አማኞችን በእምነት ማጎልበት

የሹዋ እቅብተ እምነት አገልግሎት ዓላማ አማኞች እምነታቸውን በልበ ሙሉነት እንዲቃኙና እንዲከላከሉ የሚያስችል ግንዛቤ መስጠት ነው።

Personal Journey

የእምነት እና የመረዳት ለውጥ ጉዞዎች

የሹዋ እቅብተ እምነት አገልግሎት፣ የእኛ ተልእኮ ተማሪዎች፣ በተለያዩ መስኮች የተሰለፉ መምህራንን ስለ ክርስቲያናዊ እቅብተ እምነት አጠቃላይ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ነው። በዚህ ዘመን አማኞች ከእነርሱ ውጪ ባሉ ቤተ እምነት የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶችና መሠናክሎችን የሚፈታ፣ እምነታቸውን በተለያዩ አካባቢዎች በነፃነት እንዲገልጹ የሚያስታጥቅ ደርዙን የጠበቀ ይዘት ያለው ትምህርት በብዙዎች ዘንድ የለም። ከእኛ ዘንድ ግን ይሄን ጉድለት ለመሙላትና ብቁ የሆነ ክርስቲያን ለማፍራት እንሰራለን።

የሹዋ እቅብተ እምነት አገልግሎት ይህን ድህረገጽ ከመክፈቱ በፊት በሌሎች ገጾቹ ክርስቲያናዊ ትምህርት እና አገልግሎት የላቀ እውቅና አግኝቷል። ይህም የእኛ ይዘት በአሁን ላይ በተለያዩ የክርስቲያን ቤተእምነቶች እውቅናው እየሰፋ በመሄዱ ምክንያት ይህ ድህረገጽ እንዲከፈት ግድ ሆኗል። ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮችን የያዙ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ገጾች ቢኖሩም ይህን ድህረገጽ ልዩ የሚያረገው ክርስቲያኖች በእምነታቸው ላይ ለተመሠረቱ ጥያቄዎች መልስ በሚሹ ወጣቶች መካከል እያደገ የመጣ ሆኖ ብዙ ተከታዮችን ያፈራ መሆኑ ነው። ከህብረተሰቡ ጋር ባለን ተሳትፎ እና በምንቀበላቸው አስተያየቶች ሁል ጊዜም እንኮራለን፣ ይህም ያለማቋረጥ ለማሻሻል እና የመዳረስ ሀብታችንን እንድናሰፋ ያነሳሳናል። በዚህ ገጽ ላይ ይህን ለማድረግም በብዙ ሰንቀናል። በዚህም አስተያየታችሁን ከታች ባሉ ማስፈንጠሪያዎች በመጠቀም እኛን ያግኙን።

ተባረኩ።

እውነት ነው እግዚአብሔር ሁሉን የፈጠረ ነው። አይመረመሬውን እንመርምር ብንል ትርፉ ድካም ነው። ይህ ማለት ግን ከቶ አናቀውም ማለት ግን አይደለም። እርሱ ራሱን በቃሉ ላይ በገለጠልን ልክ እንረዳውም ዘንድ ዛሬም በመንፈሱ በኩል ከእኛ ጋር አለና።

የሹዋ እቅብተ እምነት
እምነት እንዲያድግ በማመዛዘን እና በመረዳት ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት ብለን እናምናለን።
Reasoned Faith

ከእምነትና ከመረዳት ምርምር ባሻገር

በየሹዋ እቅብተ እምነት አገልግሎት የአንድን ሰው እምነት መረዳት አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን። እውቀት በራስ የመተማመን ስሜትን ያመጣል ፤ በራስ መተማመን ደግሞ ስለ አምላክ ትርጉም ያለው ውይይት ለማድረግ ያስችላል ።

አቀራረባችን የሃይማኖታዊ ማስተዋልን ከፍልስፍና ጥያቄ ጋር አጣምሮ የያዘ ነው ። የሐሰት ትምህርቶችን እንቃወማለን፤ እንዲሁም የክርስትናን አመለካከት ለማመቻቸት ሌሎች እምነቶችን ከልባችን እንመርምራለን።

አባል ይሁኑ

ሃሳብን የሚጭሩ ጽሁፎች በኢሜል እንዲደርሶ አባል ለመሆን ይመዝገቡ

Email
The form has been submitted successfully!
There has been some error while submitting the form. Please verify all form fields again.
Scroll to Top