ ከዘመናውያኑ ሥነ መለኮት ምሁራን አንዱ የሆነው ኮሊን ክሩዝ ደግሞ “ኁልቆ መሳፍርት ለሌላቸው የክርስትና ትውልዶች መነሳሳት የፈጠረና በስርዓት ላጠኑት ሁሉ ታላላቅ ሽልማቶችን ያስታቀፈ” [2] በማለት መስክሮለታል። የጸሃፊው ማንነት ➥የወንጌሉን ትክክለኛ ጸሃፊ በተመለከተ የተለያዩ አመለካከቶች ቢኖሩም በሐዋርያው ዮሃንስ ስለመጻፉ የሚቀርቡ ሃሳቦች ከሌሎች ይልቅ ተጨባጭነት አላቸው። በቅድሚያ የመጽሃፉን ውስጣዊ ማስረጃዎች (internal evidences) እንመልከት። ጸሃፊው የአረማይክ ቋንቋ ችሎታ ያለው አይሁዳዊ ስለመሆኑ ለሚጠቅሳቸው አንዳንድ የእብራይስጥና አራማይክ ቃላት ትርጉም ማስቀመጡ ምስክር ነው፤ የአይሁድን ወግና ስርአት ጠንቅቆ የሚያውቅ ሰው መሆኑን የገዛ ጽሁፉ ያሳያል (ዮሃ 4፡ 9፣ 20)፤ ስለ መጀመሪያው ክፍለ ዘመን የእስራኤል መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ በትክክል እንደሚያውቅም ከወንጌሉ ላይ መረዳት ይቻላል (ዮሃ 1፡44፣ 2፡1፣ 4፡5፣ 4፡21፣ 9፡7፣ 11፡18፣ 18፡1)፤ እንደዚሁም የአይን ምስክርና የኢየሱስ የቅርብና ተወዳጅ ሰው እንደነበርም ይናገራል (ዮሃ 1፡14፣ 19፡35) [3]።ከኢየሱስ የቅርብ ደቀ መዛሙርት መሃል ያዕቆብ ብዙም ሳይቆይ ስለሞተ፤ እንዲሁም ጴጥሮስ ቶማስና ፊሊጶስ በሶስተኛ መደብ እየተጠሩ ስለተዘገቡ የጸሃፊው ማንነት ዮሃንስ የመሆኑ እውነታ የበለጠ ተአማኒነት አግኝቶአል። ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ ያሉ ማስረጃዎችን (External Evidences) በአጭሩ ስንዳስስ ደግሞ የጥንት የቤተክርስቲያን አባቶችን ምስክርነት እናገኛለን።ከላይ እንደተመለከትነው አውሳብዮስ ዘቂሳርያ በዘገበው መሠረት የእስክንድርያው ቀለሜንጦስ ይህንን ወንጌል መንፈሳዊ ወንጌል ብሎ ጠርቶታል። ቀለሜንጦስ ወንጌሉን በዚህ ስም የጠራውም ዮሐንስ ወንጌሉን የጻፈው በደቀ መዛሙርት ተገፋፍቶና በመንፈስ ቅዱስ ተነሳስቶ እንደሆነ በማመኑ እንደነበረ አውሳብዮስ ጨምሮ ዘግቧል [4]። በመሆኑም ቀለሜንጦስ አራተኛው ወንጌል የተጻፈው በሐዋርያው ዮሐንስ እንደሆነ ያምን ነበር። 200 ዓ.ም አካባቢ እንደጻፈ የሚገመተው ኢራኒየስ ወንጌሉን የጻፈው የተወደደው ደቀ መዝሙር ዮሐንስ መሆኑንና የጻፈውም በኤፌሶን ሳለ እንደነበረ ተናግሯል [5]። በተጨማሪም የተወሰኑትን የአዲስ ኪዳን መጻሕፍት ዝርዝር ይዞ የተገኘውና ከ 180-200 ዓ.ም ድረስ እንደተጻፈ የሚገመተው የሙራቶሪያን ጽሁፍ አራተኛውን ወንጌል በዮሐንስ እንደተጻፈ ይመሰክራል። ዮሐንስ ወንጌሉን እንዴት ጻፈው? ለሚለው ጥያቄ ይህ ጽሁፍ ተአማኒ ዝርዝር ባይኖረውም ወንጌሉ በተጻፈባቸው አመታት ውስጥ ጸሃፊው ዮሐንስ መሆኑ ይታመንበት እንደነበር ያሳያል [6]። በመሆኑም ከውስጣዊ ማስረጃዎች ጸሃፊው ፍልስጤም ምድር ውስጥ የሚኖር አይሁዳዊ መሆኑን፣ የኢየሱስ የአይን ምስክር መሆኑን፣ከአስራ ሁለቱ ደቀ መዛሙርት አንዱ መሆኑንና ከጽሁፉ ዝርዝሮች በመነሳት ጸሃፊው ዮሐንስ እንደሆነ መገመት እንደሚቻል ስንረዳ ከውጫዊ ማስረጃዎች ደግሞ ወንጌሉ ለተጻፈበት ዘመን የሚቀርቡ አባቶችና ተጨማሪ ጽሁፎች የዮሐንስን ጸሐፊነት እንደሚደግፉ መገንዘብ ይቻላል። የዮሐንስ ወንጌል በራሱ በዮሐንስ መጻፉን የሚጠራጠሩ ምሁራን ቢኖሩም ከላይ ባነሳናቸው ማስረጃዎች መሠረት ጸሃፊው ሐዋርያው ዮሐንስ መሆኑን ተቃውሞ በብቃት የሚቆምና ተለዋጭ ጸሃፊ በርግጠኝነት የሚያቀርብ መከራከሪያ ግን ሊገኝ አልቻለም። የተጻፈበት ዘመንና ስፍራ ➥ልክ እንደ ጸሃፊው ማንነት ሁሉ በዘመናችን ምሁራን ዘንድ ወንጌሉ መቼ እንደተጻፈ የማያባራ ክርክር ይደረጋል። አንዳንዶች የተጻፈው በ2ኛው ክፍለ ዘመን መካከለኛ አመታት፤ ማለትም 150 ዓ.ም አካባቢ እንደሆነ በማንሳት ይከራከራሉ። ይሁን እንጂ የሥነ ቁፋሮ (Archaeology) ጥናቶች የሚያሳዩት የዮሐንስ ወንጌል የተጻፈው በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን መገባደጃ ላይ መሆኑን ነው። የዮሐንስ ወንጌል የመጀመሪያው እደ-ክታብ Papyrus 52 የሚባል ሲሆን የምዕራፍ 18ን የተወሰኑ ክፍሎች የያዘና በ130 ዓ.ም አካባቢ እንደተጻፈ የሚገመት ቁራጭ ብራና ነው። ቀጥሎም ከምዕራፍ 1-14 ድረስ ያለውን አብዛኛውን ክፍልና የቀሩትን ምዕራፎች በከፊል የያዘው Papyrus 66፤ እንዲሁም ከምእራፍ 1-11 እና ከ12-15 ድረስ የያዘው Papyrus 75 ከጥንታዊ እደ ክታባት ይመደባሉ። እነዚህ እደ ክታባት ከሁለተኛው ክፍለ ዘመን መጨረሻ ይመዘዛሉ [7]። እንግዲህ እስካሁን የሚታወቀው የመጀመሪያው የወንጌሉ ቅጂ (P 52) የተጻፈው እንደተገመተው በ 130 አካባቢ ከነበረ የመጀመሪያው ጽሁፍ የተጻፈው በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን መሆኑ ግድ ነው። ወንጌሉ የት ተጻፈ? ለሚለው ጥያቄ ደግሞ በቀለሜንጦስ ዘእስክንድርያንና በኢራንየስ ትውፊቶች ላይ መደገፍ ግድ ይለናል። ቀለሜንጦስ እንደጻፈው ዮሐንስ ከፍጥሞ ደሴቱ ስደት ወደ ኤፌሶን የተመለሰው ንጉሡ ዶሚሽያን ከሞተ በኋላ (ከ 81-96) ሲሆን ኢራኒየስ ደግሞ ሐዋርያው እስከ ትራጃን ንግስና ዘመን ድረስ (ከ98-117) እዚያው ኤፌሶን እንደነበረ ይናገራል [8]። ይህም ወንጌሉን በዚያ ጊዜ (በመጀመሪያው ክፍለ ዘመን መጨረሻ) በኤፌሶን ሳለ ጽፎታል የሚል ግምትን አሳድሯል። ስለዚህም የዮሐንስ ወንጌል ከ80-90 ዓ.ም ሐዋርያው ዮሐንስ በኤፌሶን ሳለ የጻፈው ወንጌል መሆኑ በብዙዎች ዘንድ ተቀባይነት አለው። የዮሐንስ ወንጌል ዋና ዋና ይዘቶች ➥በመጀመሪያው ምእራፉ ስለዋና ገጸ ባህርዩ ማንነት በዝርዝር ይናገራል። ይህም ገጸ ባህርይ በመጀመሪያ ከእግዚአብሔር ጋርየነበረው በፍጥረት ስራ ላይ ተሳታፊ የነበረውና በኋላም ሰው ሆኖ የመጣው ኢየሱስ መሆኑን ይናገራል። ➥እስከ ምእራፍ 12 ድረስ ሰፋ ባሉ ንግግሮችና በተአምራት የተገለጠውንና በልጁ ለሚያምኑ ሁሉ የዘለአለም ህይወት የሚሰጥአባቱን የተረከውን ኢየሱስን በተዋበ የመክፈቻ ንግግር መልክ እናገኛለን። ➥ከምእራፍ 13 – 20 ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን ለቀጣይ ዘመናት ሲያዘጋጅ፣ ሲመክራቸውና ሲጸልይላቸው፣ እንዲሁም ስቃዩን፣ ስቅለቱንና ሞቱን እንዲሁም ትንሳኤውን ያስቃኘናል። ➥ምእራፍ 21 ተጨማሪ የትንሳኤውን ምስክርነቶች፣ ለጴጥሮስ የተሰጠውን ተልአኮ ከሞቱ ትንበያ ጋር፣ እንዲሁም የተወደደውን ደቀ መዝሙር ምስክርነት ያስቃኘናል [9]። የዮሃንስ ወንጌል ልዩ ባህርያት ➥በሶስቱ ተመሳሳይ ወንጌላት ዘገባ የኢየሱስ አገልግሎት ትኩረት ያደረገው በገሊላ ሲሆን የዮሃንስ ወንጌል ግን በብዛት የኢየሱስን የይሁዳና የኢየሩሳሌም አገልግሎት ያስቃኘናል። ተመሳሳዮቹ ወንጌላት የኢየሱስን ምሳሌያዊ ንግግሮች፣ የእግዚአብሔርን መንግስት የተመለከቱ ስብከቶቹን፣ እንዲሁም በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ያደረጋቸውን ንግግሮች (ለምሳሌ ስለ ምጽዋት፣ ስለጋብቻና ፍቺ፣ ስለግብር ስለጭንቀት፣ ስለሃብት፣ ወዘተ…) ሲያስነብቡን የዮሃንስ ወንጌል ግን “እኔ… ነኝ” በሚሉ ሃረጋት በሚጀምሩ ኢየሱስ ስለራሱ በተናገራቸው ንግግሮች ይታወቃል። የዮሃንስ ወንጌሉ የኢየሱስ ንግግር ከሶስቱ ተመሳሳይ ወንጌላት በተለየ ከላይና ከታች፣ ብርሃንና ጨለማ… ወዘተ በሚል ሁለት ነገሮችን በተነጻጻሪነት በሚመለከት አጻጻፉ ይታወቃል። በዮሃንስ ወንጌል በተዘገበው የኢየሱስ አገልግሎት የሚገኙት ክስተቶች በሌሎቹ ወንጌላት ውስጥ አይገኙም። ማለትም የወይኑ ተአምር (2: 1-11)፣ ከኒቆዲሞስ ጋር ያደረገው ጭውውት (3:1-13)፣ የሳምራዊቷ ሴት ታሪክ (4:1-42)፣ የቤተዛታው ኩሬ ፈውስ (5:1-18)፣ የሰሊሆም መጠመቂያው ፈውስ (ምእራፍ 9)፣ የአላዛር ከሞት መነሳት (ምእራፍ 11)፣ ኢየሱስ የደቀ መዛሙርቱን እግር ማጠቡ (13: 1-11)፣ እንዲሁም ኢየሱስና ጲላጦስ ያደረጉት ዘለግ ያለ ንግግር (18:28-19:22) የሚገኙት በዮሃንስ ወንጌል ብቻ ነው [10] የዮሐንስ ወንጌል ስነ መለኮት ➥የዮሐንስ ወንጌል በውስጡ ብርሃንና ጨለማ፣ ሞትና ህይወት የሚሉ ሐሳቦች በተነጻጻሪነት ተደጋግመው ተነስተዋል፤ ይህም የኖስቲክ እሳቤን የያዘ ወንጌል እንደሆነ እንዲታሰብ ምክንያት ሆኗል። ነገር ግን የኖስቲክ መምህራን ስጋን ሁሉ እንደ እርኩስ ነገር ስለሚቆጥሩ አምላክ በስጋ እንደመጣ የሚናገረው የዮሐንስ ወንጌል ከእነርሱ አስተምህሮ በተቃራኒ እንደሚቆም ለመረዳት አይከብድም[11]። ይህ ወንጌል ልዩ የሆነ ነገረ ክርስቶስን ይዟል፤ ይህንንም ኢየሱስ አባቱን ለመተረክ ከሰማይ የመጣ፤ ተግባሩንም ተወጥቶ ወደመጣበት የተመለሰ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ በአግባቡ በማሳየት ገልጦታል። (ዮሐ 1:18፣ 3:13፣ 6፡33፣ 38)። በስጋ የተገለጠ አምላክ የሚልን ነገረ ክርስቶስ በዋናነት የምናገኘውም እዚሁ ወንጌል ውስጥ ነው። መንፈስ ቅዱስ በታሪካዊው ክርስቶስ (Historical Jesus) የተገለጠውን እውነት ወደ አማኞች በማምጣት ተግባሩ ተገልጧል። የዩሐንስ ወንጌል በቃልና በስራ ለእግዚአብሔር የመታዘዝን ስነ ምግባር በኢየሱስ በኩል ያስተምራል። ዋናውን የኢየሱስን ትእዛዝ ፍቅርንና ትህትናን በአማኞች መሃል ያስተዋውቃል (ዮሐ 13:14)። ይህንንም ኢየሱስ ራሱ በተግባር በማድረግ አስተምሯል (ዮሐ 15:12-14) [12] ወንጌሉ የተጻፈበት አላማ ➥ለዚህ ጥያቄ እንደ መልስ የሚቀርበው የመጀመሪያው መላ ምት ዮሐንስ ወንጌሉን የጻፈው ለሶስቱ ወንጌላት ተጨማሪ ድጋፍ ይሆን ዘንድ ነው ይላል። በዚህ መላ ምት መሠረት ሐዋርያው ከእርሱ በፊት የተጻፉትን ሶስቱን ወንጌላት በተመለከተ ጊዜ ይዘታቸው አላረካውም፤ ስለዚህም ወንጌሉን በዚህ መልኩ ጻፈው። ነገር ግን ወንጌሉ በሶስቱ ወንጌላት ላይ ጥገኝነት ባለማሳየቱ ይህ

የዮሐንስ ወንጌል አጭር ሐተታ Read More »

ሥነ አመክንዮአዊ ተቃርኖ በመጽሐፍ ቅዱስ አይሳሳቴነት – ክፍል 2

ለዘብተኛ ምሑራን ሆኑ ከክርስትና ውጪ ባሉ ሰዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ህጸጽ አልቦነትን በዚህ መልኩ ሲቃወሙ እናያለን፦መንደርደሪያ አንድ፦ በእጆቻችን ላይ ህጸጽ አልቦ የሆኑ እደ ክታባት የሉንምመንደርደሪያ ሁለት፦ እደ ክታባት ቅዱሳት መጻሕፍት ናቸው[¹]ስለዚህ: መጽሐፍ ቅዱስ ህጸጽ አልባ አፊዎተ ቃለ እግዚአብሔር አይደለም።(ማሳሰቢያ የሁለተኛው አዋጅ አጽዕኖት ከክርስቲያናዊ እደ ክታባት ያፈነገጠ ተደርጎ እንዳይታሰብ) በመጀመሪያ ይሄን ሙግት ርዕቱ ነው ወይስ አይደለም? ከማለታችን በፊት ህጸጽ አልቦነትን(inerrancy) ምን ማለት እንደሆነ እንመልከት። ህጸጽ አልቦነትን ማለት ከስህተት የጸዳ እውነት አዘል አልያም ዝንፈተ እውነት የሌለበት ማለት ነው። አንዳንዶች የመጽሐፍ ቅዱስን ህጸጽ አልቦ አፊዎተ ቃለ እግዚአብሔርነቱ ላይ ሒስ ለማቅረብ ሲሉ ሁለት መሰረታዊ ነባቤ ቃላትን እርስ በእርሳቸው ያጠረማምሳሉ(ለምሳሌ የኤቲስቱ ባርት ኧርማን ሙግት)፤ ይኸውም የቃል በቃል አጠባበቅ እና ህጸጽ አልቦነትን ነው። ሁለቱ መሠረታዊ ልዩነቶች ያሏቸው ሲሆኑ የአንድ ነገር ንግግር ወይም ጽሑፍ የቃል በቃል አጠባበቅ ላይ ችግር ማግኘታችን ህጸጽ አልቦነቱን ላያሳጣው ይችላል። ባጭሩ የዚህ ሙግት ችግር የመጽሐፍ ቅዱስ እውነተኛ ግልጠት ማለታችን በእደ ክታቦቹ የቃል በቃል መስማማት አለባቸው ከሚለው ቅድመ ግንዛቤ ላይ የተመረኮዘ አለመሆኑን ካለመረዳት አንጻር ሊታይ ይችላል። ለምሳሌ ያክል የሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለሮሜ ሰዎች በጻፈው ደብዳቤ በሁለት የግሪክ ቃላት ብቻ ልዩነት የተፈጠረ አንድ የሚስተዋል ልዩ ምንባባት አሉ፦ እንግዲህ በእምነት ከጸደቅን በእግዚአብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ፤ሮሜ 5፥1 አንዳንድ እደ ክታባት ሰላምን እንያዝ የሚለውን ሐረግ ሲያካትቱ አንዳዶቹ ደግሞ ሰላም አለን የሚልን ነባቤ ሐረግ ይጠቀማሉ(አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚሁ መልክ ሲጠቀም ይታያል)። የግሪኩ ቃል አንዱ ኤኾሜን በኦሜጋ ፊደል(ἔχωμεν) ሲጠቀም ሌላኛው ደግሞ ኤኾሜን በኦሚክሮን ፊደል (ἔχὸμεν) ይጠቀማል። ምንም እንኳን እንደዚህ አይነት የቃላት ልዩነት ቢኖርም የአረፍተ ነገሩ ዋና ሐተታዊ እውነታው የሚደበዝዝ ወይም ሊናድ አይችልም። የአረፍተ ነገሩ ትክክለኛው አቀማመጥ፦ “peace is the possession of those who have been justified” እስከሆነ ድረስ የክታቡን ህጸጽ አልቦነት በቃላት ቦታ መለዋወጥ ሆነ አለመመሳሰል ልናጣው በፍጹም አንችልም። ምክንያቱም ህጸጽ አልቦነት የሚገናኘው ከትክክለኛ ዓርፍተ ሐሳቦ ጋር ነው። ነገር ግን አንድ መታወቅ ያለበት ነገር ቢኖር አንዳንድ የእደ ክታባቱ ልዩ መሆን(texual variant) ችግር ሆነው የሚመጡበት ጊዜ ሆነው የሚመጡበት ሰዓት ሊኖር ይችላል። ይሄን መሠል ችግሮች አገኘን ማለት ግን እንደነዚህ አይነቱን ለመለየት አስቸጋሪ አይደለም እንደውም በቀላሉ የሚለዩ ናቸው። ሙስሊሞችም ሆኑ ለዘብተኛ ምሑራን የሚጠቅሷቸው ነጠሮች በአጥባቄው ምሑራኑ ዓለም ውስጥ መልስ ተሰጥቷቸው ያለፉ ናቸው። በምሳሌም እውቁ የምንባባዌ(ጽሑፋዊ) ሕያሴ ስኮላር ዋላስ 99 በመቶ በላይ የሚሆኑት በእነርሱ መካከል ልዩ ምንባባት እንደሌሉ ይናገራሉ። Matthew Barrett በመጽሐፉ እንዲህ ሲል ያስቀምጠዋል፦ “….textual variations in the copies do not imply that the original manuscripts contained errors. These variations are seen as part of the natural process of transmission over time, but they do not undermine the truthfulness of Scripture as it was originally given. the existence of textual variants should not shake one’s confidence in the inerrancy of the Bible, as the original text remains reliable and intact, even if minor discrepancies exist in the copies..” በዚህ መሠረት ደግሞ በመጀመሪያው ጽሑፍ መካከል ልዩነት አለና በኋላ ላይ ባሉት ኮፒዎች ልዩነት አለ በሚሉ ሰዎች ሙግት ልዩነቶቹ በራሷቸው የእግዚአብሔር ቃል ህጸጽ አልቦ መሆኑን ሊሸፍኑ አንዳች አይቻላቸውም በማለት ክታባቱን ያጠኑ ምሑራን በዚህ መልክ ያስቀምጡታል ማለት ነው። ማጣቀሻ Barrett, Matthew. God’s Word Alone: The Authority of Scripture. Zondervan, 2016

ሥነ አመክንዮአዊ ተቃርኖ በመጽሐፍ ቅዱስ አይሳሳቴነት – ክፍል 2 Read More »

መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እና ሕጸጽ አልቦ

ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለባቸው ናቸው፤ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማቅናት በጽድቅም መንገድ ለመምከር ይጠቅማሉ።2ኛ ጢሞ 3፥16 (አዲሱ መ.ት) መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ለክርስትና እምነተ መርሕ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ የማይሳሳትና ሊሳሳት የማይችል ባለሥልጣን እንዳለው የሚገልጽ ክርስቲያናዊ መርሕ ነው። ይሄንን ሐሳብ ብርሐነ አለም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ለመንፈሳዊ ልጁ ለጢሞቴዎስ በጻፈለት መልዕክት ላይ ቅዱሳት መጻሕፍት ሁሉ እስትንፋሰ እግዚአብሔር (ቴዎኔዩስቶስ/θεόπνευστος) መሆናቸውን ሲነግረው እንመለከታለን። በዚህም መሠረት ቅዱሳት መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔር አፊዎተ እግዚእ ማለትም በቀጥታ መለኮታዊ ግልጠት መሆናቸውን እና ከዚህም የተነሳ እውነተኛ እና ሕጸጽ አልቦ ናቸው ብለን እናምናለን። የቤተ ክርስቲያን አበው ይህንኑ ሐሳብ ሲደግፉ ይስተዋላል። የአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን አባት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ(John Chrysostom) ክፍሉን በድርሳኑ ላይ ሲያብራራ ቅዱሳት መጻሕፍት አፊዎተ እግዚእ መሆናቸውን እና ለአማኞች ትክክለኛ የቅድስና እና የህይወት መንገድ መሮች መሆናቸውን ይናገራል።[1] ቅዱስ ሔሬኔዎስ ዘሊዮን በመድፍነ መናፍቃን መጽሐፉ ላይ ቅዱሳን መጻሕፍት እስትንፋሰ እግዚአብሔር እና የበላይ ባለስልጣን መሆናቸውን በመግለፅ እውነተኛው የክርስትና አስተምህሮ መሠረት የሆኑ  እና ሐሰተኛውን አስተምህሮ የምንከላከልባቸውም (የምንመክትባቸው) ጭምር እንደሆኑ ይገልጻል (Against Heresies)።  ቅዱሳት መጻሕፍት የእግዚአብሔር እስትንፋስ በመሆናቸው ስለ እውነት ፤ ክርስትያናዊ የሕይወት መርህ እና ድነት አስፈላጊ የሆኑትን ሥነመለኮታዊ አስተምህሮ ሁሉ በውስጡ ያካተቱ በመሆናቸው ለዚህም አስተምህሮ ብቁ ባህሪዎት እንዳላቸው እንመለከታለን። ቅዱስ አትናቴዎስ (Athanasius of Alexandria) በክታቡ እንዲህ ሲል ይናገራል፦ The Holy Scriptures, given by inspiration of God, are of themselves sufficient toward the discovery of truth.[2] ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ለክርስቲያን ሥነመለኮት ብቁ ነው ስንል በራሱ ትውፊትን የሚያገልል ወይም የሚቃወም ተደርጎ በፍጹም መታሰብ የለበትም። ይሄ አስተምህሮ ግን ማለትም የመፅሐፍ ቅዱስን በቂነት(Material Sufficiency) ልጅ የጥንት ማህበረሰብ ስምምነት(ኮንሴንሰስ ፓትረም) ያለው እምነት መሆኑ ፕሮቴስታንት በዚህ ላይ ጽኑ መሠረት እንዳለው እናውቃለን። ይሄ አስተምህሮ ግን ለትውፊት, ለአምልኮ ሥርዓት ሆኑ ለጉባኤያት አስተምህሮ እና እውነተኝነት ትክክለኛው መመዘኛ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑን የሚናገርም ነው። በተጨማሪም ሁሉም ከፍተኛ ባለሥልጣን ለሚለው ለመጽሐፍ ቅዱስ መገዛት እና ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር ህብረት መፍጠር እንዳለባቸው የሚያመላክትም ጭምር ነው። ምክንያቱም ትውፊት, የአምልኮተ ሥርዓት ሆኑ, ጉባኤዎች የማይሳሳቱ ስላልሆኑ ማለትም ሊሳሳቱ የሚችሉ በመሆናቸው ምክንያት መመዘን ያለባቸው አይሳሳቴና የእግዚአብሔር እስትንፋስ በሆነው በመጽሐፍ ቅዱስ ነው። ይህንን ሐሳብ ቅዱስ አውግስጢኖስ ዘሒፖ(Augustine of Hipo) በመደገፍ መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ዝንፈተ እውነት የሌለበት እንደሆነ ይናገራል፦ I have learned to yield this respect & honor only to the scripture, of these alone do I most firmly believe that completely inerrant (free from error) [3] ትውፊትም, የአምልኮ ሥርዓቶች ሆኑ ጉባኤያት ስህተት ሊገኝባቸው ይችላል። ምክንያቱም የትውፊት አስተላለፋቸውን በተመለከትን ጊዜ በሰዋዊ አተረጓጎም, በተፈጥሮዋቸው የሚሳሳቱ ስለሆኑ እና በባህል ተጽዕኖ የታሰረ በመሆኑ ትክክለኛው መልዕክቱ ተበላሽቶ(ተቀይሮ) ሊሆን ይችላል። በተለይም ትውፊት እና የሃይማኖት ሥርዓታዊ ድርጊቶች በዘመናት መሐል የተለያየ ብርዘት እና ለውጥ ሊገባባቸው የሚችሉ ናቸው። ለምሳሌ ያክል በካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳቱ መብት እያደገ እየተሻሻለ በመምጣት ወደ የፖፑ አለመሳሳት(papal Infallibility) በመጨረሻም ወደ ስህተት መምጣታቸው የሚዘነጋ አይደለም። በተጨማሪም በነገረ ማሪያም ያላቸውን ዶክትሪን እጅጉን እየለጠጡ በመምጣታቸው ወደ Immaculate conception(አንዳንድ ኦርቶዶሳውያንም ይህንኑ አስተምሮ ይቀበላሉ) እንዳመሩ እንመለከታለን። የፑርጋቶሪ ምልከታ ሌላው የሚጠቀሱ ጉዳዮች ናቸው። በኦርቶዶክሱም ሆነ በካቶሊኩም የሚስተዋለው የመጽሐፍ ቅዱስ የቀኖና ችግር ስንመለከት ትውፊት በዘመናት መካከል ሊቀያየር እና ሊበከል የሚችል ጉዳይ ሁኖ እናገኘዋለን። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በማቴዎስ ወንጌል 15:3 ላይ በመለኮታዊ ግልጠት ላይ ያልተመሠረተውን ያልሆነውን የአይሁዳውያንን ትውፊት ሲመረመር እንመለከታለን። የመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እነዚህ ሁሉ ትውፊት እና ስርዓተ አምልኮ በሕጸጽ አልቦው እና በአይለወጤው በእስትንፋሰ እግዚአብሔር ቃል መሠረት ተመዝነው መጥራት ያለባቸው ጉዳዮች መሆናቸውን የሚገልጽ ክርስቲያናዊ መርህ ነው። ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ ትክክለኛው ሚዛን እና የሁሉ የበላይ ሊሳሳት የማይችል ባለስልጣን የሆነ ያለው ነው። ማጣቀሻ 1] Homilies on 2 Timothy 2] Against the Heathen, 1:3 3] Letters, 82:3

መጽሐፍ ቅዱስ ብቻ እና ሕጸጽ አልቦ Read More »

Scroll to Top